ድምጻዊ እዮብ መኮንን ከዚህ አለም በሞት ተለየ።

ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  ታዋቂው ድምጻዊ እዮብ መኮንን በብስክሌት ላይ ሆኖ ሲጓዝ በመውደቁ ሆስፒታል ከገባ በሁዋላ በህክምና ሲረዳ ቆይቷል።

አርቲስት እዮብ በባልደረቦቹ እርዳታ  ወደ ኬንያ በመሄድ ለአጭር ቀናት በህክምና ሲረዳ ቆይቷል።

ኢሳት በአርቲስት እዮብ ሞት የተሰማውን ሀዘን ለመግለጽ ይወዳል።