ህዳር ፰ (ሰምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ የሚገኙ የኢትዮጲያ ሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እስር ቤት ድረስ ሔዶ ለመጎብኘት ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች በከፍተኛ መዘጋጀታቸውን ከአዲስ አበባ የመጣው ዜና ያስረዳል። የፊታችን ዕሁድ ቃሊት ወህኒቤት ድረስ ተሰባስበው በመሄድ ታሳሪዎቹን ለመጎብኘት በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች ጥሪ መተላለፉ የተሰማ ሲሆን በጉዞው ሒደት ተንኳሽ ድርጊቶች የሚፈፅሙ ሃይሎች ሠርገው እንዳይገቡ ሁሉም ሙስሊም የጥንቃቄ ርምጃ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የፌድራል ፖሊሶች ህፃን በናትዋ ጀርባ ላይ እንዳለች በዱላ መተው መግደላቸው ተዘገበ
ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሀና ማሪያም አካባቢ መንግስት የሚያደርገውን መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ አስፈፃሚ የሆኑ የፌድራል ፖሊሶች ህፃን በናትዋ ጀርባ ላይ እንዳለች በዱላ መተው መግደላቸው ተዘገበ። ከ30.000 ሺህ በላይ አባ ወራ በተፈናቀለበት የንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ ትላንት በናትዋ ጀርባ እንዳለች በፌድራል ፖሊስ ተመታ ከሞተችው ህፃን ጋር የሞቱት ቁጥር አራት ደርሰዋል። መጠለያም ...
Read More »በሊቢያ የሚገኙ ኢትዮጽያውያን ከካምፕ እንዲወጡ በመደረጋቸው ለብርድና ለሀሩር መዳረጋቸውን ገለጡ
ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ሬዲዮ ያናገራቸው በሊቢያና በቱኒዚያ ድንበር ላይ የሚገኙ ኢትዮጽያውያኖች እንደገለፁልን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽን ጉዳያቸውን የያዘ ቢሆንም ከፊሎቹን በስደተኝነት ተቀብሎ ከፊሎቹን ሳይቀበላቸው በመቅረቱ ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል ። በሊበለያ ከ10 እስከ 20 አመት የኖሩ ነገር ግን በሊቢያ በተነሳው ህዝባዊ አመጽ ወደካምፕ እንዲገቡ ከተገደዱት ከነዚህ ኢትዮጽያዊያን መካከል የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ኢትዮጽያዊ እንደገለፀችልን ያለ ...
Read More »አይ ኤል ኦ ኢትዮጵያ የመደራጀት መብትን አግዳለች አለ
ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት አይ ኤል ኦ ኢትዮጵያን የማህበራትን የመደራጀት ነጻነት ከገደቡ ቀንደኛ 5 ሀገራት አንዶ መሆኖን አስታወቀ። ጄኔቫ የሚገኘው አለም አቀፉ የሰራተኞች ማህበር ዛሬ ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳስታወቀው የመሰባሰብና የመደራጀት ነጻነት ካፈኑና አደገኛና ፍጹም የሆነ ገደብ የጣሉ ሲል ካወጣቸው 32 ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ፣ ካምቦዲያ፣ ፊጂ፣ አርጀንቲናና ፔሩ በዋነኝነት አስቅቀምጦቸዋል። የአይ ኤል ኦ ...
Read More »በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱ ተነገረ
ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጲያ የሕዝብ ምሬት መባባሱን ጮህቱም ሰሚ ማጣቱን አንዲት የመንግስት ባለስልጣን ገለጹ። ሥለችግሩ ብናነሳም የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ምን አገባችሁ በሚል መሳለቂያ ያረጉናል ሲሉም ምሬታቸውን ሲገልጹ በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን ታይተዋል። የዲሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈጻሚ ተቋማት ኋላፊነት በሚል ርዕስ ባጠቃላይ በሚንስትሩ ጽ/ቤት በተካሄደ ውይይት ላይ ይህንን የተናገሩት የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዳይሬክተር ወ/ሮ ፎዚያ አሚን ናቸው። በመንግስት ...
Read More »በደራ ወረዳ የተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት አነጋጋሪነቱ ቀጥሎአል -የወንጀሉ ተባባሪዎች የሆኑ 3 ፖሊሶች እስካሁን አልተያዙም
ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የፍትህና ጸጥታ ሹም የሆነ ግለሰብ ከሶስት ፖሊሶች ጋር በመ ሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ ማድረጉን፣ እንዲሁም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ከተደረገ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ባለቤቱ አስጸያፊ ድርጊቶችን እንድትፈጽም፣ በሰደፍ በመመታቱዋም የስድስት ...
Read More »በኦህዴድ ውስጥ የተፈጠረው ችግር እንደቀጠለ ነው
ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ እንደቀጠለ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ የኦሮሞ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት አሁንም በችግር እየታመሰ ነው፡ የኢሳት የኦህዴድ ምንጮች እንደገለጡት በሀረሪ ክልል የሚገኙ አንዳንድ የኦህዴድ ባለስልጣናት ከሀላፊነት ተነስተዋል። ኦህዴድ ካካሄደው ግምገማ በሁዋላ የተባረሩት ባለስልጣናት አብዛኞቹ በአናሳ ብሄር አንገዛም ከሚሉት የኦህዴድ ባለስልጣናት መካከል የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል። የሀረሪ ...
Read More »አምባሳደር ተወልደ አጋመ ከህወሀት ለቀቁ
ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሕወሐት ማዕከላዊ ኰሚቴ አባል የሆኑት አምባሳደር ተወልደ ገብሩ (በቅጽል ስማቸው ተወልደ ዓጋመ) በገዛ ፈቃዳቸው ከፓርቲው መልቀቃቸውን ኢየሩሳሌም አርአያ ዘገበ። የህወሀትን ገመና ፈልፍሎ በማውጣት የሚታወቀው ጋዜጠኛ አርአያ ተስፋ ማርያም የድርጅቶቹን ምንጮች በመጥቀስ እንደዘገበው፤ አምባሳደር ተወልደ አጋመ በቅርቡ በተካሔደው የፓርቲው ጉባኤ ላይ የመልቀቂያ ጥያቄ በማቅርበ ከማዕከላዊ ኰሚቴ አባልነት ራሳቸውን እንዳገለሉአስታውቀዋል። በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ተወልደ «አጋሜ» ...
Read More »በደራ ወረዳ በአንዲት ሴት ላይ የተፈጸመውን ግፍ በይፋ ያጋለጡት የቀበሌው ሊቀመንበር ቃለምልልስ ሰጡ
ህዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የወረዳው የአስተዳደርና ፍትህ ሀላፊ የቅርብ ዘመድ የሆነ አቶ አየለ የተባለ ከሌሎች ሁለት ግብረ አበር ፖሊሶች ጋር በመሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ ማድረጉን፣ እንዲሁም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ከተደረገ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ...
Read More »ከአዲስ አበባ ውጪ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ መኢአድ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ
ህዳር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአዲስ አበባ ውጪ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በኢህአዴግ ካድሬዎችና በመንግሥት ባለሥልጣናት ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን አስታወቁ፡፡ የክልል ምክር ቤቶችና የወረዳዎች የምርጫ እንቅስቃሴ በመጀመሩ የኢህአዴግ ካድሬዎች እንደተለመደው አውሬ ባህሪያቸው ጎልቶ ወጥቷል ያሉት የመኢአድ የአሶሳ የአመራር አባል የመንግሥት ደህነቶች የተቃዋሚ ፓርቲ በተለይም የመኢአድ ፓርቲ አባላትንና ደጋፊዎችን እየለቀሙ መሬታችሁን ለቃችሁ ...
Read More »