.የኢሳት አማርኛ ዜና

17 ሰዎችን የገደለው የፌደራል ፖሊስ ማንነት በውል አልታወቀም

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እሁድ ግንቦት4፣ 2005 ዓም ከምሽቱ 2 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ፣ የሁለት አመት ህጻንን ጨምሮ 17 ሰዎችን  በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 11 ወይም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ማንነት እና የገደለበት ምክንያት በውል አለመታወቁን ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች እየተሰነዘሩ ነው። ወታደሩ ድርጊቱን የፈጸመው አንድ ያፈቀራት ወጣት ከእርሱ ጋር ለመቀጠል ...

Read More »

በጭልጋ ወረዳ በተነሳ ተቃውሞ 60 ሰዎች ታሰሩ በርካቶችም በረሀ ገብተዋል

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከጎንደር ከተማ 55 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በጭልጋ ወረዳ  አለምጸሀይ ቀበሌ አመክሊን እየተባለ በሚጠራ ጎጥ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደሮች “ ለ አገር ውስጥ ባለሀብት ሊሰጥ ነው”ከተባለው ይዞታቸው እንዲነሱ  የቀረበላቸውን ጥያቄ በመቃወማቸው በታጠቁ  የክልል እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት መንደራቸው ተከብቦ ተኩስ እንደተከፈተባቸው የ ኢሳት ወኪል ከስፍራው ዘግቧል። ይዞታችንን አንለቅም ያሉት ሁሉ  ሚያዚያ 29 ቀን ...

Read More »

ሉሲ ከአንድ ዓመት በላይ መቆየት እንዳልነበረባት ሳይንቲስቶች ተናገሩ

ግንቦት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “ሉሲ መውጣት የለባትም”የሚል አቋም ይዘው የነበሩ ወገኖች፤ በአቶ መለስ ደብዳቤ ተረትተው ሉሲ እንድትወጣ መደረጉም ተጠቁሟል። ላለፉት አምስት ዓመታት አሜሪካ ከርማ የተመለሰችው ሉሲ ከአንድ ዓመት በላይ መቆየት እንዳልነበረባት ኢትዮጵያዊው የቅሬተ አካል ሳይንቲስት ዶ/ር ዘረሰናይ ዓለምሰገድ  መናገራቸውን ሪፖርተር ዘገበ።   ዶክተር ዘረሰናይ ይህን ያሉት፤የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ሚያዝያ 30 ቀን 2005 ዓ.ም. በብሔራዊ ሙዚየም ...

Read More »

መንግስት በዜጎች መፈናቀል ከተጠያቂነት አያመልጥም ሲል መድረክ አስታወቀ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ባወጠው መግለጫ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ለደረሱትና እየደረሱ ላሉት የዜጎች በህገወጥ መንገድ መፈናቀል ተጠያቂነቱን በበታች የክልል፣ የዞን እና የወረዳ አስተዳደር አካላት ላይ በማላከክ መንግስትን ከተጠያቂነት ለማዳን መሞከር ” ተጨፈኑ ላታላችሁ” አይነት እርምጃ ነው ብሎአል። በዜጎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰ በሁዋላ መንግስትን ከሃላፊነት ለማሸሽ የበታች አካላትን የመስዋት በግ በማድረግ የተኬደበት አቋራጭ ...

Read More »

በቦና ወረዳ ከ40 በላይ ሰዎች ታፍሰው ተወሰዱ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ጎንደር ዞን በቦና ከተማ ሚያዚያ 29 ቀን ፣ 2005 የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከ40 በላይ ሰዎች በመከላከያ ሰራዊት አባላት ታፍሰው የተወሰዱ ሲሆን ከ8 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ በደረሰባቸው ከፍተኛ ደብደባ በጽኑ ቆስለዋል። ግጭቱ የተፈጠረው በቅጽል ስማቸው አቶ በደሌ የተባሉ ባለሀብት ማህበረሰቡ የሚጠቀምበትን የምንጭ ውሀ በማጠር ለራሳቸው የከብት ማድለብ ስራ ሊጠቀሙበት ማሰባቸውን ህብረተሰቡ በመቃወሙ ነው። ህዝቡ ...

Read More »

የገቢዎችና የጉምሩክ ባለስልጣን ዋና እና ምክትል ዳይሬክተሮችን ጨምሮ 16 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን መንግስታዊ መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ቀደም ሰል የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩትና ሚኒስቴሩ በበለስልጣን መስሪያ ቤት ሆኖ ሲዋቀር ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ መላኩ ፋንታ፣ ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ ወልደዋህድ ገብረጊዮርጊስ እና ሌሎች ከ 10 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስና ተጠርጥረው እንደሆነ መንግስት ገልጿል። የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዜና አቅራቢ አጠቃላይ የታሰሩት ሰዎች 12 መሆናቸውን ሲገልጽ፤ዝርዝር ዜናውን ያነበበው ሪፖርተር ታሳሪዎቹ 16 መሆናቸውን ...

Read More »

በአውሮፓ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ ህብረት ጽህፈት ቤት ፊትለፊት የተቃውሞ ሰልፍ ሊያደርጉ ነው

ግንቦት ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያውያን ማህበር በኔዘርላንድስ ከቤልጂየም የኢትዮጵያውያን ማህበር ጋር በመተባበር የፊታችን ረቡእ ፣ እኤአ ሜይ 15፣ 2013 በብራሰልስ በሚገኘው በአውሮፓ ህብረት ፊት ለፊት የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርግ ለኢሳት በላከው ደብዳቤ አስታውቋል።   ሰልፉ በአማራ ተወላጆች ላይ በተደጋገሚ እየተፈጸመ ያለውን የማፈናቀል ዘመቻ ፣ በልማት ስም የአፋር፣ የጋምቤላ እና የሌውንም ህዝብ ህልውና ለማጥፋት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማውገዝ፣ በየእስር ቤቱ ውስጥ ...

Read More »

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሙሀመድ ኡመር አድገናል በማለት የምናቀርበው ሪፖርት ሁሉ ውሸት ነው አሉ

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፕሬዚዳንቱ የካቢኔ አመራሮችን እና የሶህዴፓ ፓርቲ አባሎችን በመሰብሰብ እንደተናገሩት ክልሉ እንደ ለማ እንደ አደገ ተደርጎ ለመንግስት የሚቀርበው ሪፖርት ሁሉ ግምገማ ለማለፍ ተብሎ የሚቀርብ በውሸት የተሞላ ነው ብለዋል። ፕሬዚዳንቱ በስሜት ውስጥ ሆነው ባደረጉት ንግግር ”  እኛ እንዳደግን ፣ ጥሩ ደረጃ ላይ እንደደረስን ተደርጎ በየጊዜው የሚቀርበው ሪፖርት ፍጹም ትክክል ያልሆነ ውሸት ነው። አሁን በእጄ የያዝኩት ...

Read More »

የኦነግ ወታደሮች አንድ የጸጥታ ሹም ገድለው 7 ፖሊሶችን አቆሰሉ

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቦረና ዞን ፣ የሚኦ ወረዳ  የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት  አቶ ጁኬ የአካባቢውን ፖሊሶች በማሰልፍ የኦነግን ታጣቂዎች ለማደን  ሚያዚያ 29፣ 2005 ዓም ቢንቀሳቀሱም የኦነግ ወታደሮች   ጨሶ እና ሜጢ በሚባል ቦታ ላይ አድፍጠው በመጠበቅ በወሰዱት እርምጃ ፣ የጸጥታ ሹሙን አቶ ጁኬን ገድለው፣ 7 ፖሊሶች ደግሞ አቁስለዋል። 6ቱ ፖሊሶች   በያቤሎ ሆስፒታል ተኝተው በመታከም ላይ ሲሆኑ አንዱ ...

Read More »

በ ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ደማቅ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ግንቦት ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያውያኑ ሰልፉን ያደረጉት ገዥው የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ እየፈጸማቸው ያሉትን ኢፍትሀዊ እና ህገ ወጥ ድርጊቶች በመቃወም ነው። በርካታ  ኢትዮጵያውያን በተሳተፉበት በዚህ ሰልፍ፤ ገዥው ፓርቲ ዜጎችን በዘር እየመረጠ ከመኖሪያ ይዞታቸው ከማፈናቀል ተግባሩ እንዲገታ፣ አላግባብ የታሰሩት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ፣ ጋዜጠኞች፣የሙስሊም መሪዎችና ሌሎች የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ! መንግስት በሀይማኖት ተቋማት ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም፣በዋልድባ ...

Read More »