.የኢሳት አማርኛ ዜና

ጣልቃ የሚገቡ ሚኒስትሮች ፍትህን ሲያዛቡ ቆይተዋል ተባለ

           (ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 25/2010) በኢትዮጵያ ያለ ስራ ሃላፊነታቸው በማይመለከታቸው ጉዳይ ጣልቃ የሚገቡ ሚኒስትሮች ፍትህን ሲያዛቡ መቆየታቸውን የቀድሞው የሃገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ገለጹ። ከነዚሁ ሚኒስትሮች መካከልም ያለሃላፊነታቸው የታክስ አቤቱታ የሚሰሙ፣ጨረታ ተከለከልኩ ያሉትን አቤቱታ በመቀበል በአማላጅነት ጣልቅ የሚገቡት አቶ በረከት ስምኦን ነበሩ ብለዋል። አቶ መላኩ ፈንታ የአቶ በረከት ስምኦን ባለቤት ወይዘሮ አሰፉ ፈንቴ ዘመናዊ የፊልም ካሜራ ያለቀረጥ ...

Read More »

አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ለማስታረቅ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 24/2010)ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱትን አቶ በረከት ስምኦንና አቶ ታደሰ ካሳን ከድርጅቱ አመራሮች ጋር ለማስታረቅ እንቅስቃሴ የጀመሩ ባለሃብቶችና ፖለቲከኞች ተቃውሞ ገጠማቸው። አቶ በረከትም ሆነ አቶ ታደሰ ካሳ በኢትዮጵያ ደረጃም ሆነ በአማራ ክልል ለፈጸሟቸው ወንጀሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ቢጠበቅም እናስታርቃለን የሚሉ የአማራ ክልል ባለሃብቶች እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተቃውሞ እንደገጠመው ታውቋል። እርቁ እንዲወርድ ባለሃብቶችን ይዘው እንቅስቃሴ የጀመሩት አቶ አዲሱ ለገሰና የተወሰኑ የጎንደርና ...

Read More »

ታማኝ በየነ ወደ ኢትዮጵያ ሄደ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 25/2010) አርቲስትና አክቲቪት ታማኝ በየነ ወደ ኢትዮጵያ ሄደ። ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ ዳለስ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነገ ዕለት ጠዋት አዲስ አበባ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል። ታማኝ በመቶዎች በሚቆጠሩ አደናቂዎቹ፣ ወዳጆቹና ጓደኞች አሸኛኘት ተደርጎለታል። አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በኢትዮጵያ መንግስት በተደረገለት ግብዣ ከ22 ዓመት በኋላ ወደ ሀገሩ ይገባል። በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀ ...

Read More »

በቴፒ የሚታየው ችግር እየተባባሰ መምጣቱንና ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ነዋሪዎች ተናገሩ

በቴፒ የሚታየው ችግር እየተባባሰ መምጣቱንና ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚል ስጋት መኖሩን ነዋሪዎች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ/ም ) ካለፉት 3 ሳምንታት ጀምሮ በከተማውና አካባቢው የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ እስካሁን 5 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ በተለይ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል አካባቢውን ከጎበኙ በሁዋላ፣ የአፈጉበኤዋን ውሳኔ ተግባራዊ ላለማድረግ ግጭቶችን እየቀሰቀሱ ነው። በቴፒ የነበረውን ግጭት ተከትሎ ለ3 ዓመታት ታስሮ በቅርቡ ...

Read More »

የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት ከፓርቲው ስልጣን የለቀቁት በገዛ ፈቃዳቸው እንጅ ተገደው አለመሆኑን ገለጹ

የሃረሪ ክልል ፕሬዚዳንት ከፓርቲው ስልጣን የለቀቁት በገዛ ፈቃዳቸው እንጅ ተገደው አለመሆኑን ገለጹ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ/ም ) ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያሳየው የክልሉ ምክር ቤት ነሃሴ 23 ቀን 2010ዓም በተጠራበት ወቅት በኦህዴድና ሃብሊ ድርጅት መሪዎች አለመግባባት መፈጠሩን ያመለክታል። የሁለቱ ድርጅቶች አመራሮች መግባባት አለመቻላቸው በሚነገርም፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት ግን ይህንን ያስተባብላሉ። ፕሬዚዳንቱ አቶ ሙራድ አብዱላሂድ ለኢሳት እንደገለጹት ሁለቱ ድርጅቶች ...

Read More »

ከንቲባውን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች ከአዋሳ ግጭት ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ከንቲባውን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች ከአዋሳ ግጭት ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ቀረቡ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ/ም ) የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ እና ሌሎችም ከ100 ያላነሱ ሰዎች በሲዳማና በወላይታ መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ ለበርካታ ዜጎች ሞትና መፈናቀል ተጠያቄዎች ተደርገዋል። የተከሳሾች ጉዳይ የሚታየው በሃዋሳ ከተማ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሲሆን ፣ ከሳሽ ደግሞ የፌደራል አቃቢ ህግ ነው። የዞኑ ...

Read More »

በጎንደር ለአርበኞች ግንቦት ሰባት አቀባበል ዝግጅት እየተደረገ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 24/2010) በጎንደር ለአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሮችና አባላት አቀባበል ለማድረግ የተቋቋመው ኮሚቴ ዝግጅት እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ። ዘመቻ ነጻ ትውልድ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የአቀባበል ፕሮግራም በቅርቡ ከእስር የተፈታችው ታጋይ ወይዘሮ እማዋይሽ  ዓለሙ በተገኙበት ዛሬ በጎንደር ስብሰባ ማካሄዱ ታውቋል። በሌላ በኩል በአዲስ አበባ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሮችንና አባላቱን ለመቀበል በየክፍለ ከተማው ዝግጅቱ ተጠናክሮ እየተካሄደ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ...

Read More »

የአየር ሃይል የመጓጓዣ አውሮፕላን ውስጥ ሲቪሎች መሳፈራቸው ያልተለመደ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ24/2010)በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ሉሜ ወረዳ ከተከሰከሰው የአየር ሃይል የመጓጓዣ አውሮፕላን ውስጥ ከሞቱት 18 ሰዎች መካከል ሲቪሎች ተሳፍረው መገኘታቸው ያልተለመደ መሆኑን የቀድሞው አብራሪ ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ ገለጹ። ከሟቾቹም መካከል 15ቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ ሲቪሎች መሆናቸው ታውቋል።–ከሟቾቹ መካከል ሁለት ሴቶችና ሁለት ልጆች መኖራቸውን መረጃዎች አመልክተዋል። የአደጋው መንስኤም ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ካፒቴኑ ገልጸዋል። የአደጋው ...

Read More »

አብዲ ዒሌ የጠየቁት ዋስትና ውድቅ ሆነ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 24/2010) በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ዑመር አብዲ ዒሌ የጠየቁት ዋስትና ውድቅ መደረጉ ተገለጸ። ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ  ፍርድ ቤቱ ፈቅዷል። ከአቶ አብዲ ዒሌ ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት ሌሎች የቀድሞ የሶማሌ ክልል አመራሮችም ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ታውቋል። በስም መመሳሰል ታስረው የነበሩት አንድ አመራርም መለቀቃቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። አቶ አብዲ ዒሌ ትላንት ...

Read More »

አቶ በረከት ስምኦን ተቃውሞ ገጠማቸው

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 23/2010) አቶ በረከት ስምኦን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየሰጧቸው ያሉ አስተያየቶች በማህበራዊ ድረገጾችና በበርካታ ኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ  ገጠመው። አስተያየት ሰጭዎች እንደሚሉት አቶ በረከት ሕዝቡን ከለውጥ አራማጆች ጋር በማጋጨት የመከፋፈል ስራ እየሰሩ ነው። በቅርቡ ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱት አቶ በረከት ስምኦን የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችንና የለውጥ አራማጆችን ማውገዛቸው በሕዝቡ ዘንድ ቁጣን ፈጥሯል። አቶ በረከት በተለይም ከብአዴን አመራር አባላት መካከል ምክትል ጠቅላይ ...

Read More »