ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስተዳድሩ-ለፓርቲው በጻፈው ደብዳቤ- መድረክ ለእሁድ ሐምሌ 7 ቀን 2005 ዓመተ ምህረት ከጧቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡00 ሰዓት የሚቆይና ከስድስት ኪሎ ተነስቶ በአራት ኪሎ፣ በፒያሳና በቸርችል ጎዳና በማድረግ መዳረሻው ድላችን ሐውልት የሚያደርግ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያቀረበውን ጥያቄ እንደተመለከተው በመጥቀስ፤ሰላማዊ ሰልፉ የሚደረግበት የጉዞ መስመር በአሁኑ ጊዜ እየተዘረጋ ባለው የባቡር መስመር የትራፊክ መስመር እየተጨናነቀ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ትንታጉ የደቡብ አፍሪካ ፖለቲከኛ ጁሊየስ ማሌማ ፓርቲ መሰረተ
ሐምሌ ፬( አራት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ የወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር ጁሊየስ ማሌማ ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተር የተሰኘ ፓርቲ መስርቷል። ወጣቱ ፖለቲከኛ በነጮች የተያዙት የአገሪቱ መሬት ለህዝቡ እንዲከፋፈል እና ዋና ዋና የማእድን ፋብሪካዎች በመንግስት ቁጥጥር ስር እንዲውሉ እንደሚታገል አስታውቋል። ማሌማ ፓርቲው ጸረ ካፒታሊዝም መሆኑም ገልጿል። “እኛ ጥቁሮች በዚህ አገር ስንኖር የምናሳያው ነገር የለንም፣ ልናሳየው የሚገባ ነገር ...
Read More »አንድነት ፓርቲ በደሴና በጎንደር በመጪው እሁድ ለሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳውን ቀጥሎአል
ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ የኑሮ ውድነት እና የፍትህ እጦት ለመቃወም ፓርቲው በጎንደርና በደሴ የጀመረውን ቅስቀሳ ወረቀቶችን በመበተን፣ እና በመኪና ላይ በመሆን በየሰፈሩ በመዘዋወር በድምጽ ማጉያ የትግል ጥሪ እያስተላለፈ ነው። በደሴ ከተማ በማስተባበር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃንና የፍኖት ነጻነት ጋዜጠኛ የሆነዉ አቶ ወንደወሰን ክንፈ ታግተው ...
Read More »የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ገንዘባቸውን ከንግድ ባንክ ውጭ ባሉ የግል ባንኮችም ማስቀመጥ ይችላሉ ተባለ
ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በ10/ 90 ወይም በ20 / 80 የቁጠባ ስርአት የኮንዶሚኒየም ቤት ለመስራት የሚፈልጉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገንዘባቸውን የመንግስት ንብረት በሆነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ እንዲያስቀምጡ ትእዛዝ ማስተላለፉ የግል ባንኮችን የሚያዳክም ነው የሚል ትችት ሲቀርብ ሰንብቷል። ገንዘባቸውን በግል ባንኮች ያስቀምጡ የነበሩ ደንበኞች ደንበኝነታቸውን እየሰረዙ በንግድ ባንክ ማስቀመጥ ከጀመሩ ባንኮች በደንበኛ እጥረት ከገበያ ውጭ ...
Read More »በኢትዮጵያ የ35 ሀገራት አምባሳደሮች የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጠርተው አነጋገሩ
ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሜሪካን ኤምባሲ በተካሄደው የአምባሳደሮቹ ስብሰባ ላይ በቅርቡ የተመሰረተውንና በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙበትን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ የቻለውን ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ ጠርተው አነጋግረዋል። በተለምዶ ‘‘የኢትዮጵያ ለጋሾች ቡድን’’ የሚል መጠሪያ ያለውና የአሜሪካንን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች በአባልነት የሚገኙበት የለጋሾች ቡድን በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ከፍተኛ የተቃዋሚ አመራሮች ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ...
Read More »በቁጫ ወረዳ የመከላከያ ሰዎች በየቀበሌው እየዞሩ ህዝቡን በማስፈራራት ላይ መሆናቸው ታውቋል
ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የመከላከያ ሰራዊት አባላትና ልዩ ፖሊሶች በቶዮታ ፒክ አፕ መኪኖች ላይ ሆነው በየመንደሩ በመዞር ህዝቡን ሰብስበው እያነጋገሩ ነው። ወታደሮቹ ” የማንነት ጥያቄዎችን ያቀረባችሁት እናንተ ናችሁ ወይስ ጸረሰላም ሀይሎች ናቸው?” በማለት ጥያቄ ሲጠይቁ መዋላቸው ታውቋል። ድርጊቱ በሚቀጥሉት ቀናት በተማሳሳይ መንገድ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀውን የተቃውሞ ሰልፍ ከአሁኑ ለማኮላሸት የታሰበ መሆኑን የአካባቢው ...
Read More »በቁጫ ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩ ሰዎች ቁጥር ከ450 በላይ መድረሱ ታወቀ
ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ካለፈው አርብ ጀምሮ ከማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ተቃውሞ ከ470 ያላናሱ ሰዎች እስከ ትናንት ድረስ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ተቃውሞውን አስተባብረዋል ከተባሉት መካከል በዋና ከተማዋ ሰላም በር የሚኖሩ ከ13 በላይ የአገር ሽማግሌዎችና ታዋቂ ሰዎች ተመርጠው ወደ አርባ ምንጭ እስር ቤት መወሰዳቸው ታውቋል። ወደ አርባምንጭ እስር ቤት ከተላኩት መካከል አቶ አማኑኤል ...
Read More »አዲሱ የአዲስአበባ ም/ቤት ካቢኔ ተመሰረተ
ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ እንደሚሆኑ አስቀድሞ ሲነገርላቸው የነበሩት የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ድሪባ ኩማ የአስተዳደሩን ኃላፊነታቸውን ከአቶ ኩማ እጅ ተረክበዋል፡፡ በተለይ ሪፖርተር ጋዜጣ የምክትል ከንቲባነት ሥልጣን እንደሚይዙ የተነበየላቸው ወ/ሮ አዜብ መስፍን እንደተገመተው ወደስልጣኑ ያልመጡ ሲሆን በምክትል ከንቲባነት የቀድሞ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው ተሹመዋል፡፡ ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በተከናወነው ...
Read More »አንድነት ፓርቲ ለአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ አቤቱታ አቀረበ
ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ፓርቲው ያወጣውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ፣ ወረቀቶችን በትነዋል የተባሉ ሰዎች በየቦታው እየታሰሩ በመሆኑ መንግስት ድርጊቱን እንዲያስቆምና የታሰሩትም እንዲፈቱ ጠይቋል። በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ አብርሃ ጅራ ከተማ አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ ፣ በጎንደር ከተማ አቶ ማሩ አሻገረ አቶ አምደማሪያም እዝራ፣ አቶ ስማቸው ዝምቤ በወገራ ...
Read More »አቶ አየለ ደበላ አረፉ
ሐምሌ ፪( ሁለት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አራጣ በማደበር ተከስሰው 25 ዓመት የተፈረደባቸው አየለ ደበላ በቅጽል ስማቸው አይ ኤም ኤፍ የቀብር ስነስርአት በቅድስት ስላሴ ካቴደራል በከፍተኛ ስነስርዓት ተፈጽሙዋል፡፡ አቶ አየለ የባንክን ሥራ ተክተው በመሥራት፣ አራጣ በማበደር፣ ግብር ባለመክፈልና በሌሎችም ክሶች ጥፋተኛ ተብለው በከፍተኛው ፍርድ ቤት በ22 ዓመታት እስርና በባንክ ያላቸው 12 ሚሊዮን ብር እንዲወረስ ከተወሰነ በሁዋላ፣ አቃቢ ህግ ይግባኝ ...
Read More »