ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-34 የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በአባልነት ያቀፈው ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ህገ-መንግስቱን በመጣስ ሶስት ጠ/ሚኒስትሮች በሾሙት በ/ጠ/ሚ/ር ሀ/ማርያም ደሳለኝ፣ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና ሹመቱን በተቀበሉት ሶስቱ ም/ጠ/ሚኒስትሮች ላይ ክስ ሊመሰረት መሆኑን ገልጠዋል። ተሾሚዎቹም ቢሆኑ ሹመቱን መቀበል የለባቸውም ነበር ያሉን መግለጫውን አስመልክተን ያናገርናቸው ያስተባባሪ ኮሚቴው ፀሀፊ አቶ ግርማ በቀለ ህገ-ወጥ መሆኑን እያወቁ በመቀበላቸው ተከሳሾች ኛቸው ብለዋል። በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት ላይ የተመሰረተው ክስ አግባብ አይደለም ያሉት የ34 ተቀዋሚ ፓርቲ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ፀሀፊ አቶ ግርማ በቀለ በዚህና በአዲስ አበባ ከተሞች በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ ቤታቸውን በማፍረስ የመኖር መብታቸውን መንግሰት በመጣሱ እንቃወመዋለን እዚህ ላይም እየሰራን ነው ብለዋል። መንግስት ሁሉንም በእኩል የማስተዳደር ሀላፊነት እንዳለበት የገለፁት አቶ ግርማ ከዚህ በፊት ያቀረብናቸውን ጥያቄዎች አልመለሱልንም ለዚህም በተለየ አግባብ ለጥያቄያችን መልስ ለማግኘት እንሰራለን ሲሉ አስታውቀዋል።
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በእስር ላይ በሚገኙት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት እስላማዊ መንግስት ለመመስረት እንሰራ ነበር ብላችሁ እመኑ በመባል እየተደበደቡነ እየተሰቃዩ መሆኑ ተገለጠ
ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእስር ላይ በሚገኙት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት እስላማዊ መንግስት ለመመስረት እንሰራ ነበር ብላችሁ እመኑ በመባል እየተደበደቡነ እየተሰቃዩ መሆኑ ተገለጠ:: በዛሬው እለት የነበራቸው ቀጠሮም ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ መሰረዙ ታወቀ:: በሌላ በኩል ደግሞ በነገው እለት በአጠቃላይ በሀገሪቱ ታላቅ የተቃውሞ ትእይንት በየመስኪዱ እንደሚደረግ ተገለጠ:: ምንጮቻችን ባደረሱን መረጃ መሰረት አሸባሪ በሚል ክስ የተመሰረተባቸው የሙስሊሙ ...
Read More »በግብጽ በፕሬዚዳንቱ ቤተመንግስት በተቃዋሚዎችና በፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች መሀከል በተነሳ ግጭት 5 ሰዎች መገደላቸውንና ከ 644 በላይ መቁሰላቸውን ቢቢሲ ዘገበ::
ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ይህን ግጭት ተከትሎም የግብጽ ሰራዊት ከፕሬዚዳንቱ ቤተመንግስት አካባቢ ተቃዋሚዎችንና የመገናኛ ብዙሀን አባላትን በማስወጣት ላይ ይገኛል:: ከቤተ መንግስቱ አካባቢ እንዲለቁ በተሰጣቸው የሰአት ገደብ መሰረት አብዛኖቹ ተቃዋሚዎች መልቀቃቸው ሲታወቅ የተወሰኑ የተቃዋሚ አክቲቪስቶች በዛው እንደሚገኙ የቢቢሲዘገባ አመልክቶል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋነኛው የግብጽ እስላማዊ አካል ፕሬዚዳንት ሙርሲ የሀገሪቱን አጠቃላይ ስልጣን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል የተባለውን ህግ እንዲያነሱ ጠይቆል:: ...
Read More »የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብሄር ብሄረሰቦችን በአል አከባበር ነቀፉ
ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢሳት ያነጋገራቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የብሄር ብሄረሰቦች በአል አከባበር የይምሰል ነው በማለት ተችተዋል። የተረፈች ልጅ በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስድስት ኪሎ ግቢ ተማሪ እንደተናገረው ኢትዮጵያ በጥቂቶች የምትገዛ ፣ አብዛኛው ህዝብ የበይ ተመልካች የሆነባት አገር ናት ። በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የብሄሮች መብት አለመከበሩ በግልጽ የሚታየው በስድስት ኪሎ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ...
Read More »በባህርዳር በመቶዎች የሚቆጠሩ በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች ተይዘው አንድ ካምፕ ውስጥ ታጎሩ
ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ለኢሳት ከባህርዳር የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማዋ ውስጥ በመዘዋወር ይለምኑ የነበሩ ሰዎች ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ ተሰብስበው ጅንአድ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ እንዲጠራቀሙ ተደርጓል። ጎስቋሎቹ የተያዙት በባህርዳር የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች በአል ውበት ይቀንሳሉ፣ ለከተማዋም መጠፎ ምስል ይፈጥራሉ በሚል ምክንያት ነው። እንደ ፈለጉ የመዘዋወር ህገመንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ እንዲታጎሩ የተደረጉት ጎስቋሎች፣ በአሁኑ ጊዜ በቂ ምግብና ...
Read More »በአማራ ክልል የሚገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እያቋረጡ ወደ አረብ አገራት በብዛት በመሰደድ ላይ ናቸው
ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአማራ ክልል የሚገኙ መምህራን ለኢሳት እንደገለጡት በሰሜን ወሎ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት ብቻ ከመስከረም እስከ ታህሳስ ወር ከ 5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉት ክፍሎች ውስጥ 44 ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ አረብ አገራት ሄደዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ፓስፖርት በማውጣት ጉዞአቸውን እየተጠባበቁ ነው። መምህራንም እንደ ተማሪዎች የሚሰደዱ መሆናቸው ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል። መንግስት ...
Read More »የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊዎችን ጉዳይ ለማየት ተጨማሪ ቀጠሮ ሰጠ
ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- 16ኛው ወንጀል ችሎት የኮሚቴ አባላቱ ጠበቆች ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ ነበረ ቢሆንም፣ ቀጠሮውን ለታህሳስ 8 ፣ 2005 ኣም ለማሸጋጋር ወስኗል። ዳኞች ለጠበቆችና አቃቢ ህጎች፣ የተከሳሾች ቁጥር ብዙ በመሆኑ ሁሉንም ተመልክተን ለመወሰን አልቻልንም በማለት እንደነገሯቸው ታውቋል። ዳኞቹ እስረኞቹ ችሎት እንዳይቀረቡ የተደረገው ለደህንነታቸው ሲባል ነው በማለት መናገራቸውን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ...
Read More »ጠ/ሚ/ር ሀይለማሪያም ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጋር በማናቸውም መድረክ አስመራ ጭምር ሄደው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጡ
ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጠ/ሚ/ር ሀይለማሪያም ደሳለኝ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በማናቸውም መድረክ አስመራ ጭምር ሄደው ለመነጋገር ዝግጁ መሆናቸውን ገለጡ:: አቶ ሀይለማሪያም ይህንን የገለጡት ከአልጀዚራ ቴሌቭዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው:: በዛሬው እለት በተሰራጨው የአቶ ሀይለማሪያም ቃለምልልስ አስመራ ሄዶ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የመነጋገር ፍላጎት የቀድሞው ጠ/ሚ/ር መለስ ዜናዊ ፍላጎት ጭምር እንደነበር ገልጠዋል:: አቶ መለስ ከአቶ ...
Read More »የዩናይትድ ስቴት ፓርላማ አመታዊው የዲቪ ሎተሪ እጣ እንዲቆም አርብ እለት ባካሄደው ስብሰባ ገለጠ
ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ይህ ውሳኔ በአሜሪካ ሴኔትና በፕሬዚዳንቱ ካልጸደቀ በስተቀር ተግባራዊ እንደማይሆን ታውቆል:: በሪፐብሊካን አነሳሽነት ለፓርላማ እንደቀረበ በተገለጠው የዲቪ ሎተሪ ይቁም ጥያቄ ከ245 የፓርላማ አባል የ 139ኙን ድምጽ በማግኘት ነው ያለፈው:: በሀገሪቱ ስደተኞችን ለመግታት በሚለው የሪፐብሊካን አንዱ ስትራቴጂ እንደሆነ በሚነገርለት የዲቪሎተሪ ይቁም ሀሳብ በተለዋጭ ከአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በኢንጂነሪን ፡ በቴክኖሎጂና በሳይንስ ለተማሩ የውጭ ሰዎች ቪዛው ይሰጣል ...
Read More »ከአውሮፓና ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን በመንግስት ደህንነቶች እንደሚመረመሩና እንደሚታሰሩ ተገለጠ
ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ጋምቤላ ቤተሰቦቻቸውን ለመጎብኘት ተጉዘው የነበሩት ዶ/ር ማኝ አንግ ለኢሳት እንደገለጡት በጋምቤላ በክልሉ ፕሬዚዳንት ተጠርተው ደህንነቶች እንደሚፈልጎቸው ከተነገራቸው በሆላ ለ 2 ሰአት ያህል እንደመረመሮቸው አስታውቀዋል:: ማንኛውም የጋምቤላ ተወላጅ ወደተወለደበት ሀገር ሲሄድ ያሬድ፡ ኤፍሬምና ዳዊት በሚባሉ የመንግስት ደህንነቶች ይመረመራል፤ በጋምቤላ ከሚገኙ የተቃዋሚ መሪዎች፤ ከግምቦት ሰባትና በጋምቤላ ከሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ...
Read More »