ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻነት››በሚል መሪ ቃል በጀመረው ህዝባዊ ንቅናቄ በመንግስት ሀይሎች እንቅፋት እየተፈጠረበት መሆኑን አስታውቋል። ፓርቲው የመጀመሪያውን የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2005 ዓ.ም ለማድረግ በህገ መንግስቱ መሰረት ለሚመለከተው አካል የማሳወቂያ ደብዳቤ በማስገባት የቅስቀሳ ስራውን በጎንደርና አካባቢው መስራት ቢጀምርም፤ መንግስት በ አባላቱ ላይ ህገወጥ እስር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በግብጽ የፕሬዚዳንት ሙርሲ እጣ ፈንታ አልታወቀም
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብጽ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ ፕሬዚዳንቱ በተቃዋሚዎች የቀረበውን ጥያቄ በ48 ሰአታት ውስጥ እንዲመልሱ ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የግብጽ ቀጣይ እጣ ፋንታ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አልታወቀም። ፕሬዚዳንት ሙርሲ ህገ መንግስቱን ለማስከበር የህይወት መስዋትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ሲገልጹ፣ የመከላከያ ባላስልጣናት ደግሞ የራሳቸውን መፍትሄ ሀሳብ አቅርበዋል። የመከላከያ አዛዦች ፍላጎት በውል ባልታወቀበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንቱ ...
Read More »የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አዋጅ ጸደቀ
ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሚኒስትር ማእረግ ደረጃ እንዲቋቋም የታሰበው የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት መ/ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ከአንድ ሳምንት ዕይታ በኋላ ዛሬ ለፓርላማው ቀርቦ እምብዛም ውይይት ሳይደረግበት መጽደቁ ታውቋል፡፡ የኣመቱ ሥራውን ሰኔ 30 የሚያጠናቅቀውና ለዕረፍት የሚዘጋው ኢህአዴግ መራሹ ፓርላማ በተጣደፈ አሰራር ያጸደቀው በዚሁ አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው መ/ቤት መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተንና የማቅረብ እና የደህንነት አገልግሎት የመስጠት እንዲሁም ...
Read More »ሩሲያ ተዋጊ ጄቶችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ እየተደራደረች ነው
ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አር አይ ኤ የተባለው የዜና ማሰራጫ የሮስቦሮን ኤክስፖርት አርምስ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑትን አሌክሳንደር ሚካሄቨን ጠቅሶ እንደዘገበው ሩሲያ 18 ኤስ ዩ 30 ከ የተባሉ የጦር ጄቶችን ለኢትዮጵያ ለመሸጥ በድርድር ላይ ናት። ጄቶችን ለመሸጥ ከኢትዮጵያ ጋር እየተነገጋገርን ነው። የጄቶችን ቴክኒካዊና ታክቲካዊ ብቃት ከፍ ለማድረግ እንዲሁም ከአየር ወደ ምድር የሚወነጨፉ ሚሳኤሎችን እንዲሸከሙ ለማድረግ ሀሳብ ...
Read More »መንግስት በእስራኤል አገር የሰለጠኑ የደህንነት ሀይሎችን አሰማራ
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የብሄራዊ ጸጥታና ደህንነት መስሪያ ቤት በእስራኤል አገር በታል አራድ ኔጊቭ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሰለጠናቸው 987 የደህንነት ሰራተኞች በመላ አገሪቱ በሚገኙ 572 ታላላቅ መስጊዶች እና በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ማሰማራቱን ከደህንነት መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል ፡፡ ከሰልጣኞች መካከል 11 ዱ ብቻ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አረብኛ አቀላጥፈው የሚናገሩ ፣ ቁራንን በስርዓት ...
Read More »በቤተመንግስት ዙሪያ የተገደለው ሰው ማንነት ታወቀ
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ዜናውን ይፋ ካደረገው በሁዋላ የሟቹ ጓደኛ የሆነ አንድ ግለሰብ መረጃውን ለሟቹ ባለቤት በሚስጢር ማስተላለፉንና ባለቤቱ እና ልጆቹ በጋራ ወደ ሚኒሊክ ሆስፒታል በመሄድ አስከሬኑን መለየታቸው ታውቋል። ባለቤቱ አስከሬኑን ለመለየት የቻለችው በሰውነቱ ላይ ባለው ልዩ ምልክት ሲሆን፣ ጉዳዩን ለማጣራትም ወደ ቤተመንግስት በመሄድ የባለቤቷን አድራሻ መጠየቋ ታውቋል። ከቤተ-መንግስት የተሰጣት መልስ ሟቹ ለልዩ ተልእኮ ...
Read More »ፕሬዚዳንት ግርማ ከሊቀ ትጉሐን አስታጥቄ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው ተባለ
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በከባድ የማታለል ወንጀል የተከሰሱት የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኀበር ፕሬዚዳንት የሆኑት ሊቀትጉሃን አስታጥቄ አባተ የቀረበባቸው ክስ እንዲቋረጥ ለፍትህ ሚኒስትር ደብዳቤ እስከመጻፍ የደረሱት ከሊቀመንበሩ ጋር የቅርብ ትስስር ስለነበራቸው እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ዓርብ በፖሊስ ተይዘው ችሎት የቀረቡት የ82 ዓመቱ አዛውንት ሊቀትጉሃን አስታጥቄ አባተ በከባድ የማጭበርበር ወንጀል ...
Read More »የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሥራቸውን ለቀቁ
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላለፉት ስምንት ዓመታት የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅትን በዋና ሥራ አስፈጻሚነትና በቢሮ ኃላፊነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ሽፈራው ዓለሙ፣ ሥራቸውን ከሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ ሥራቸውን መልቀቃቸው ተዘገበ። አንዳንድ ወገኖች ሥራ አስኪያጁ ሥራቸውን የለቀቁት ከጤና ጉዳይ ጋር በተያያዘ በፈቃዳቸው ነው ሲሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ የሙስና ክስ ስለተመሰረተባቸው ሥራቸውን ይለቁ ዘንድ ከመንግስት ባለስልጣናት ጫና ተደርጎባቸው ...
Read More »የግብጽ መከላከያ የ48 ሰዓታት የጊዜ ገደብ ሰጠ
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲን አስተዳደር ያልተቀበሉት የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች ፣ ሞካታም እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን የገዢውን ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት በመዝረፍ በርካታ ንብረቶችን ማውደማቸውን ተከትሎ፣ የአገሪቱ መከላከያ መንግስት እና ተቃዋሚዎች ችግራቸውን በ48 ሰአታት ውስጥ የማይፈቱ ከሆነ፣ የራሱን የሰላም የመፍትሄ ሀሳብ እንደሚያስቀምጥ አስታውቋል። የአገሪቱ ጦር ያወጣው መግለጫ የሙርሲ የአንድ አመት የስልጣን እድሜ ማክተሙን ...
Read More »አንድነት ፓርቲ በጎንደር ቅስቀሳ እያደረገ ነው
ሰኔ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ሰኔ 30 ቀን በጎንደር ከተማ አደባባይ ለሚያካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ በከተማዋና በዙሪያ ወረዳዎች የጥሪ ወረቀቶችን በመበተን ላይ እንደሚገኝ የሰሜን ኢትዮጵያ አደራጅ እና የብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አእምሮ አወቀ ለኢሳት ገልጸዋል። በምእራብ አርማጭሆ በአብራሀ ጅራ ከተማ አለልኝ አባይ፣ እንግዳው ዋኘው፣ አብርሀም ልጃለም እና አንጋው ተገኘ የተባሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት ወረቀቶችን ...
Read More »