.የኢሳት አማርኛ ዜና

መንግስት አቡነ መርቆርዮስ ቢመለሱ አልቃወምም ማለቱ ተዘገበ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴርን ጠቅሶ ሳምንታዊ ሰንደቅ  እንደዘገበው መንግስት በህገ-መንግስቱ መሠረት በሃይማኖቶች የውስጥ ተግባር ጣልቃ መግባት ስለማይችል አቡነ መርቆርዮስ ይመለሱ ወይም አይመለሱ የማለት ህገ-መንግስታዊ መሰረት የለውም። በመሆኑም በኢትዮጵያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ፤ <<4ኛው ፓትርያሪክ የነበሩት አቡነ መርቆርዮስ ይመለሱ ብሎ ካመነ  መንግስት ተቃውሞ የለውም>>ብሏል-ሚኒስቴሩ። የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ...

Read More »

መምህራን ተማሪዎችን ፈርመው እንዲረከቡ የሚያደርግ መመሪያ ተዘጋጀ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች መጨመራቸውን ተከትሎ ፣ በአማራ ክልል የሚያስተምሩ መምህራን ተማሪዎችን በሰሚስተሩ መጀመሪያ ላይ ቆጥረው ተረክበው፣ በሰሚስተሩ መጨረሻ ላይ ቆጥረው እንዲያስረክቡ የሚያደርግ መመሪያ ወጥቶ ለውይይት ቢቀርብም፣ መምህራን ግን አጥብቀው ተቃውመውታል። በአንድ የትምህርት ዘመን ውስጥ መምህሩ ቆጥሮ ከተረከባቸው ተማሪዎች መካከል ከ2 ተኩል በመቶ በላይ ተማሪዎች ቢያቋርጡ፣ መምህሩ በጥፋተኝነት የሚመዘገብ ሲሆን፣ አስፈላጊውን እድገትም አያገኝም። ...

Read More »

በ ኢትዮጵያውያ ከ11 ሚሊዮን በላይ ተረጅዎች አሉ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው 4 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና በአለም ባንክና በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ በምግብ ለስራ ታቅፈው የሚረዱ 7 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ታውቋል። መንግስት ሴፍቲኔት እያለ በሚጠራው መርሀግብር የታቀፉ ኢትዮጵያውያን ምእራባዊያን ለጋሾች እርዳታቸውን ቢያዘገዩ ወይም ቢያቋርጡ ወደ አስቸኳይ ተረጅነት የሚወርዱ ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ በሚታየው የምግብ እጥረት የተነሳ በሴፍቲኔት የሚታቀፉ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱም ታውቋል። ...

Read More »

የሶሪያ ፖሊስ ሠራዊት አዛዥ የፕሬዚዳንት አል-አሳድን መንግስት ከዱ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሶሪያ ፖስ ሠራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል አብዱልአዚዝ አልሻላል የፕሪዚዳንት አል አሳድን መንግስት በመክዳት ወደ ቱርክ መኮብለላቸውን ቢቢሲ ዘገበ። የፖሊስ አዛዡ ከቱርክ ሆነው በለቀቁት የቪዲዮ ምስል ላለፉት ለተነሳበት ተቃውሞ ለ ዓመታት  መፍትሄ መስጠት ተስኖት አገሪቱን ወደ እርስበርስ እልቂት ያመራትን የፕሬዚዳንት አልአሳድን መንግስት መክዳታቸውን በግልጽ አስታውቀዋል። እንደ ቢቢሲ አገባ ሌተናል ጄነራል አብዱል አዚዝ መንግስትን ...

Read More »

አፋሮች በብዛት እየታሰሩ ሴቶቻቸውም እየተደፈሩ ነው ተባለ

ታህሳስ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከስኳር ልማት ጋር በተያያዘ በአፋር አካባቢ የሚደርሰው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መጨመሩን የአካባቢው ተወላጆች ተናግረዋል። ህዳር 20 ቀን 2005 ዓም በዱብቲ ወረዳ ቀይ አፈር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ፋጡማ ኡህመድ ገዶ የተባለች የ11 አመት ልጅ ተደፍራ መሞቷን የልጂቱ አጎት ለኢሳት ገልጸዋል። ልጂቷን የደፈሩት ሰዎች መንግስት ለስኳር ልማት ስራ ብሎ ያመጣቸው ሰራተኞ ች ይሁኑ የመከላከያ ...

Read More »

ሁለት የአረና አባላት የድርጅቱን ልሳን ሲበትኑ ተያዙ

ታህሳስ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አረና ፓርቲ በየሶስት ወሩ ማሳተም የጀመረውን የድርጅቱን ልሳን ሲያሰራጩ የተገኙ 2 የድርጅቱ አባላት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የመቀሌ የአረና  ጽህፈት ቤት ተጠሪ የሆኑት አቶ ሱልጣን ህህሸ ለኢሳት እንደተናገሩት አቶ አያሌው በየነና አቶ ተካልኝ  ታደሰ የተባሉት ድርጅቱ አባላት የተሳሩበት ምክንያት የፓርቲውን መታወቂያ አልያዛችሁም ተብለው ነው። ይሁን እንጅ ፓርቲው እስረኞቹ የድርጅቱ ...

Read More »

የ40 በ60 የ”ቤት ልማት ፕሮግራም ትግበራ የመንግስት አካላትን ግራ አጋብቷል

ታህሳስ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስአበባ ከተማ ተጀምሮ ወደ ክልሎች ይስፋፋል በሚል ትልቅ ተስፋ እየተሰጠበት ያለውና በቁጠባ ላይ የተመሰተረው የ40 በ60 ቤቶች ፕሮግራም አጀማመር ባለቤቱን አዲስአበባ አስተዳደርን ግራ በማጋባቱ እስካሁን ምዝገባ መጀመር ባለመቻሉ በተለያዩ የተምታቱ መግለጫዎች ሕዝቡን ግራ እያጋቡት መሆናቸው ተሰማ፡፡ በአቶ መኩሪያ ኃይሌ የሚመራው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አጠናሁት ባለው መሰረት አንድ ቤት ፈላጊ በስቱዲዮ፣ባለአንድ መኝታ ...

Read More »

የህወሀት አባላት የሆኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አሜሪካ በመምጣት ከትግራይ ተወላጆች ጋር ብቻ ሊመክሩ ነው

ታህሳስ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ምክትል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር  ደብረ-ጽዮን ገብረሚካኤል፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሀኖም እና አቶ አባይ ወልዱ በመጪው ጥር ወር አሜሪካ በመምጣት  ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር ብቻ እንደሚመክሩ ተመለከተ። የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናቱ በ ኢትዮጵያ  ፖለቲካዊ ጉዳይ ከትግራይ ተወላጆች ጋር እንዲመካከሩ መድረኩን ያመቻቸው የትግራይ ልማት ማህበር ነው። ደ-ብረብርሀን ብሎግ እንደዘገበው የትግራይ ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን ሴቶች ወደ ዱባይ ለሥራ እንዳይሄዱ በህግ ታገዱ

ታህሳስ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት  ሴቶች ወደተባበሩት አረብ ኢምሬት(ዱባይ) ለሥራ  እንዳይሄዱ በህግ ማገዱን አስታወቀ።ህገ-ወጥ ጉዞው ግን እንደቀጠለ ነው አለ። በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግርማ ሸለመ ፥ በጉብኘትና በግል ቪዛ በቤት ሰራተኛነት ለመቀጠር ወደ ዱባይ የሚያደረገው ጉዞ እንዲቆም የተደረገው ራስን ለከፋ ችግር የሚዳርግ በመሆኑ ነው ብለዋል። ዜጎች ህጋዊ ጥቅሞቻቸውና መብቶቻቸው ...

Read More »

ቤኔዲክት 16ኛ ለ ሶሪያ ሰላም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቀረቡ

ታህሳስ ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የልደት በዓል በመላው ዓለም እየተከበረ ነው:: ሊቀ-ጳጳስ ቤኔዲክት 16ኛ ለሶሪያ ሰላም ጥሪ ያቀረቡት ዛሬ የፈረንጆች ገናን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ነው። በቫቲካን ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ፔጥሮስ አደባባይ ቡራኬያቸውን ለመቀበል ለተገኙ በሺዎች ለሚቆጠሩ አማኞች ባስተላለፉት የመልካም ልደት መልዕክት ላይ በተለየ መልኩ ትኩረት ሰጥተው ለሶሪያ ችግር ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈለግ ጥሪ ያቀረቡት ሊቀ-ጳጳሱ፤በሁሉም ወገን  ሶሪያውያንም ...

Read More »