.የኢሳት አማርኛ ዜና

የእንድብር ነዋሪዎች በመብራት እና ውሀ መጥፋት ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናል ይላሉ

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጉራጌ ዞን የእንድብር ከተማ  ነዋሪዎች እንደተናገሩት በከተማቸው ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ መብራት በመጥፋቱ እናቶች እህል አስፈጭተው ልጆቻቸውን መመገብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። አቅሙ ያላቸው 30 ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው ወልቂጤ ከተማ በመሄድ እህል ለማስፈጨት መቻላቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ አቅሙ የሌላቸው ግለሰቦች ግን ይህን ማድረግ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል ብለዋል። ይህ በእንዲ እንዳለ መብራት መጥፋቱን ...

Read More »

የቀድሞው የፍልስጥኤም መሪ ያሲር አራፋት የሞቱት ፖሎኒየም በተሰኘ ንጥረ ነገር ተመርዘው እንደሆነ የሚያረጋግጥ መረጃ መውጣቱን አልጀዚራ ዘገበ።

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የስዊዝ ሳይንቲስቶችን የምርመራ ውጤት በመጥቀስ አልጀዚራ  እንደዘገበው፤ በያሲር አራፋት ሰውነት ውስጥ ከመጠን ያለፈ ፖሎኒየም የተሰኘ የራዲዮ አክቲቭ ንጥረ ነገር ክምችት ተገኝቷል። ይሁንና እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2004 ለሞት የተዳረጉት ያሲር አራፋት በፖሎኒየም የተመረዙት መቼ እንደሆነ የሳይንቲስቶቹ ጥናት አያመለክትም። የምርመራ ጥናቱ ውጤት በያሲር አራፋት አስከሬን ውስጥ ከትክክለኛው መጠን   የ 18  ጊዜ  ያህል ብልጫ ያለው ...

Read More »

ቁጫ ዛሬ በተቃውሞ ሰልፍ ስትናወጥ ዋለች

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ አንዴ ሲሞቅ ሌላ ጊዜ ሲቀዘቅዝ የነበረው የቁጫ ተቃውሞ በዛሬው እለት በሰላም በር ከተማ ተጠናክሮ መካሄዱን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመልክታል። ዛሬ ተቃውሞውን ያካሄዱት ተማሪዎች ሲሆኑ ፣ ተማሪዎችም ላቀረብነው ጥያቄ መልስ የማይሰጠን ከሆነ ትምህርት አንማርም ብለዋል። ተቃውሞውን አስተባብረዋል የተባሉ መምህራንም በአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተው ተቃውሞን የመሩትን እንዲያጋልጡ ተጠይቀዋል። ልዩ ሀይል ከተማዋን ተቆጣጥሮ በተማሪዎች ...

Read More »

መንግስት አገሪቱ በሽብር ጥቃት ኢላማ ውስጥ ገብታለች አለ

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጸረ ሽብር ግብረሀይል  ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላላፈው መልእክት አልሸባብና በኤርትራ የሚደገፉ ሀይሎች በመላው አገሪቱ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጁ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ ደርሶኛል ብሎአል። ዜጎች እራሳቸውን ለመከላከል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም ገልጿል። ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ፍተሻዎች ሲደረጉ የሰነበቱ ሲሆን፣ የትናንቱ ማስጠንቀቂያም ይህን ተከትሎ የተሰጠ ነው። መንግስት በኤርትራ የሚደገፉ የሽብር ሀይሎች ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጅተዋል ቢልም ...

Read More »

የኢንተርኔት አፈናንና ስለላን የሚፈቅደው አዋጅ ሀሙስ ይጸድቃል

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ደንብ ቁጥር 250/2003 ሽሮ እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀ ፤ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ለማቋቋሚያ የወጣው አዋጅ ሀሙስ ይጸድቃል።በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተዘጋጅቶ በካቢኔ ፀድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉ የትራንሰፖርት እና የኢንዱስትሪ የቁጥጥር ስርዓቶች ደህንነት ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉት የኢነርጂ፣ የባቡር ኔትዎርክ፣ የአቬሽን፣ ...

Read More »

መከላከያ ኦዲት እንዳይደረግ የሚያስችል አዋጅ ተረቀቀ

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ እንደዘገበው በ2004 በጀት ዓመት ባልተሟላ ሰነድ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ባላይ ወጪ በማድረጉ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጠንካራ ትችት የቀረበበት የመከላከያ ሚኒስቴር የሒሳብ መዛግብቱን ዋናው ኦዲተርን ጨምሮ ለማንኛውም አካል ሚስጢር ማድረግ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል። አዲሱ የመከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅ ሰነድ በአንቀጽ 72 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ...

Read More »

ኢትዩጵያ በምግብ እጥረት የተነሳ ከልጆቹዋ በየዓመቱ 144 ቢሊዮን ብር ታጣለች ተባለ

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወጣት እስከ አዋቂ ያለው ከግማሽ በላይ የሚሆነው ኢትዮጵያ በልጅነቱ  በቂ ምግብ ሳያገኝ ተጎድቶ እንደሚያድግ የተመለከተው በኢትዮጵያ ይፋ በሆነው the cost of hunger in Ethiopia ጥናት ውስጥ ነው። 67 ከመቶ የሚሆነውና ከ15 አስከ 64 የእድሜ ክልል ውስጥ ያለው ኢትዮጵያዊ ጠንካራ ሰራተኛ ቢመስልም በልጅነቱ ያጣው የተመጣጠነ ምግብ አቀንጭሮትና አቀጭጮት አቅም አሳጥቶት በስራው ውጤታማ እንዳይሆን ...

Read More »

በአፋር ሚሌ በሚደረገው ፍተሻ ሾፌሮች መማረራቸውን ገለጹ

ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሾፈሮቹ ለኢሳት እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የሚሄዱና   ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እቃዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ተፈትሸው ለማለፍ ረጅም ጊዜ እንደሚወስዱባቸው ተናግረዋል። ከ10 እስከ 15 ኪሎ ሜትር የሚደርስ የመኪኖች ሰልፍ መኖሩን የሚናገሩት ሾፌሮች፣ በጸሀይ ላይ በሚያደርጉት ጥበቃ በርካታ ሾፌሮች እየተጎዱ መሆኑንም ይገልጻሉ። ፍተሻው የተጀመረው ዛሬ አራት አመት ገደማ ቢሆንም፣ ሰሞኑን የሚታየው ፍተሻ ከወትሮው በከፋ ...

Read More »

የጅጅጋ ነዋሪዎች በብሄር ብሄረሰቦች በአል ስም የሚደርስብን እንግልት ከፍቷል ይላሉ

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ መጪውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በጅጅጋ ከተማ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል። ለገዢው ፓርቲ ታማኞች ናቸው የተባሉና ” በተለምዶ ልማታዊ አርቲስትና ጋዜጠኞች እየተባሉ የሚጠሩ ታዋቂ ሰዎች አካባቢውን በመጎብኘት አድናቆታቸውን ሰጥተዋል። ኢሳት በክልሉ ያለውን ሁኔታ ከዘገበ በሁዋላ የተለያዩ ነዋሪዎች እና ጎብኝዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ክልሉን በቅርቡ አይታ የተመለሰች የመሀል አገር ወጣት፣ ዘመዶቿን ...

Read More »

በአዋሳ አንድ የውጭ አገር ዜጋ ተወግቶ ተገድሎአል

ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምሽቱ 7 አካባቢ አንድ የውጭ አገር ዜጋ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ጀርባው አካባቢ በጩቤ ተወግቶ መገደሉን ለማወቅ ተችሎአል። ግለሰቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኛ ሳይሆን አይቀርም። ግድያውን ማን እንደፈጸመውና ለምን እንደተፈጸመ የታወቀ ነገር የለም። የክልሉን ፖሊስ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን የምናቀርብ መሆናችንን እንገልጻለን።

Read More »