ለእርቅ ጉባኤ አሜሪክ ቆይተው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት አባቶች በሽምግልና ኮሚቴ ላይ ጠንከር ያለ መግለጫ አወጡ

ታህሳስ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባና በውጭ ሀገር የሚገኙ አባታቶችን በሶስት ዙር ሲያደራድር የቆየውና ለአረተኛ ዙር ቀጠሮ ይዞ የተነሳው የሽምግልና ቡድን ባለፈው አርብ ያወጣው መግለጫ እንዳስቆጣቸው የገለጹት አባቶች ይቅርታ ካልተጠየቁ በተያዘው የእርቅ ንግግር እንደማይቀጥሉ አረጋግጠዋል::

በቤተክርስትያኒቱ መካከል እርቅ ለማውረድና ሰላምን ለማውረድ ሲንቀሳቀስ የቆየው አስታራቂ ቡድን አዲስ ፓትሪያርክ ለመምረጥ ኮሚቴ መሰየሙን በመቃወም ባለፈው አርብ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል::

ለእርቅ ንግግር ወደአሜሪካ የተጎዙት ልኡካን ባልተመለሱበትና  ቀጣይ ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ በያዙበት ወቅት በአንዳንድ አባቶች ግፊት እ  እርምጃ ተገቢአይደለም ሲል ነበር ሸምጋዩ ቡድን መግለጫ ያወጣው::

እንደ ሽምግልና ቡድኑ ሁሉ ፓትርያርክ ለመምረጥ አስመራጭ ኮሚቴ መሰየሙን በመቃወምና እንደማይቀበሉ በማረጋገጥ ለአሜምጽ ሬዲዮ የአማሪኛው አገልግሎት መግለጫ የሰጡት አባቶች አዲስ አበባ ከደረሱ በሆላ ሸምጋዮቹን በመውቀስ ያወጡት መግለጫ አነጋጋሪ ሆኖል::

በሸምጋዩ ቡድን አርብ ታህሳስ 23/2005 መግለጫውን ሲያወጣ በአሜሪካ የነበሩትና ታህሳስ 15/2005 ወደ ኢትዮጵያ የተጎዙት አባቶች ከአዲስ አበባ ያወጡትን መግለጫ አሜሪካ በነበሩበት ቀን ታህሳስ 13/2005 እንደሆነ መደረጉ ግልጽ አልሆነም::

የልኡካን ቡድኑ አባላት ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ገሪማ፡ ብጹእ አቡነ አትና ቲዎስ ፡ ብጹእ አቡነ ቀውስጦስ ፡ ንቡረ እድ ኤሊያስ አብርሀ ባወጡት መግለጫ ሸምጋዩ ቡድን ቅዱስ ሲኖዶሱን ተዳፍሮል በማለት ወቅሶል:: በሽምግልናውም ሂደት ወገንተኝነት ይንጸባረቅበት ነበር ሲሉ አክለዋል::

የሽምግልናው ኮሚቴ ይህንን ስህተቱን አምኖ ይቅርታ ካልጠየቀ ከዛሬ ጀምሮ በዚህ ኮሚቴ አማካኝነት በሚደረግ ንግግር አንሳተፍም ብለዋል::

ለሰላም ያለን ፍላጎት ግን አይታጠፍም ሲሉም አጠቃልዋል::