.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ውይይት አደረገ

ሰኔ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአፍሪካ ጉዳዮች ሃላፊ ዶናልድ ያማማቶ፣ በአፍሪካ የዩሴ አይ ዲ ዳይሬክተር ኤሪል ጋስት፣ በአፍሪካ  ጉዳዮች ተመራማሪ  ዶ/ር ፒተር ፓሀም፣ የግንቦት7 ሊቀመንበር ዶ.ር ብርሀኑ ነጋ ፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር  አቶ ኦባንግ ሜቶና የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአሜሪካ ተወካይ  ሚስተር አዶቲ አኪዌ እና ሌሎችም ታዋቂ ምሁራን ፖለቲከኞች የተሳተፉበት ውይይት የተካሄደ ሲሆን፣ አምባሳደር ያማማቶ እና ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አሳትፎ በ3 ወራት ውስጥ ህዝባዊ ንቅናቄ ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

ሰኔ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆነው ወጣት ዳንኤል ተፈራ ለኢሳት እንደገለጸው ፓርቲው  በሚቀጥሉት ሶስት ወራት እና ከዛም በሁዋላ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተሸራረፉ ያሉ ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማድረግ ይሰራል። የጸረ ሽብር ህጉ እንዲሰረዝ፣ የህዝብ ማፈናቀል እንዲቆም፣ የኑሮ ውድነቱ እና የስራ አጥነት ችግር እንዲቀረፍ፣ የንግዱ ማህበረሰብ ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እንዲነግድ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ  እንደሚጠይቅ ...

Read More »

መሬታቸው የተወሰደባቸው ከ50-60 የሚጠጉ የመተማ አርሶአደሮች ጫካ መግባታቸውን ሲያስታውቁ ከ30 ያላነሱት ደግሞ ታስረዋል

ሰኔ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በመተማ ዮሐንስ እና በኮኪት ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች መሬታችን አድሎአዊ በሆነ መልኩ ለባለሀብቶች እየተሰጠብን ነው” በማለት ተቃውሞአቸውን ማሰማታቸውን ተከትሎ ጸረ ሽምቅ እና ልዩ ሀይል የሚባሉ የመንግስት ታጣቂዎች ከ30 ያላነሱትን የአካባቢውን ሰዎች ሲያስሩ፣ በታጣቂዎች ከሚፈለጉት መካከል ደግሞ ከ50- 60 የሚሆኑት አርሶደሮች ጫካ መግባታቸውን አስታውቀዋል። ባለፉት ሳምንታት  አቤቱታቸውን አዲስ አበባ ተገኝተው ለም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ...

Read More »

ኤጀንሲው በአማራ ህዝብ ቁጥር መቀነስ ዙሪያ ፍተሻ ማድረጉን አስታወቀ

ሰኔ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የሕዝብ ቆጠራ ኮምሽን በ1999/2000 ዓ.ም የሶስተኛው የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት ይፋ በተደረገበት ወቅት በተለይ የአማራ ክልል ሕዝብ ብዛት ከሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ ከትንበያው ዝቅ ብሎ ተገኝቷል በሚል በቀድሞ የፓርላማ አባላት በቀረበው ቅሬታ ላይ ኮምሽኑ ፍተሻዎችን ማድረጉንና ምንም ዓይነት ስህተት አለማግኘቱን አስታውቋል፡፡ የቤቶች ቆጠራ ኮምሽን ዛሬ ለፓርላማው ያቀረበው ሪፖርት ...

Read More »

የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያውያን ለመብታቸው መከበር የሚያሰሙትን ድምጽ ይሰማል ሲሉ ወ/ሮ አና ጎሜዝ ተናገሩ

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ አባል የሆኑት እና በምርጫ 97  ወቅት የህብረቱ የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ  የነበሩት ወ/ሮ አና ማርያ ጎሜዝ ይህን የተናገሩት ኢትዮጵያውያን ዛሬ በአውሮፓ ህብረት መቀመጫ ፊትለፊት  ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ  ነው ። ወ/ሮ አና ጎሜዝ የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያውንን ጩሀት ሰምቶ መልስ እንደሚሰጥ  ተናግረው፣ በግላቸው ከኢትዮጵያውያን ጎን ቆመው  ለውጥ እስከሚመጣ  እንደሚታገሉ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ከፍተኛውን ኢንቨስተር መንግስት ነው ሲል የአለም ባንክ አስታወቀ

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ባንኩ  በገንዘብና የ ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አነሳሽነት ያጠናቀረውን ሪፖርት  በሸራተን አዲስ ይፋ ሲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት በዓለም በከፍተኛ መጠን ኢንቨስት ያደርጋሉ ከሚባሉ ሦስት መንግሥታት መካከል  እንደሆነ ፤በ አንፃሩበግል ዘርፉ የሚካሄደው   ኢንቨስትመንት የ ኣለማችን ስስድስተኛው ዝቅተኛ  ኢንቨስትመንት መሆኑን አመልክቷል፡፡ እንደ ሪፖርተረ  ዘገባ፤ የባንኩ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጉዋንግ ቼንግና የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ...

Read More »

በአማራ ክልል ከ493 ሺ በላይ ሄክታር መሬት ደን እየወደመነ ተባለ፣ ክልሉ ግን አስተባብሎአል።

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በደብረ ማርቆስ የየራባ ደን ፤በአዊ ዞን እንጅባራ የገንብሃ ጫካ ፤በደብረ ታቦር እና በኮምቦልቻም አመታትን ያስቆጠሩ ደኖች እየጠመነጠሩ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል፡፡ ከፍተኛ የደን ቆረጣ በሚካሄድባቸው በአዊ እና በደብረማርቆስ አካባቢዎች ነዋሪዎች ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው። ብዛታቸው ያልታወቀ ጥቁር ዝንጀሮ፣ ጅብ፣ ከርከሮ፣ ድፈርሳ፣ ትልልቅ ጥንቸሎች፣ አረንጓዴ ልባስና ቀይ መንቁር ያላቸው ወፎች፣ የሐበሻ ነብር ...

Read More »

በአዲስ አበባ ከተማ የጉለሌና አራዳ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ የውሃ እጥረት እንዳጋጠማቸው ገለጹ።

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የአዲሱ ገበያና የቀጨኔ አካባቢ ነዋሪዎች  የውሃ እጥረቱ ለኢኮኖሚና ለጤና ቀውስ እንደዳረጋቸው ተናግረዋል። በዚህ ዓመት  በተደጋጋሚ ከአንድ ወር በላይ የቆየ የውሃ እጥረት እንዳጋጠማቸው ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። መንግስት ” የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የቦታ አቀማመጥ ለውሃ ሥርጭቱ አመቺ አለመሆን፣ በእነዚህ ክፍለ ከተሞች ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር መጨመር ፣ በተለያዩ የልማት ሥራዎች ምክንያት የውሃ መስመሮች መሰበርና ...

Read More »

ማእከላዊ አፍሪካን ሪፑብሊክን በማሸነፍ የኢትዮጵያን ታሪክ እንደምንቀይረው አልጠራጠርም ሲል ምንያህል ተሾመ ተናገረ

ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ምን ያህል ለኢሳት እንደገለጸው በተፈጠረው ነገር በእጅጉ አዝኗል። እኔ በአገሬ ላይ አውቄ እንዲህ አይነት ነገር አልሰራም ያለው ምንያህል፣ ቢጫ ካርድ ከተሰጠው ከ10 ወራት በሁዋላ ብዙ ጨዋታዎችን መጫወቱ ቢጫ ማግኘቱን እንዲዘነጋ እንዳደረገው  ገልጿል። የሚመለከታቸው የስፖርቱ ሀላፊዎች “ሁለት ቢጫ ካርዶችን ማየትክን  አልነገሩህም ነበር? ተብሎ ለተጠየቀው ደግሞ  አንድ ቢጫ ብቻ እንዳለኝና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ...

Read More »

ግብጽና ኢትዮጵያ የቃላት ጦርነቱን ለመቀነስ ተስማሙ

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሁለቱ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሰጡት መግለጫ አገራቱ የቃላት ጦርነቱን አቀዝቅዘው የኤክስፐርቶች ቡድን በቅርቡ በሰጠው አስተያየት ላይ ተጨማሪ ውይይት እንዲያደርጉ ተስማምተዋል። የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ በአባይ ላይ አብረን መዋኘት ካልቻልን ተያይዘን እንሰምጣለን ብለዋል። በውይይቱ መሀልም ሱዳንን ለማካተት ተስማምተዋል። በውይይቱ አንድ ስምምነት ላይ እስከሚደረስ ድረስ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ለማቆም  መስማማት ...

Read More »