ግብጽና ኢትዮጵያ የቃላት ጦርነቱን ለመቀነስ ተስማሙ

ሰኔ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የሁለቱ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሰጡት መግለጫ አገራቱ የቃላት ጦርነቱን አቀዝቅዘው የኤክስፐርቶች ቡድን በቅርቡ በሰጠው አስተያየት ላይ ተጨማሪ ውይይት እንዲያደርጉ ተስማምተዋል።

የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም፣ በአባይ ላይ አብረን መዋኘት ካልቻልን ተያይዘን እንሰምጣለን ብለዋል።

በውይይቱ መሀልም ሱዳንን ለማካተት ተስማምተዋል። በውይይቱ አንድ ስምምነት ላይ እስከሚደረስ ድረስ ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ ለማቆም  መስማማት እና አለመስማማቷ አልተገለጸም።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለቱ አገራት ችግራቸውን በስምምነት እንዲፈቱ መጠየቁ ይታወሳል።