ታማኝ በየነ ወደ ኢትዮጵያ ሄደ

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 25/2010) አርቲስትና አክቲቪት ታማኝ በየነ ወደ ኢትዮጵያ ሄደ።

ዛሬ ከዋሽንግተን ዲሲ ዳለስ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ነገ ዕለት ጠዋት አዲስ አበባ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ታማኝ በመቶዎች በሚቆጠሩ አደናቂዎቹ፣ ወዳጆቹና ጓደኞች አሸኛኘት ተደርጎለታል።

አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ በኢትዮጵያ መንግስት በተደረገለት ግብዣ ከ22 ዓመት በኋላ ወደ ሀገሩ ይገባል።

በተያዘው መርሃ ግብር መሰረት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ጋር ይገናኛል።

ታማኝ ወደ ሀዋሳ፣ አምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ድሬዳዋ፣ ባህርዳር፣ ጎንደርና ሌሎች ከተሞች በመሄድ ከኢትዮጵያውያን ጋር እንደሚወያይ የደረሰን መረጃ ያመልክታል።

ነገ አዲስ አበባ ለሚደርሰው ታማኝ በየነ ደማቅ የአቀባበል ዝግጅት የሚኖር ሲሆን ለዚህ የተቋቋመው ኮሜቴ ህዝቡ አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነን ለመቀበል በነቂስ እንዲወጣ ጠይቋል።