.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሳውዲ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰው ግፍ እንደቀጠለ ነው

ህዳር ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ በሳውዲ አረብያ በተለያዩ የማጎሪያ ጣቢያዎች ታስረው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እንደቀጠለ ሲሆን፣ በዛሬው እለት 2 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ኢትዮጵያውያኑ እንደሚናገሩት ሰዎቹ የተገደሉት ባልና ሚስቶችን ለመለያየት በተደረገ ሙከራ ላይ በተፈጠረ ግርግር ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከሳዑዲው  አቻቸው ልዑል ሳውድ አል ፋይሰል በስልክ መወያየታቸውን የመንግስት የመገናኛ ...

Read More »

በአዲስ አበባ ፍተሻው በአዲስ መልክ ተጀመረ

ህዳር ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ የተባለው አሸባሪ ቡድን እና በኤርትራ መንግስት እገዛ የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በኢትዮጽያ ውስጥ የተለያዩ ስፍራዎች የሽብር ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጁ መሆናቸውን የሚያሳይ አስተማማኝ መረጃ ያለው መሆኑን የብሄራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል ጥቅምት 27 ቀን 2006 ዓ.ም ካስታወቁ በኃላ በአዲስአበባ በመንግስት በግል ተቋማት ከወትሮው የተለየ ፍተሻ በአዲስ መልክ ተጀምሯል፡፡ ግብረኃይሉ በዚሁ ...

Read More »

የግንቦት 7 መሪዎችን ለመግደል የተጠነሰሰው ሴራ ከሸፈ

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ሃለፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ እና በጠቅላይ ሚኒስትሩ የብራዊ ደህንነት አማካሪ በአቶ ጸጋየ በርሄ ቁጥጥር የተመራና በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና በግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል መሪዎች ላይ የተቀነባበረው የግድያ ሙከራ ከሸፈ። ከግንቦት7 ህዝባዊ ሀይል ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንዳመለከተው ለግድያ የተላከው ሙሉቀን መስፍን የተባለው ግለሰብ በትናንትናው እለት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፣ በእየደረጃው ከሚገኙ ...

Read More »

ኢህአዴግ በነገው እለት ስለጸረ ሽብር እንቅስቃሴው ሊመክር ነው

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክር ቤቱ ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ለመንግስት ስልጣን አስጊ ሆኗል ባለው የሽብርተኝነት አደጋ ላይ እንደሚመክር ለማወቅ ተችሎአል። ምክር ቤቱ ከፍተኛ ስጋት ደቅነዋል ባላቸው ግንቦት7 እና የኤርትራ መንግስት ላይ ተነጋግሮ የመፍትሄ እርምጃ ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። ምክር ቤቱ በሳውዲ አረቢያ በካምፕ ውስጥ ስላሉ ኢትዮጵያም ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት 4 ሺ 321 ኢትዮጵያውያን ...

Read More »

የአፍሪካ ጋዜጠኞች የኢህአዴግ ልማታዊ ጋዜጠኝነት አስተሳሰብ ተቹ

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮምሽን በመካሄድ ላይ ባለው 6ኛው የአፍሪካ ሚዲያ አመራሮች ፎረም ላይ ኢህአዴግ የሚያቀነቅነው  የልማታዊ ጋዜጠኝነት ጽንሰ-ሀሳብ በአፍሪካ ጋዜጠኞች ተተችቶአል። ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ችግሮቻቸውን ፊትለፊት አውጥተው መናገር ባለመቻላቸውም ወቀሳ ደርሶባቸዋል። ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ በዚሁ ጉባዔ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጽያ መረጋገጡን በማውሳት ፕሬሱ ግን በውስጡ የአቅም ውስንነቶች እንዳሉበት ይህን ችግር ...

Read More »

ወደ ጅጅጋ መግባትም መውጣትም አይቻልም ተባለ

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በሶማሊ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ የሚታየው ሁኔታ እስከ ዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየ ነው ይላሉ ነዋሪዎች። ከሌሎች አካባቢዎች በመሄድ ወደ ከተማው መግባት ወይም ከከተማው በመውጣት ወደ ሌሎች አካባቢዎች መሄድ  የተከለከለ ነው ይላሉ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማው በብዛት በመገኘት ቤት ለቤት የሚያካሂዱት ፍተሻ ለነዋሪዎች ጭንቀትን ፈጥሮባቸዋል። በክልሉ ፕሬዚዳንት ትእዛዝ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ላፕቶፕ ኮምፒዩተራቸውን ...

Read More »

በየካ ክፍለከተማ አንድ ጤና ጣቢያ ወደ ፖሊስ ጣቢያነት ተቀየረ

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ አጠራሩ ከፍተኛ 12 ቀበሌ 18 ለህዝብ አገልግሎት በሚል የተሰራው ጤና ጣቢያ ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ የእስረኞች ማጎሪያ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሆን መደረጉን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የአካባቢው ነዋሪ በቂ የህክምና ቦታ አጥቶ በሚቸገርበት ጊዜ ፣ መንግስት ጤና ጣቢያውን ፖሊስ ጣቢያ ማድረጉ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የክፍለ-ከተማውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ...

Read More »

በቁጫ ወረዳ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ የሚማሩ ተማሪዎች ከማንነት እና መብት መከበር ጋር በተያያዘ ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ የአንደኛ እና መለስተኛ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትምህርት ማቆማቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ተማሪዎቹ በቋንቋችን እንማር፣ በአካባቢያችን የሚታየው የመብት ረገጣ ይቁም የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ ቁጥራቸው ከ25 እስከ 40 የሚደርሱ ተማሪዎችን ይዞ ...

Read More »

ከመሬት፣ እንዱ ስትሪና ከተማ ፤ልማት ጋር በተያያዘ ከ990 ሺ በላይ አቤቱታዎች መፍትሄ ማጣታቸው ተመለከተ።

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመሬት፣  ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች  መንግስት መልስ ለመስጠት እንደተሳነው መረጃዎች አመልክተዋል። የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት ሴክሬታርያት ፅ/ቤት የ2005 የ6 ወራት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያሳየው ከመሬት፣  ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች መንግስት መልስ ለመስጠት ተስኖታል። የመልካም ...

Read More »

አርሶደአሮች አሸባሪዎችን ነቅታችሁ ጠብቁ መባላቸውን ገለፁ፡፡

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ወሎ ዞን በእያንዳንዱ ቀበሌ  10 ሰዎች እየተመለመሉ አሸባሪዎችን ነቅተው እንዲጠብቁ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን አርሶ አደሮች ተናግረዋል። በስልጠናው የተነሳ አዝመራችንን እንኳ በወቅቱ ለመሰብሰብ አልቻልንም የሚሉት አርሶደአሮች፣ በአካባቢያቸው ጸረ ሰላም ሀይሎች ሲንቀሳቀሱ ከተመለከቱ ወይም ጸጉረ ልውጦችን ከተመለከቱ ለመንግስት አካላት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተነግሮአቸዋል። ለሁለት ሳምንት በሚቆየው በዚህ ስልጠና አርሶአደሮቹ ስለመጪው ምርጫ እና ስለኢህአዴግ እቅድ ...

Read More »