.የኢሳት አማርኛ ዜና

ረገብ ብሎ የሰነበተው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ተካሄደ

መጋቢት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የጁመአን ስግደት ተከትሎ ዘወትር አርብ ሲካሄድ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሰሞኑን ረገብ ብሎ ቢቆይም  ፣ በዛሬው እለት በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአዲስ አበባ ቤኒን መስጊድ ተካሂዷል። ሙስሊሞቹ እጅግ ለእጅ በመያያዝ አንድ መሆናቸውን አሳይተዋል። የአለፉትን 1 አመት ከ3 ወራት በከፍተኛ ጫና እና እንግልት ያሳለፉት ሙስሊሞች ” የታሰሩ መሪዎች ሳይፈቱና ጥያቄዎቻችን ሳይመለሱ” ትግላችንን አናቆምም ...

Read More »

የአዲስ አበባ መስተዳድር ለ40 በ60 ቤቶች በድጋሜ ምዝገባ ሊጀምር ነው፤ የምርጫ ቅስቀሳው አካል ነው ተብሎአል

መጋቢት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር በሚያዝያ ወር ለሚያካሂደው የአዲስአበባና የአካባቢ ምርጫ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚረዳውን የ40 በ60 ቤቶችና የኮንዶምኒየም ቤቶች ዳግም ምዝገባ ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተጠቆመ፡፡ በተወሳሰበ የመልካም አስተዳደር ችግር፣ በሙስናና ብልሹ አሰራር በሕዝብ ዘንድ ክፉኛ የሚወገዘው የኩማ አስተዳደር በተለይ የአዲስአበባ ከተማ ሕዝብን ቁጣና ኩርፊያ ለማለዘብ ይረዳኛል በሚል ያሰበውን ከቤቶች ልማት ጋር የተገናኘ ቅስቀሳና ...

Read More »

የአቶ መለስ ፋውንዴሽን ነገ ይፋ ይሆናል

መጋቢት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በነገው ዕለት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ የሚካሄደው የመለስ ፋውንዴሽን መስራች ጉባዔ ላይ 13 አባላት ያሉት የቦርድ አባላት እንደሚመረጡና ፋውንዴሽኑ የመለስ ሁለት ልቦለድ መጽሐፍትን ጨምሮ ሌሎችንም ፖለቲካዊ ጹሑፎች እንደሚያሳትም ተጠቆመ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በሞት ከተለዩ ከሰባት ወራት በላይ የተቆጠረ ሲሆን ተተኪው አመራር የእሳቸውን ሌጋሲ ሳይበረዝ ሳይከለስ ለማስቀጠል በገባው ቃል ...

Read More »

የመንግስት ባለስልጣናት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ የተፈናቀሉ አርሶአደሮችን እያነጋገሩ ነው

መጋቢት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአማራ ክልል የተውጣጡ ባለስልጣናት በፍኖተ ሰላም ከተማ ሰፍረው የሚገኙትን የቤንሻንጉል ጉሙዝ አማርኛ ተናጋሪ ተፈናቃዮችን በማነጋገር ላይ መሆናቸውን በሰፍራው የሚገኙ ተፈናቃዮች ገለጡ። ባለስልጣናቱ ተፈናቃዮቹ የምርጫ ካርዶችን፣ ግብር የከፈሉባቸውን ደረሰኞች፣ የክልሉን መታወቂያ እንዲሁም ሌሎች አባሪ ሰነዶችን አቅርበው እንዲያስመዘግቡ አድርገዋል። ይሁን እንጅ ተፈናቃዮች ወደ መጡበት አካባቢ ስለመመለስ እና አለመመለሳቸው ወይም ሀብትና ንብረታቸው ተመልሶላቸው ወይም ካሳ ...

Read More »

በአዲስ አበባ የሚኖሩ ነዋሪዎች ቤቶቻችን ሆን ተብሎ በመንግስት ሰዎች እየተቃጠሉብን ነው አሉ

መጋቢት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በትናንትናው እለት ብቻ ሁለት ቦታዎች ላይ በተመሳሳይ ሰአት ቃጠሎ የደረሰ ሲሆን፣ ድርጊቱ ያበሳጫቸው ወጣቶች ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር መጋጨታቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። የመጀመሪያው የእሳት አደጋ የደረሰው በአባኮራን ሰፈር ፋሲል ሆቴል አጠገብ ከቀኑ 5፡10 ሲሆን፣ ቃጠሎውም እሰከ 7፡30 ድረስ መቆየቱ ታውቋል። አንድ ሰው ጭንቃላቱ አካባቢ ቃጠሎ ሲደርስበት ሌላ አንዲት ወጣት ደግሞ ...

Read More »

ኢህአዴግ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ያሉ ሰራተኞች ድርጅቱን እንዲመርጡ ቃል የሚያስገባ ቅጽ ለአባሎቹ ሰጠ

መጋቢት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚሁ የቃል ኪዳን ቅጽ ላይ ” በከተማዎች የሚካሄደውን የወረዳ፣ የክፍለከተማና የከተማ ምክር ቤት አባላት ምርጫ ነጻ ፣ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና በህዝብ ተአማኒነት ያለው እንዲሆን በማድረግ ድርጅታችን ኢህአዴግ አሸናፊ እን ዲሆን የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረግ፣ የታላቁ መሪያችንን ጓድ መለስ ዜናዊ ሌጋሲ ለማስቀጠልና ራእዩን ከግብ ለማድረስ የገባሁትን ቃል ተግባራዊ ማድረግ” የሚል ሀረግ ተጽፎ የሚገኝ ሲሆን፣ ” ...

Read More »

በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሰውን መፈናቀል ኢትዮጵያውያን ማውገዛቸውን ቀጥለዋል

መጋቢት ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከ5 እስከ 10 ሺ የሚደርሱ የአማራ ተወላጆች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ አካባቢ ተፈናቅለው ወደ መጡበት የትውልድ ቀያቸው እንዲመለሱ መደረጉ ኢትዮጵያውያንን ከጫፍ እስከ ጫፍ ማነጋገሩን ቀጥሏል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን በመወከል በሩዋንዳ በተፈጸመው የዘር ማጥፋት ወንጀል የፍርድ ሂደት በአቃቢ ህግነት የተሳተፉት    ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በጉራፈርዳ ወረዳ የተፈጸመው አማርኛ ተናጋሪዎችን የማፈናቀል ድርጊት በዘር ማጥራት ወንጀል በማንኛውም ጊዜ ...

Read More »

አቶ ስብሐት ነጋ ኤርትራውያንንና ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ስብሰባ ጠሩ

መጋቢት ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር የሚገኘውና በቀድሞ የህወሃት መስራችና አመራር አባል አቶ ስብሃት ነጋ የሚመራው የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት የፊታችን ቅዳሜ የኢትዮጵያና ኤርትራ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር ሕዝባዊ ስብሰባ በአዲስአበባ ጠራ፡፡ በትጥቅ ትግሉ ወቅት እና ወደመንግስት ስልጣን ከመጡም በኃላ በመጀመሪያዎቹ 10 ዓመታት ሃይለኛ ፍቅር ውስጥ የነበሩት ሻዕቢያና ...

Read More »

የሳውዲ አረቢያ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር አንድ ባለስልጣን በኢትዮጵያ ጉዳይ የሰጡትን መግለጫ አስተባበለ

መጋቢት ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሳውዲ አረብያ ም/ል የመከላከያ ሚ/ር በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባውን የሀይል ማመንጫ አስመልክቶ  የሰጡት ምገለቻ የሀገሪቱን መንግስት አቋም እንደማይገልፅ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጹን የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ፋና ብሮድካስቲን ዘግቧል። የኢትዮጵያና የሳዑዲ አረቢያ የሁለትዮሽ ግኑኝነት መከባበርንና የጋራ ተጠቃሚነትን እንዲሁም አንዱ በሌላው ውስጣዊ ጉዳይ ላይ ጣልቃ አለመግባትን መሰረት ያደረገ መሆኑን የገለጠው ድርጅቱ፣ በቅርቡ የሳውዲ ...

Read More »

በአማራ ተወላጆች ላይ የተፈጸመው የዘር ማጥራት ወንጀል ሊያስጠይቅ እንደሚችል አንድ ታዋቂ ምሁር ገለጹ

መጋቢት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም  ኢሳት ዜና:-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካኝነት በሩዋንዳ የተካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በአቃቢህግነት በመምራት  የሚታወቁት የህግ ባለሙያው ዶ/ር ያዕቆብ ሀይለማርያም ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደገለጡት ከዚህ ቀደም በደቡብ ክልል በጉራፈርዳ ወረዳ፣ አሁን ደግሞ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በአማራ ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለው ወንጀል በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ የሚችል ዘር ማጥራት ወንጀል መሆኑን ገልጸዋል። ምሁሩ እንዳሉት ድርጊቱ የዘር ማጥፋት ...

Read More »