.የኢሳት አማርኛ ዜና

የቁጫ የአገር ሽማግሌዎች በጠቅላይ ሚ/ሩ ጽህፈት ቤት ተገኙ

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 60 የሚጠጉ የወረዳዋ ሽማግሌዎች በዛሬው እለት ለ7ኛ ጊዜ በጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ጽሀፈት ቤት ቢገኙም ጠ/ሚኒስትሩን ሊያገኙዋቸው እንዳልቻሉና በተወካያቸው በአቶ ወርቁ በኩል መንግስት ጉዳዩን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያሳውቃል የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ለኢሳት ገልጸዋል። በመንግስት መልስ ደስተኞች ያለሆኑት የአገር ሽማግሌዎች፣ እንደገና ተመልሰው ወደ ክልሉ ዋና ከተማ አዋሳ ማቅናታቸው ታውቋል። ሽማግሌዎቹ ለጠ/ሚንስትር ሀይለማርያም ተወካይ ፣ ...

Read More »

የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎችን ቤት ለማዳረስ ከ20 ዓመታት በላይ እንደሚፈጅ አንድ ሰነድ አመለከተ

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ረቂቅ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ የኮንዶሚየም ቤት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ እንደሚወስድ ጠቆሟል። አስተዳደሩ ለኮንዶሚየም ቤቶች ብቻ ከ800ሺ በላይ ዜጎችን ቢመዘግብም በቀጣይ አምስት ዓመት ለመስራት ያቀደው 178 ሺ ቤቶችን ብቻ ነው፡፡ አስተዳደሩ ከ2006 እስከ 2010 ዓ.ም ሥራ ላይ ...

Read More »

ሰላሳ ሶስቱ ፓርቲዎች -ሰማያዊ ፓርቲን ከፓርቲዎች የትብብር መድረክ አሰናበቱ።

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የ33ቱ ፓርቲዎች የትብብር መድረክ -ሰማያዊ ፓርቲን ያሰናበተው፤የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ሰሞኑን ለ ሰንደቅ ጋዜጣ የሰጡት ቃለምልልስ የሌሎች ፓርቲዎችን ክብር የነፈገ ነው በሚል ነው። በዚህም መሰረት ፓርቲዎቹ ባደረጉት ስብሰባ ሰማያዊ ፓርቲ ከስብስቡ እንዲወጣ መወሰናቸውን የቪኦኤ ዘገባ ያስረዳል። የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፀሀፊ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ ውሳኔው የተላለፈው ባለፈው እሁድ በተካሄደ አስቸኳይ ስብሰባ ...

Read More »

በአማራ ክልል በአንድ ሰምንት ጊዜ ውስጥ በጎርፍ ከ45 ሰዎች በላይ ሞቱ

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአካባቢው በሚጥለው ከባድ ዝናም የተነሳ በክልሉ በሚገኘው ኦሮሚያ ዞን ባለፈው ሳምንት ከ30 ያላነሱ ሰዎች የተገደሉበትን ክስተት ጨምሮ ፣ በደቡብ ወሎ ዞን በአንባሰል ወረዳ አንዲት ሚኒ ባስ በጎርፍ በመወሰዷ የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል። በጎርፍ የተወሰዱ ሰዎችን አስከሬን ለማግኘት በተደረገ ጥረት የ14 ሰዎች አስከሬን ተገኝቷል። የአካባቢውን ፖሊስ አዛዥ ለማግኘት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። በክልሉ ...

Read More »

ሆስኒ ሙባረክ ተፈቱ

ነሃሴ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር ተፈተው በሄሊኮፕተር ወደ ጦሩ ሆስፒታል ለምርመራ ተወስደዋል፣ ጊዚያዊው መንግስት ከቤታቸው እንደማይወጡ አስታውቋል። ፕሬዚዳንቱ ከቀረረበባቸው የሙስና ክስ ነጻ በመሆናቸው መፈታታቸው ተገልጿል። ይሁን እንጅ ከሁለት አመት በፊት በግብጽ ከተካሄደው አብዮት ጋር በተያያዘ አሁንም ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸዋል። ደጋፊዎቸቻቸው ደስታቸውን ቢገልጹም፣ የሙስሊም ብራዘርሁድ ደጋፊዎች ደግሞ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። ግብጽ አሁንም በመስቀለኛ ...

Read More »

በቁጫ የተነሳውን ተቃውሞ አስተባብረዋል የተባሉ 32 ሰዎች ከስራ ተባረሩ

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት የወረዳው ምንጮች እንደገለጹት ከተባረሩት ሰራተኞች መካከል 2 አቃቢ ህጎች፣ 2 ዳኞች ፣ 1 ፍርድ ቤት ሬስጅስትራርና አንድ ፖሊስ ይገኙበታል። 8 ሰዎች ደግሞ ከስራ ገበታቸው ላይ ለቅቀው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተሰደዋል። የሚታሰሩ ሰዎች እየተበራከቱ መምጣቱን የሚናገሩት ምንጮች፣ 16 ሰዎች ሰሞኑን ተይዘው ታስረዋል። ካለፈው ወር ጀምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉት 40 ሰዎች ደግሞ በዛሬው ...

Read More »

በቡሬ ግንባር በሰራዊቱ የሚደፈሩ ሴቶች ቁጥር ጨምሯል

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቡሬ ግንባር የሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተለያዩ ጊዜያት የአፋር ሴቶችን አስገድደው እንደሚደፍሩ ከስፍራው ደረሰን መረጃ አመለከተ። የሰራዊቱ አባላት ለቅኝት ወይም ለተለያዩ ስራዎች በሚወጡበት ጊዜ ግመል እና ፍየል የሚጠብቁ ሴቶች ሲያገኙ በሀይል ይድፍራሉ። ነሀሴ 3 ቀን 2005 ዓም አንዳባ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሀሊማ አህመድ የሱፍ የተባለች እድሜዋ ከ45 እስከ 50 የሚጠጋ ሴት በሰራዊቱ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚታየው የመብራት መጥፋት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነዋሪዎች ይናገራሉ

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለሳምንታት መብራት የተቋረጠባቸውን አካባቢዎች በማስመልከት ዘገባውን ያጠናከረው ዘጋቢያችን እንደሚለው በየጊዜው እየሄደ ሳይታሰብ የሚመጣው የኤሌክትሪክ ሀይል፣ መንግስት ላለፉት 21 ዓመታት ገነባሁት የሚላቸው የሀይል ማመንጫዎች የት እንደደረሱ ጥያቄ የሚፈጥር ነው። ያለምንም መብራት መቋረጥ አንድ ሳምንት መድፈን ብርቅ ነው የሚለው ዘጋቢያችን፣ በተለይ የህክምና መስጫ ተቋማት ከመብራት መጥፋት ጋር ተያይዞ በሚፈጠር ችግር ...

Read More »

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሰራተኞች የፓርቲ ስራ እንደሰሩ መታዘዛቸውን ተቃወሙ

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አንዳንድ ሰራተኞች የኢህአዴግ የ2006 እቅድ መስሪያ ቤቱ ካለበት መደበኛ ስራ ውጪ የገዢውን ፓርቲ ድርጅታዊ ስራ በልዩ ሁኔታ እንዲያስፈፅም ማስገደዱን እየተቃወሙ ነው።አብዛኛዎቹ ሰራተኞች ሚኒስቴሩ በ2006 ዓ.ም ድርጅታዊ ስራን ትኩረት ሰጥቶ እንዲተገብር መድረጉ ሰራተኛው ያለፍላጎቱ የመንግስትንና የድርጅትን ስራ ቀይጦ እንዲሰራ የሚያስገድድ ነው ብለዋል። ለጋዜጣው ዝግጅት ክፍል ቅሬታ ያቀረቡት እነዚሁ ...

Read More »

የሆስኒ ሙባረክ መፈታት ግብጽን እንደገና ሊከፍላት ይችላል ተባለ

ነሃሴ ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሲኤን ኤን፣ ቢቢሲ እና ሌሎችም ታዋቂ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞችን በማነጋገር እንደዘገቡት የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር መፈታት ግብጽን በድጋሜ ከሁለት ሊከፍላት ይችላል። አንዳንድ ተንታኞች እንደሚሉት ሙባረክን ለማውረድ የታገሉ ወጣቶች ምናልባትም ራሳቸውን ከሙስሊም ብራዘርሁድ ጋር በማቀናጀት በስልጣን ላይ ባለው መንግስት ላይ ሊዘምቱ ይችላል። ይሁን እንጅ የሙርሲን መንግስት ከስልጣን በማውረድ ...

Read More »