.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአውሮፓ ህብረት የልኡካን ቡድን የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ ይገመግማል

  መጋቢት ፫(ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-30 አባላት ያሉት የአውሮፓ የሰብአዊ መብቶች የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንደሚገመግም የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ። የልኡካን ቡድኑ ዋና አላማ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ መገምገም ሲሆን፣ ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ በእስር ላይ ከሚገኙት ጋዜጠኞች እና የሲቪክና የሀይማኖት መሪዎች ጋር ይገናኛል ተብሎ ይጠበቃል። ይህ በልማት ሽፋን የሚካሄደው  የልኡካን ቡድኑ ...

Read More »

አሰላ ትናንት በእሳት ዛሬ በመኪና አደጋ ተጠቃች

  መጋቢት ፫(ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በከተማዋ ትናንት ሌሊት 5 ሰአት ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ ከ10 በላይ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን በብዙ ሚሊዮን የሚገመት ንብረትም ወድሟል። ኮምፒዩተር ቤቶች፣ ምግብ ቤቶች እና የሙዚቃ መሳሪያዎች መሸጫ ቤቶች በቃጠለው ከወደሙት መካከል ይገኙበታል። የከተማው ነዋሪዎች ፖሊሶች እና የመስተዳዳሩ ባለስልጣናት ከዝርፊያ ሊታደጉዋቸው እንዳልቻሉ ለኢሳት ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው እለት አንድ ከባድ ተሽከርካሪ መኪና  መስመሩን ...

Read More »

የፍትህ ሚኒስቴር በስራ ላይ ያለውን የይቅርታ አዋጅ የሚያሻሽል አዲስ ረቂቅ ሕግ እያዘጋጀ መሆኑ ተሰማ፡፡

  መጋቢት ፫(ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሚንስቴሩ  ሕጉን ለማሻሻል የፈለገው እስር ቤቶች በእስረኞች ብዛት እየተጣበቡ በመምጣታቸው ነው ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል። ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ በፌዴራልና በክልሎች መንግስታት በሚገኙ እስር ቤቶች ቆይታቸው መልካም ስነምግባርን አሳይተዋል የተባሉ ከ62 ሺ በላይ እሰረኞች ይቅርታ ተደርጎላቸው ከእስር ቤት መውጣታቸው በአዲሱ ረቂቅ ሰነድ ውስጥ ተመልክቷል እስር ቤቶች በአመክሮ፣በይቅርታ ወይም ሙሉ የፍርድ ጊዜያቸውን ጨርሰው የሚለቀቁ እስረኞች ከእስር ...

Read More »

የውጭ አገር ባለሀብቶች በመንግስት ካድሬዎች ተማረናል አሉ

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ የተሰማሩ የአውሮፓ እና አሜሪካ ባለሀብቶች ፣ በመንግስት ካድሬዎችና ሹመኞች በመማረራቸው ስራ ለመስራት በማይችሉበት ደረጃ ላይ መገኘታቸውን ገልጸዋል። ባለሀብቶቹ ይህን የገለጹት የሁለት አመት ከስድስት ወራት የ እድገት እና ትራንስፎርሜሽንኑን እቅድ ለመገምገም በተጠራ ስብሰባ ላይ ነው። ሪፖርተር እንደዘገበው ” የመንግሥት ካድሬዎችና የበታች ቢሮክራቶች በውጭ ኢንቨስተሮች መስተንግዶ ላይ የሚያደርሱት መጉላላት ከፍተኛ ...

Read More »

እነ አቶ አያሌው ተሰማ ጥፋተኞች ተባሉ

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 8ኛው ወንጀል ችሎት የአያት አክሲዎን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አያሌው ተሰማ፣ የአክሲዮን ማህበሩ የፋይናንስና ኢንቨስትምንት ዳይሬክተሩ ዶ/ር መሀሪ መኮንን እና የፋይናንስ ዋና ክፍል ሀላፊ አቶ ጌታቸው አጎናፍር በተደራጀ መልኩ የባንክ ስራን ሲሰሩ በመገኘታቸውና በታክስ ማጭበርበር በፍርድ ቤት ጥፋተኞች ተብለዋል። ተከሳሾች ከቀረበባቸው ክሶች ውስጥ በ21ዱ  ጥፋተኞች ሲባሉ፣  የዱቤ አገልግሎት ...

Read More »

ፎቶ ጋዜጠኛ ቢንያም መንገሻ ተሰደደ

  መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በተለያዩ ፎቶግራፎቹ ከፍተኛ እውቅና ያተረፈው ጋዜጠኛ ቢንያም መንገሻ አገሩን ጥሎ ለመሰደድ የተገደደው በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አገዛዝ አገሪቱን ሙሉ በሙሉ እያወደማት መሆኑን በመገንዘብ፣ የራሱን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው። ጋዜጠኛ ቢንያም ከኢሳት ጋር ባደረገው ሰፊ ቃለምልልስ በስልጣን ላይ ያለው ሀይል ኢትዮጵያ በመኖርና ባለመኖር መካከል ከትቷታል። በመንግስት የተበላሸ ፖሊሲ የተነሳ ኢትዮጵያ በፍጥነት ወደ ምደረ በዳነት እየተቀየረች ...

Read More »

ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ ተፋጠዋል

መጋቢት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን እና በደቡብ ኮሪያ መካከል ላለፉት 60 አመታት ጸንቶ የቆው የተኩስ አቁም ስምምነት መፍረሱን የሰሜን ኮሪያ ባለስልጣናት ገልጸዋል። የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ ቃል አቀባይ እንደገለጡት በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የተኩስ አቁም ስምምነት ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ተሽሯል። ሰሜን ኮሪያ የጸጥታው ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት የጣለውን ከባድ ማእቀብ በመቃወም  የሚሳኤል እና የኒውክሊየር ሙከራዎችን በማድረግ ላይ ናት። ...

Read More »

በሁሉም ክልሎች የአማራ ተወላጆች እንዲወጡ መደረጉ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል ሲል መኢአድ ገለጸ

የካቲት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-የመኢአድ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ወንድማገኝ ደነቀ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ” በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የአማራ ተዋላጆች ወደ ክልላቸው እንዲመለሱ መታዘዙ፣ ችግሩን በእጅጉ ውስብስብ አድርጎታል። በደቡብ ክልል በጉርዳ ፈርዳ ወረዳ የተጀመረው መፈናቀል ሳይቆም፣ በባሌ፣ በአፋርና በሶማሊ ክልሎች ተመሳሳይ መመሪያዎች እየተላለፉ መሆኑን የገለጡት ምክትል ሊቀመንበሩ ፣ ተፈናቃዮች ለሞት መዳረጋቸውን ገልጸዋል አቶ ወንድማገኝ በአማራ ...

Read More »

በአፋር ክልል ነዋሪዎችን የማፈናቀሉ ዘመቻ ቀጥሎታል

የካቲት  ፴ (ሰላሳ)  ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ከክልሉ ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ከሸንኮራ አገዳ ልማት ጋር በተያያዘ ተጠናክሮ የቀጠለው የህዝብ መፈናቀል ህብረተሰቡን ለከፋ ድህነት እየዳረገው ነው። የመንግስትን ትእዛዝ ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑ ሴቶች እስከ ልጆቻቸው መታሰራቸውን የክልሉ የመኢአድ ጠጠሪ የሆኑት አቶ አሊ ሚራህ ለኢሳት ገልጸዋል ህዝቡ ጉዳዩን ገለልተኛ አካል መጥቶ እስከሚያየው ድረስ ከቦታችን አንነሳም ማለቱን  አቶ አንፍሬ ተናግረዋል በአፋር፣ በቦረና ዞን እና  ...

Read More »

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለሦስተኛ ጊዜ በሌላ ህትመት ወደ አንባብያን መመለሱን አስታወቀ

የካቲት ፴ (ሰላሳ)  ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-ተመስገን ይህን ያስታወቀው፤ <<ይህ ለአፈና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምጽ ነው>> በሚል ርዕስ  በፌስ ቡክ ገፁ ባሰፈረው ጽሁፍ ነው። ቀደም ሲል  ፍትህ ጋዜጣን፣ ከዚያም አዲስ ታይምስ መጽሔትን  በ እግድ ምክንያት ያጣው ተመስገን ለሦስጠኛ ጊዜ በሌላ ህትመት መመለሱን ባስታወቀበት በዚሁ ጽሁፍ፤<<ለዜጎች ክብር የማይሰጠው ኢህአዴግ፣ ህዝብ በሚከፍለው ግብር መልሶ የሚያፍነው ኢህአዴግ፣ የሀይማኖት ተቋማትን ወደ ‹‹አጋር ፓርቲ››ነት ...

Read More »