መጋቢት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአለም ባንክ በሂውማን ራይትስ ወች የቀረበለትን ጥያቄ መነሻ በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚከተለው ፖሊሲ የተነሳ ሰብአዊ መብቶች መጣሳቸውን ለማረጋገጥ የጠራው ስብሰባ መራዘሙን ሂውማን ራይትስ ወች ዘግቧል። ድርጅቱ በድረገጹ ላይ ባሰፈረው ዘገባ ” የአለም ባንክ ፕሮጀክት ከሰፈራ ፕሮግራም ጋር የተያያዘ ነው። ሂውማን ራይትስ ወች የአለም ባንክ ከሰፈራ ጋር በተያያዘ የሚከተለውን ፖሊሲ እንዲመረምር ጥያቄ ማቅረቡን አስታውሷል። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የግራዚያኒን ሀውልት ግንባታ በመቃወም ታሰረው የተፈቱ ዜጎች ዘራቸው እየተጠቀሰ መሰደባቸው ታወቀ
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፋሽስት ኢጣሊያ መንግስት ወኪል በመሆን በአንድ ቀን ከ30 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንን በስድስት ኪሎ አደባባይ የጨፈጨፈውን የሮዶልፎ ግራዚያኒን ሀውልት ለማቆም እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለመቃወም ትናንት እሁድ በስድስት ኪሎ የተሰባሰቡ የባለራእይ ወጣቶች ማህበር አባላት፣ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እንዲታሰሩ ተደርጓል። የጸጥታ ሀይሎች ታዋቂውን የህግ ባለሙያና ፖለቲከኛ ዶ/ር ያእቆብ ሀይለማርያምን ጨምሮ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ...
Read More »በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ፍተሻው ተጠናክሯል
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችን ስብሰባ ተከትሎ በአዋሳ፣ አዳማ እና ባህርዳር ጥብቅ ፍተሻ መካሄዱን የአይን እማኞች ገለጹ በተለይ በአዳማ እና በአዋሳ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ፍተሻ ከቅዳሜ ከሰአት ጀምሮ እስከ ዛሬ መካሄዱ ታውቋል። ወደ አዋሳ ከተማ የሚገቡ ሰዎች በጥብቅ የተፈተሹ ሲሆን፣ በከተማዋ ውስጥም በአንዳንድ ቦታዎችም ፍተሻዎች ተደርገዋል። በአዋሳ የተለያዩ ቦታዎች ድንኳኖች ተተክለው የኢህአዴግ ደጋፊዎች ሲበሉና ...
Read More »የአልጀዚራን ድረ-ገጽ በኢትዮጵያ እንዳይታይ ታገደ
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት የ አልጀዚራን እንግሊዝኛ እና ዐረብኛ ድረ-ገጾች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታዩ ማገዱን አልጀዚራ ዘገበ። ድርጊቱ፤የ ኢትዮጵያ መንግስት እንደ አዲስ እያደረበት ከመጣው ፍርሀት አኳያ ሚዲያዎችን ጸጥ ለማሰኘት እየወሰደ ያለው እርምጃ አካል ነው ብሏል- አልጀዚራ። አልጀዚራ ከጎግል የተቀበላቸው ዳታዎች እንደሚያሳዩት፤ባለፈው ሀምሌ ወር እስከ 50000 ደርሶ የነበረው እንግሊዝኛ ድረ-ገፁን የሚጎበኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር በመስከረም ወር በአስደንጋጭ ሁኔታ ...
Read More »በጄኔቭ በተመድ ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ሊካሄድ ነው
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከነገ በስቲያ ማርች 20፣ 2013 በጄኔቭ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽ/ት ቤት ፊት ለፊት ኢህአዴግ በእመነት ተቋማት ላይ እአካሄደ ያለውን ጣልቃ ገብነት በመቃወም፣ ሙስሊም ወገኖች ያቀረቡትን የእመነት ነጻነት ጥያቄ ወደ ጎን መግፋቱን በመቃወም እና የሚካሄድባቸውን አፈናና ጣልቃ ገብነት በመቃወም፣ የሽብርተኝነት ታርጋ እየለጠፈ በንጹህን ዜጎች ላይ የሚካሄደውን አፈናና የመብት ረገጣ በመቃወም፣ በአጠቃላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ...
Read More »አልሸባብ የኢትዮጵያ ጦር የያዘውን ከተማ መልሶ ያዘ
መጋቢት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኢትዮጵያ፣ ከኬንያ እና ከሶማሊያ መንግስት ወታደሮች ከፍተኛ ጥቃት ሲደርስበት የቆየው አልሸባብ፣ ትክክለኛ ምክንያቱ ባልተወቀ ሁኔታ የኢትዮጵያ ጦር ከባይደዋ አቅራቢያ የምትገኘዋን የሁድሩ ከተማን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ፣ ከተማዋን መልሶ ተቆጣጥሯል። የከተማዋ ነዋሪዎች አልሸባብ አካባቢውን ለረጅም ጊዜ ከቦ መቀመጡ የምግብ እጥረት እንዲፈጠር ማድረጉን በምሬት ሲናገሩ መደመጣቸውን ጋሮየ ኦን ላይ ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት ጦር ከተማዋን ለቆ ስለወጣበት ...
Read More »መኢአድ መንግስት በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲከሰሰ ጠየቀ
መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ ” በቋንቋ ማንነት ህዝብን መግደል፣ ማፋናቀል እና ማሰር የዘር ማጥፋት ወንጅል ነው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” ሰሞኑን በቤንሻንሂል ጉሙዝ ክልል በአማራ ተናገሪ ማህበረሰብ ላይ የተከፈተው ማፈናቀል ፣ በጅጅጋ እና በአፋርም የቀጠለ ሲሆን በመላው አገሪቱ የአማርኛ ተናጋሪ ህዝብ ቤት እንዳይኖረው ፣ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዳይሳተፍ በተለያየ ስልት ደሀ ሆኖ እና በጎዳና እንዲበተን ...
Read More »በኮብል ስቶን ሰራተኞች ጠብ የሟቾች ቁጥር 8 ደረሰ
መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በሚገኘው ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ ቦሌ ለሚ በሚባል አካባቢ ማክሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2005ዓ.ም. ኮብልስቶን በሚሰሩ ሰዎችና በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት 8 ሰዎች መሞታቸውንና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ፍኖተ ነጻነት ዘገበ፡፡ የግጭቱ መንስኤ የሞባይል መጥፋት እንደሆነ እና በዚህም ኮብልስቶን ትሰራ የነበረችን የአንዲት የአካባቢው ነዋሪ ሴት ጡት ሌላው ሰራተኛ ...
Read More »አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በአስገድዶ መድፈር ሙከራ አቤቱታ እንደቀረበበት ተዘገበ። ሠራዊት በበኩሉ <<ወሬው በሬ ወለደ >>ነው ይላል።
መጋቢት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በገዥው ፓርቲ ቀንደኛ ደጋፊነቱ የሚታወቀው አርቲስት ሠራዊት ፍቅሬ በ አስገድዶ መድፈር ሙከራ ወንጀል ክስ እንደቀረበበት አዲስ አድማስ ዘገበ። ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው የሠራዊት መልቲ ሚዲያ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ የሆነው ሠራዊት ፍቅሬ ላይ የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ክስ ለፖሊስ ያቀረበችው አንዲት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነች። ሠራዊት ፍቅሬ ግን፤ በመድፈር ሙከራ አቤቱታ እንደቀረበበት መወራቱን በተመለከተ ተጠይቆ፤ “በሬ ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን አጠንክረው አሰሙ
መጋቢት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 13 ወራት ዘወትር አርብ ተቃውአቸውን ያለመሰልቸት በጽናት እያሰሙ ያሉት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን፣ ዛሬም ተመሳሳይ ተቃውሞ ሲያሰሙ አርፍደዋል። በሻሸመኔ፣ አርሲ፣ ደሴ ፣ ስልጤ እና ሌሎችን ከተሞች በድምጽ ተቃውሞዎች ሲካሄዱ፣ በአዲስ አበባ ደግሞ ወትሮ ተቃውሞ የሚደረግበት ታላቁ አንዋር መስኪድ ጭር ብሎ ፒያሳ የሚገኘው ኑር መስጊድ በሰዎች ተጨናንቆ አርፍዷል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ ...
Read More »