ታህሳስ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ከታህሳስ 17-18 በተጠራ ስብሰባ ላይ የተገኙ ነጋዴዎች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ታውቋል። ስብሰባውን ከ6 ወረዳዎች የተውጣጡ ነጋዴዎች የተሳተፉበት ሲሆን፣ መንግስት በአግልግሎት ክፍያ፣ በግብርና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ እንደሚያወያይ ጥሪ አስተላልፎ እንደነበር ነጋዴዎች ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ባለስልጣናቱ አጀንዳውን በመሰረዝ የትራንስፎርሜሽን እቅዱን እንዴት ተግባራዊ እናድርግ የሚል አጀንዳ ይዘው በመምጣታቸው ነጋዴዎች በሙሉ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢሳት ፡- ሰበር ዜና በቡሬ ግንባር ሰራዊቱ እርስ በእርስ ተዋጋ
በቡሬ ግንባር ሰራዊቱ እርስ በእርስ ተዋጋ ፤ ቁጥራቸው የበዛ የሰራዊት አባላት ተገድለዋል የቆሰሉም ብዙ ናቸው ፤ ውጥረቱም አሁንም እንደቀጠለ ነው:: በምሽቱ የዜና ዘገባ ዝርዝር ይኖረናል::
Read More »የቤተሰብ ምሽት በቶሮንቶ በደማቅ ሁኔት ተከበረ
ታህሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቶሮንቶ ከተማና በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የኢሳት የቤተሰብ ምሽትን ቅዳሜ ዲሴምበር 22 ቀን 2012 ዓ ም የዕለቱ ይክብር እንግዳ ታማኝ በየነ ከባለቤቱና ከቤተሰቡ ጋር እንዲሁም ከኦተዋ፣ ከተለያዩ የካናዳ ከተሞችና ከአሜሪካ የመጡ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል። በየዓመቱ የኢሳት የቤተሰብ ምሽትን ለማዘጋጀት ያቀደው የቶሮንቶ የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ እንዳስታወቀው የቤተሰብ ምሽቱ ለኢትዮጵያ ህዝብ በጎና ...
Read More »በኦሮሚያ ዳኞች በብዛት እየለቀቁ ነው
ታህሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በክልሉ የሚገኙ ዳኞች ከፖለቲካ ተጽእኖ ነጻ በሆነ መንገድ ለመስራት አልቻልንም በሚል ነው ስራቸውን የሚለቁት። አምና ከ100 በላይ ዳኞች ስራቸውን የለቀቁ ሲሆን በያዝነው አመት ደግሞ ቁጥሩ በእጥፍ ጨምሯል። ከአንድ ወር በፊት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ታደለ ነጊሾና አቶ ሰይድ ጁንዲን ስልጣናቸውን ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እንዲለቁ ከተደረጉ በሁዋላ፣ ...
Read More »በሎሚ ዲሳ ወረዳ የፖሊስ አባላት ከህዝብ ጎን በመቆማቸው ስብሰባ እንዳይካፈሉ ታገዱ
ታህሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን በገሳ ከተማ በተጠራው የመንግስት ሰራተኞች ስብሰባ ላይ የሎማ ዲሳ ህዝብን አዲስ የወረዳ ጥያቄን በመደገፍ ንግግር የዳረጉት የሀምሳ አለቃ ሽታየ ከታሰሩ በሁዋላ፣ ሌሎች የወረዳው ፖሊሶች ዛሬ በተጠራው ስብሰባ ላይ እንዳይካፈሉ ታግደዋል። የዞኑ ባለስልጣናት ለዲሳ ህዝብ ወረዳ አያስፈልገውም በማለት መናገራቸውን ተከትሎ አምሳ አለቃው ” ወረዳ ለህዝብ ባያስፈልግ ኖሮ ያኔ ለሲዳማ ...
Read More »የስነምግባርና የስነዜጋ ትምህርት አስተማሪዎች የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ ጫና እየደረሰባቸው ነው
ታህሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መምህራኑ ለኢሳት እንደገለጡት፣ የስነ ምግባርና የስነ ዜጋ መምህራን ከታህሳስ12 እስከ 15 ” የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት የበለፀገች ዴሞከራሲያዊት አገር ለመገንባት ያለው ፋይዳና ሕገ-መንግሥቱን ለትውልድ የማስረፅ አስፈላጊነት” በሚል ርዕስ በአዳማ፣ በሃዋሳ፣ በባህር ዳርና በጅማ ከተሞች ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ተናግረው፣ ስልጠናው በዋናነት በአገሪቱ ዲሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብቶች አያያዝና የህግ የበላይነት ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ቢጠበቅም፣ በስልጠናው ላይ ...
Read More »አዲስ አበባ በሞቱ ውሾች ሳቢያ በሽታ እንዳይነሳ ተሰግቷል፤ ቢሮዎቹ እርስ በርስ እየተወዛገቡ ነው
ታህሳስ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች ተገድለው ያልተነሱ ውሻዎች በህብረተሰቡ ዘንድ የጤና ስጋት መፍጠራቸውን ፋና ዘገበ። ራዲዮ ጣቢያው የመዲናዋን ነዋሪዎች በመጥቀስ እንደዘገበው ሰሞኑን ባልተለመደ መልኩ በተለያዩ የመዲናይቱ አካባቢዎች የሞቱ ውሾች ይታያሉ። የህብረተሰቡን ጥቆማ መሰረት በማድረግ የራዲዮ ጣቢያው ጋዜጠኞች በከተማዋ ባደረጉት ቅኝት በስታድየም ፣ በጨርቆስ ፣ በፒያሳና በገርጂ መብራት ሃይል አከባቢዎች የተገደሉ ውሻዎች ባልተለመደ መልኩ ...
Read More »ለእርቅ ጉባኤ አሜሪክ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት አባቶች በሽምግልና ኮሚቴ ላይ ጠንከር ያለ መግለጫ አወጡ
ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባና በውጭ ሀገር የሚገኙ አባታቶችን በሶስት ዙር ሲያደራድር የቆየውና ለአረተኛ ዙር ቀጠሮ ይዞ የተነሳው የሽምግልና ቡድን ባለፈው አርብ ያወጣው መግለጫ እንዳስቆጣቸው የገለጹት አባቶች ይቅርታ ካልተጠየቁ በተያዘው የእርቅ ንግግር እንደማይቀጥሉ አረጋግጠዋል:: በቤተክርስትያኒቱ መካከል እርቅ ለማውረድና ሰላምን ለማውረድ ሲንቀሳቀስ የቆየው አስታራቂ ቡድን አዲስ ፓትሪያርክ ለመምረጥ ኮሚቴ መሰየሙን በመቃወም ባለፈው አርብ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል:: ...
Read More »ያለው አማራጭ ሕገ-መንግስቱን ማሻሻል ብቻ ነው ሲሉ አንጋፋው የሕውሀት ታጋይ አቶ ስብሐት ነጋ ገለጹ
ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሐት ነጋ በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ከተማ ለንባብ ለበቃው ሰንደቅ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ የመለስ ራዕይ የሚባለው ነገር ትክክል እንደማይመስላቸውና ያለው የጋራ ራዕይ መሆኑን ገልጠዋል:: ሦስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር መሾም ያስፈለገው ክፍት የአመራር ቦታ ስለነበር እንደሆነ ያወሱት አቶ ስብሐት ነጋ: መደረግ የነበረበት ነገር መከናወኑን አስረድተዋል:: ይህ እርምጃ ሕገ-መንግስቱን ይጥሳል በሚል የሚነሳውን ተቃውሞ ...
Read More »በደቡብ ክልል የዳውሮ ወረዳ ዞን ም/ቤት አባላት ዛሬ ከጠሩት ስብሰባ 1500 ሰራተኞች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተገለጠ
ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢሳት ምንጮች ከዞኑ እንዳመለከቱት የክቢኒ አባላቱ የምረጡን ስብሰባ አድርገው በነበረ ጊዜ ህዝቡ የኔሰው ገብሬ የተሰዋበትን የሎሜ ከተማ ዋና ከተማ ዋካ ትሁን ጥያቄ ሳይመለስ ስለምርጫ አናወራም ብለው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸው ተመልክቶል:: የዳውሮ ዞን ዋና ከተማ በየኔ ሰው ገብሬና በህዝቡ ዘንድ ዋካ መሆን ይገባታል የሚል የነበረ ሲሆን የዞኑ የዴህዴን አመራር አባላት ዋካ መጤ ...
Read More »