ግንቦት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰማያዊ ፓርቲ ትናንት በተሳካ ሁኔታ ያካሄደውን ሰልፍ በተመለከተ የተለያዩ ወገኖች ለኢሳት እየደወሉ ደስታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። ፓርቲው ተቃውሞውን ከማዘጋጀት ጀምሮ አጠር እና ምጥን ያለ ዝግጅት በማቅረቡ ደስታቸውን የገለጸት አንድ አስተያየት ሰጪ፣ ተቃውሞው ብልጭታ እንድናይ አድርጎናል ብሎአል አንድ ሌላ ሴት ደግሞ በትናንትናው ሰልፍ “ትንሽ ትንሽ” ዲሞክራሲ እየመጣ ይመስለኛል ብለዋል ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ መንግስት የሰጠውን ማስፈራሪያ አመራሮች እና የህግ ባለሙያዎች ውድቅ አደረጉት
ግንቦት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እሁድ ግንቦት25 ከፍተኛ ህዝብ የተገኘበትን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ የኢህአዴግ የጽህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን ለሬዲዮ ፋና ሲናገሩ ” የሃይማኖት አክራሪነትን አጀንዳው አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ ጸረ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴው ዛሬ በጠራው ሰልፍ ተጋልጧል ” ብለዋል። ፓርቲው ያዘጋጀውን ሰላማዊ ሰልፍ ላልተፈለገ አላማ አውሎታል ያሉት አቶ ሬድዋን ፣ በሰልፉ በአብዛኛው ...
Read More »በሰስዊዘርላድ-ጄኔቭ ኢህአዴግ የጠራው የቦንድ ሽያጭ ስብሰባ “ከ ዓባይ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይገደብ!” የሚል መፈክር ባነገቡ ኢትዮጵያውያን ብርቱ ተቃውሞ ከሸፈ
ግንቦት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢህዴግ -በጄኔቭ ለ ዓባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ ለማካሄድ ካለፉት ሁለት ወራት ወዲህ በምስጢር ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ ከቆየ በሁዋላ በቅርቡ ለደጋፊዎቹ ብቻ የዝግጅቱን ዕለት፣ቦታ እና ሰዓት አስመልክቶ ጥሪ ያቀርባል። ይሁንና ኢህአዴግ መቼ እና የት ዝግጅቱን ሊያደርግ እንዳሰበ የውስጥ መረጃ የደረሳቸው በጄኔቭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጎን ለጎን የተቃውሞ ዝግጅት ሲያስተባብሩ ይከርማሉ። ከተቃውሞ ሰልፉ አስተባባሪዎች አንዱ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ መንግስት ሰበቦችን እየፈለገ ነው
ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማደናቀፍ በተለያዩ ክፍለከተሞች ስብሰባ መጥራቱ ታውቋል። የተለያዩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት መስተዳድሩ በሰልፉ ላይ ብዙ ህዝብ እንዳይገኝ ለማድረግ ከቤት ጋር የተያያዙ አጀንዳዎችን በማንሳት ህዝቡ ወደ ተቃውሞ ሰልፉ እንዳይሄድ ለማድረግ እየጣረ ነው። “ኢህአዴግ ድህነትን ለፖለቲካ ድጋፍ ማስገኛ እየተጠቀመበት መሆኑን፣ በከተማው ያሉ የቤት እና ...
Read More »ኢህአዴግ ልሳኖቼን የሚያነብ በመጥፋቱ ለኪሳራ ተዳርጌአለሁ አለ
ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-” የኢህአዴግ አባላትን ፖለቲካዊና ርእዮተ-ዓለማዊ ብቃት ለማሳደግ ለአርሶ አደሩና ዝቅተኛ የትምህርት ዝግጅት ላላቸው አባላት አብዮታዊ ዲሞክራሲ ጋዜጣንና ከፍ ያለ የትምህርት ዝግጅት ላላቸው ደግሞ አዲስ ራእይ መጽሄትን እና አብዮታዊ ዲሞክራሲ መጽሄትን የይዘት እና የስርጭት ለውጥ በማድረግ ” ለማሰራጨት ቢሞከርም ፣ አመራሩም አባላቱም ለማንበብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ለኪሳራ ተዳርገናል በማለት ድርጅቱ አስታውቋል። ይህ የተገለጸው ብአዴን ...
Read More »በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የፖሊሶችና እና የደህንነት ሀይሎች እጅ አለበት ተባለ
ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ዞን በከምሴ ከተማ ባለፈው ሳምንት በተጠራ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ወደ የመን እና እና ሳውድ ኣረቢያ በህገ ወጥ ዝውውር ከሚጓዙ ወጣቶች ጀርባ ደህንነቶችና የፖሊስ ሃይሎች መኖራቸው ተመልክቷል። የዞኑ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት እንድሪያስ አሊ ሸቱ ለኢሳት እንደተናገሩት የህገወጥ ዝውውሩ ችግር አገራዊ ይዘት ያለው ቢሆንም በህገወጥ ዝውውሩ ላይ እየተሳተፉ በሚገኙ የጸጥታ ሀይሎች ላይ ...
Read More »አትሌት ቀነኒሳ በ10 ሺ ሜትር አሸናፊ ሆነ
ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አሜሪካ ውስጥ በኢዩጂን በተደረገው የዳይመንድ ሊግ አትሌቲክስ ውድድር አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በ10ሺህ ሜትር ውድድር በማሸነፍ ወደ ቀድሞ ክብሩ መመለሱ ታወቀ። በ10 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት፣ እንዲሁም የኦሎምፒክ ሶስት የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ የሆነው ቀነኒሳ በደረሰበት ጉዳት ለረጅም ጊዜ ከውድድር ርቆ መቆየቱ ይታወሳል። ምንም እንኳን ቀነኒሳ ከጉዳቱ በደንብ ሳያገግም ባለፈው የለንደን ኦሎምፒክ ...
Read More »184 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወድቆ ያገኘው ኢትዮጵያዊ ገንዘቡን መለሰ
ግንቦት ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የፅዳት ሰራተኛ የሆነው ወጣት ብርሃኑ ጀምበሬ አይሮፕላን ሲያፀዳ በካኪ ወረቀት ተጠቅልሎ ወድቆ ያገኘውን 184 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ለባለቤቱ እንዲመለስ ማድረጉ ታወቋል። ወጣት ብርሃኑ በወቅቱ የተሰማውን ስሜት ሲገልፅ “በመጀመሪያ ገንዘቡን ሳገኝ ይህን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ አይቼ ስለማላውቅ በጣም ደነገጥኩ። በዚህም የተነሳ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ተጋብቼ ጥቂት ደቂቃዎች ...
Read More »የተለያዩ ክልል ነዋሪዎች ኑሮ እንዳማረራቸው ገልጹ
ግንቦት ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ፣ በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልሎች በመዘዋወር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማነጋገር እንደዘገቡት ዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል በ ከፍተኛ ድህነት ውስጥ እየተሰቃየ እንደሚገኝ አመለክተዋል። በጎዲዮ ዞን የሚገኙ አንድ በሽመና ስራ ላይ የሚሰሩ አዛውንት ” ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ እንደሆነባቸው ተናግረው፣ ጊዜው አስቸጋሪ መሆኑን” ገልጸዋል። ( ጌዲዮ 00070) ባለቤታቸውም እንዲሁ ” እሱ የፈጠረን ...
Read More »ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ድጋፋቸውን እየገለፁ ነው
ግንቦት ፳፫ (ሀያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በመጪው እሁድ በሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን እንደሚቆም አስታውቋል። <<ሰማያዊ ፓርቲ በሰልፉ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች የኛም ጥያቄዎች ናቸው>> ያለው አንድነት ፓርቲ፤ አባላቱና ደጋፊዎቹ ወደ ሰልፉ በመውጣት ድምጻቸውን ያሰሙ ዘንድ መልእክት አስተላልፏል። የአንድነት ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ፤ ፓርቲያቸው -የሰማያዊ ፓርቲን ጥሪ ከልብ የሚደግፍ ...
Read More »