ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወጣቱ ዙከርበርግ እንደገለጸው ድርጅቱ ከኤሪክሰን፣ ኖክያ፣ ኦፔራ፣ ኳልኮም እና ሳምሰንግ ጋር በመተባበር በሞባይል መረጃ ላይ የሚጠየቀው ክፍያ እንዲቀነስ ያደርጋል። በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የኢንተርኔት አግልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት እንደሚሰራ ዙከርበርግ ተናግሯል። አንዳንድ ባለሙያዎች በበኩላቸው የአፍሪካውያን ችግር የኔትወርክ እና የሀይል አቅርቦት ችግር መሆኑን በመጥቀስ በዚህ በኩል ቅድሚያ ሊሰጥ እንደሚገባ ይመክራሉ።
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በዛሬው ዕለት ታስቦ ከዋለው የመለስ ሙት ዓመት በዓል ጋር በተያያዘ አብዛኛው አገልግሎት ሰጪ የመንግስት መ/ቤቶች ይፋዊ ባልሆነ መንገድ ዝግ ሆነው ዋሉ፡፡
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በዓሉን አስመልክቶም ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሶአል፡፡ የአቶ መለስ ሙት ዓመት ጉለሌ በሚገኘው የዕጽዋት ማዕከል የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት፣የጎረቤት አገር መሪዎች፣ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከብርዋል፡፡ በተለይ የመንግስት ሠራተኞች በግዳጅ በመስቀል አደባባይ የሻማ ማብራት ስነስርዓት እንዲያካሂዱ መታዘዛቸው ታውቋል፡፡ ይህን ተከትሎም በርካታ ሠራተኞች ዕለቱን እንደዕረፍት በመቁጠር ...
Read More »ወ/ት ሐዲያ ሙሀመድ ከሳምንታት የእስር ቤት ስቃይ በሁዋላ ተፈታች
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራር የሆነቸው ወ/ት አዲያ አህመድ ከሀምሌ 22 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ስቃይ እስር ቤት ውስጥ ከደረሰባት በሁዋላ በዛሬው እለት በዋስ ተፈታለች። ወ/ት ሐዲያ እንዳለችው መርማሪ ፖሊሶቹ በቁጥጥር ስር ያዋሉዋት አንድነት ፓርቲ ሀምሌ 28 በሶዶ ከተማ ሊያደርገው የነበረውን ህዝባዊ ስብሰባ በተመለከተ የቅስቀሳ ወረቀቶችን መበተኑዋን ተከትሎ ነው። ...
Read More »የቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጠየቀ።
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርቲው የቁጫ ሕዝብ ጥያቄ ሕጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ እንጠይቃለን” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ፓርቲያችን አንድነት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከሚታገልላቸውና ገዥው ፓርቲ ከወረቀት አልፎ ያልተገበራቸው ሀገራዊ ቁምነገሮች ውስጥ ዜጎች ሳይሸማቀቁ በነፃነት ሃሳባቸውንና አመለካከታቸውን የመግለፅ፣ በነጻነት የመደራጀት፣ በገዛ ሀገራቸው በነጻነት የመንቀሳቀስ፣ በፈለጉበት አከባቢ የመኖር፣ የመደገፍ፣ የመቃወም እና ስለመብታቸው ሳይሸማቀቁ የመጠየቅ መብቶች እንደሚገኙበት አመልክቷል። ...
Read More »የተወዳጁ የሬጌ ሙዚቃ አቀንቃኙ የእዮብ መኮንን የቀብር ሥነ-ስርዓት ነገ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከቀኑ 9 ፡00 ሰዓት ላይ ይፈጸማል።
ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ወኪል ከስፍራው ባደረሰን መረጃ አስከሬኑ ዛሬ ንጋት ላይ ተኝቶ ሲታከምበት ከነበረው ከናይሮቢ -ወደ አዲስ አበባ ገብቷል። እዮብ ከሳምንት በፊት ልጁን በብሽክሊሊት ትምህርት ቤት አድርሶ ከተመለሰ በሁዋላ ቤቱ መግቢያ በር ላይ ሲደርስ ድንገት ሰውነቱ አልታዘዝ ብሎት መዝለፍለፉን የገለጸችው ባለቤቱ ቲና፤ከዚያ እንደምንም የበሩን ደወል ተጭኖ መጥሪያ ካሰማ በሁዋላ መቆም አቅቶት በተደገፈው በር ሸርተት ...
Read More »ለአቶ መለስ ሙት አመት መታሰቢያ የመንግስት ሰራተኞች በግድ እንዲገኙ ታዘዙ
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል በልዩ ልዩ ፕሮግራም ታስቦ እንደሚውል ለማወቅ የታቸለ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ደግሞ የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች ምሽትና ነገ ሻማ በማብራት እንዲዘክሩት ታዘዋል። አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች ኢቲቪ አቶ መለስ ዜናዊ ከተናገራቸው ንግግሮች መካከል እያለ ሲያቀርብ መሰንበቱ እንዳሰለቻቸው ተናግረው፣ የፓርቲው ካድሬዎች በየመስሪያ ...
Read More »በቁጫ ወረዳ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሮአል
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወረዳው የተነሳውን ከማንነት ጋር የተያያዘ ጥያቄ ለማፈን መንግስት የጀመረውን ዘመቻ በማጧጧፍ ለውጭ አገር ሚዲያ መረጃ ይሰጣሉ የተባሉትን የቁጫን ህዝብ በመወከል ሲከራከሩ የነበሩት መቶ አለቃ ማሴቢ ማዳልቾ፣ ባለፈው ቀድሜ ተይዘው ዛሬ ወደ አርባምንጭ ተልከዋል። በአጠቃላይ እየታደኑ ካሉት መካከል 12 አንጋፋና ታዋቂ ሰዎች ሲታሰሩ፣ 9ኙ የገቡበት አልታወቀም። በወረዳው የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ወደ ...
Read More »ቴሌ ኮሚኒኬሽን ከቻይናው ዜድ ቲ ኢ ጋር የ 800 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመ
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ስምምነቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሞባይል ስርጭት ተጠቃሚ ወደ 50 ሚሊዮን ለማሳደግ የተደረገ ነው ተብሎአል። መንግስት ለዘርፉ ከመደበው 1 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ከፊሉን ለሌላው የቻይና ኩባንያ ሀዋይ መስጠቱ ታውቋል። ሁለቱም የቻይና ኩባንያዎች የመንግስትን የስልክና የሌሎች የመገናኛ መንገዶች ጠለፋ አቅም እንደሚያዳብሩለት ኢሳት ምንጮችን በመግለጽ መዘገቡ ይታወሳል። የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ዋልታ በሰራው ዜና ...
Read More »በአዲስ አበባ በሳምንት እንድ ቀን ውሀ ማግኘት ብርቅ የሆነባቸው ሰፈሮች መኖራቸው ተዘገበ
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “በሳምንት አንድ ቀን ውሃ ማግኘት ብርቅ የሆነባቸው ሰፈሮች፣ በውሃ እጦት አካባቢያቸውን በመጥፎ ጠረን የሚበክሉ የኮንዶሚኒየም መኖሪያዎች፣ ለተደጋጋሚ አቤቱታ ምላሽ ሳያገኙ በርካታ ወራት እየተቆጠሩ የሚማረሩ ነዋሪዎች የአዲስ አበባ የዘመኑ ገጽታ ሆነዋል” ሲል አዲስ አድማስ ዘገበ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ” በቂ ውሃ ስለሌለ በራሽን ለማከፋፈል እየሞከረ” መሆኑን ገልጿል። ባለስልጣኑ ” የኤሌክትሪክ መቆራረጥና የአንዳንድ ሰራተኞች ...
Read More »ድምጻዊ እዮብ መኮንን ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታዋቂው ድምጻዊ እዮብ መኮንን በብስክሌት ላይ ሆኖ ሲጓዝ በመውደቁ ሆስፒታል ከገባ በሁዋላ በህክምና ሲረዳ ቆይቷል። አርቲስት እዮብ በባልደረቦቹ እርዳታ ወደ ኬንያ በመሄድ ለአጭር ቀናት በህክምና ሲረዳ ቆይቷል። ኢሳት በአርቲስት እዮብ ሞት የተሰማውን ሀዘን ለመግለጽ ይወዳል።
Read More »