.የኢሳት አማርኛ ዜና

ጠ/ሚኒስትሩ ተቃዋሚዎችን “ይሄ መንግስት ፈርቷል እያላችሁ ራሳችሁን አታሞኙ” አሉ

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ ሀይለማርያም ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ መንግስት የጎዳና ላይ ነውጥ ከሚያሰቡት ሀይሎች ጋር ለመነጋገር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። አቶ ሀይለማርያም በተቃዋሚዎች በኩል የሚቀርበው ቅጥ ያጣ ፍረጃ እና የጥላቻ ፖለቲካ እንዲቆም  እንዲሁም የጎዳና ላይ ነውጥ እናደርጋለን በማለት የሚያስቡ ሀይሎችም ሀሳባቸውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል። “የጎዳና ላይ ነውጥ ለማስነሳት በቂ መረጃ ...

Read More »

32ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጉባኤ በጥሩ መንፈስ እየተካሄ ነው ተባለ

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባቶች ለኢሳት እንደገለጹት በዛሬው ስብሰባ የልማት ኮሚሽኑ ሪፖርት ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ሲሆን፣ መንግስት በቤተክርስቲያኑዋ ገቢ ላይ እየተጠቀመ መሆኑ ተነግሯል። የኮሚሽኑ መሪ ” በጭንቅ ውስጥ ነው እየሰራን ያለነው ፣ በመኖርና ባለመኖር ውስጥ እንገኛለን ያሉ” ሲሆን፣ ስሜታቸውን በድፍረት ሲናገሩ ከዋሉት ጳጳሳት መካከል ብጹዕ አቡነ ቄርሊዎስ ” ዛሬ ጀመርነው፣ እስካሁን የለንም ነበር፣ ዛሬ ስለቤተክርስቲያን ...

Read More »

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሙስና ክስ ጋር በተያያዘ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ከባለሃብቶች ጋር የነበራቸው ቁርኝት የልማታችን ጸር ነበር አሉ፡፡

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ኃ/ማርያም ዛሬ ጠዋት የአገር አቀፍ የጸረ ሙስና ጥምረት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በሸራተን አዲስ በተካሄደበት ስነስርኣት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አንዳንዶቹ ባለሃብቶች ከከፍተኛ መንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሳይቀር የጠበቀ ቁርኝት ፈጥረው እንደነበር አምነው በዚህም ምክንያት ሰዎቹን መንግስት አይደፍራቸውም ተብሎ በህብረተሰቡ ዘንድ እስከመገመት ደርሶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት የመንግስት ባለስልጣናትና ኪራይ ሰብሳቢ ባለሃብቶች ቁርኝታቸውን ...

Read More »

በአፍሪካ ዋና ከተማ 24 ሰዓት ውሀ የሚያገኘው 65 በመቶው ህዝብ ብቻ ነው

ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ በአዲስ አበባ የውሀ ቀለም አይቶ የማያውቅ ህዝብ አለ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ 65 በመቶ የሚሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ ውሀ 24 ሰአት እንደሚያገኝ ገልጸው፣ 20 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሳምንት 5 ቀናት፣ ከ10-15 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሳምንት አንድ ቀን ውሀ ያገኛል ብለዋል። በአብዛኛው የአፍሪካ ዋና ዋና ከተሞች የውሀ አቅርቦት ከ75 እስከ 99 በመቶ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት ላይ ተቃውሞ አሰማች

ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ ስብሰባ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በቤተክርስቲያኑዋ ታሪክ  ተሰምቶ የማያውቅ ተቃውሞ ተከስቷል። አንድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባት እንደገለጹት በስብሰባው ላይ ”  ይህ መንግስት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እንደተነሳ በስፋት ተነግሯል። የፌደራል ጉዳዮች የሀይማኖት ክፍል ሃላፊዎች ዛሬ ስለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ገለጻ ለመስጠት በተገኙበት ወቅት ነው ...

Read More »

የሶማሊ ክልል መንግስት ባለስልጣናት ራሳቸውን ለመከላከል አዲስ ፊልም አዘጋጅተው ለቀቁ

ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ልዩ ሀይል እየተባለ በሚጠራው ታጣቂ ሚሊሺያ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት፣ አስገድዶ መድፈርና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን የሚያመለክት ዛጋቢ ፊልም በስዊድን ቴሌቪዥን መለቀቁን ተከትሎ ፣ የክልሉ መንግስት ምክትል ፕሬዚዳንቱን ቃለመጠይቅ በማድረግ አዲስ ዘጋቢ ፊልም ሰርቶ አቀረበ። የክልሉ መንግስት በለቀቀው አዲስ ፊልም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አድናቆታቸውን የገለጹበት ክፍል የተካተተ ሲሆን፣ ይህም የፌደራሉ መንግስት ጉዳዩን አያውቀውም ...

Read More »

በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ውጥረቱ ቀጥሎአል

ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተማሪዎች አለባበስ ጋር  በተያያዘ ከቀናት በፊት የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ እልባት ሳያገኝ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፡ ትናንትና ከትናንት ወዲያ ምሽት ላይ ጥይት ሲተኮስ ማምሸቱን የገለጹት አንዳንድ የተማሪዎች ቤተሰቦች፣ የተኩሱ ምክንያት ጩሀት የሚያሰሙ ተማሪዎችን ዝም ለማሰኘት ያለመ ነው ብለዋል። ተማሪዎች በየክፍላቸው ሆነው ተቃውሞ እአሰሙ እንደሚገኙ የገለጹት ቤተሰቦች፣ አንዳንዶች ግቢውን ለቀው ወጥተዋል። ዩኒቨርስቲው አዲስ ...

Read More »

አለማቀፍ ጠበቆች የኢትዮጵያን ባለስልጣናት ለፍርድ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀመሩ

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በወጣት አብዱላሂ ሁሴን አማካኝነት በኢትዮጵያ የኦጋዴን ክፍል የተፈጸመውን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብት ጥሰት ፊልም የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በስዊድን ቁጥር አንድ ቴሌቪዥን በትናንትናው እለት መቅረቡን ተከትሎ አለማቀፉ ጠበቆች ጉዳዩን ወደ አለማቀፍ ፍርድ ቤት ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀመረዋል። ወጣት አብዱላሂ ለኢሳት እንደገለጸው ፊልሙ ከተላለፈ በሁዋላ ሚዲያዎች ሸፊ ሽፋን የሰጡት ሲሆን፣ ስቴላም የተባሉ የ አይ ሲ ጄ ጠበቃ ...

Read More »

የእስልምና እምነት ተከታዮች አረፋን በአል አከበሩ

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእየአመቱ የሚከበረው የኢድ-አል አድሃ ( አረፋ) በአል ኢብራሂም ልጁን ለመስዋት ያቀረቡበትን እለት ለመዘከር ነው። በአዲስ አበባ በተካሄደው የበአል አከባበር ስነስርአት ከዚህ ቀደም ያልታዩ ክስተቶች ታይተዋል። ዘወትር እንደሚደረገው የመጅሊስና አዲስ አበባ መስተዳድር ባለስልጣናት ንግግር አላደረጉም። ድምጻችን ይሰማ ትናንት ባወጣው መግለጫ የመንግስት ባለስልጣናት ወይም የመጅሊስ አመራሮች መልእክቶችን ለማስተላለፍ ንግግር ማድረግ ከጀመሩ ህዝቡ በተቃውሞ እንዲያቋርጣቸው መመሪያ አስተላልፎ ...

Read More »

በባህርዳር ከተማ የሚፈጸመው ሙስና ተባብሶ ቀጥሎአል።

ጥቅምት ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመስተዳድሩ ውስጥ የሚሰሩ የኢሳት ወኪሎች እንደገለጹት ከዚህ ቀደም በመስተዳድሩ ውስጥ የሚፈጸመውን ሙስና ማጋለቱን ተከትሎ መንግስት ተጠርጣሪ ግለሰቦችን ከቦታቸው በማንሳት ወደ ሌሎች መስሪያ ቤቶች በማዛወር የህዝቡን ቅሬታ ለመመለስ ጥረት ቢያደርግም፣ አሁንም በአስተዳደሩ ኢንዱስትሪ ልማትና ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት ስር በሚገኙት የከተማ መሬት ልማት ማኔጅመንት ፣ የመሬትና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ምዝገባ ሂደት እንዲሁም የልማታዊ ባለሀብት መሳብና ...

Read More »