.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአዲስ አበባ የመሬት ማኔጅምንት እና ተዛማጅ ችግሮች እየተባባሱ መምጣታቸውን አመራሮች ገለጹ፡፡

ታህሳስ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አልፎ አልፎ አንዳንድ አመራሮች በአመለካከትም ሆነ በተግባር በሙስና ተዘፍቀው ተገኝተዋል ያለው የአስተዳደሩ ሰነድ፣ በከተማው ውስጥ ሕገወጥ የመሬት ወረራ፣ ሕገወጥ ግንባታና ሕገወጥ ንግድ አሁንም አሳሳቢ ችግሮች ሆነው መቀጠላቸውን አትቷል፡፡ በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮችን ጠርቶ የመከረው ቢሮው ችግሮች በስፋት የመልካም አሰተዳደር እጦት መገለጫ እየሆኑ መምጣታቸውን የቢሮው ሃላፊ አቶ ሰለሞን ሃይላይ ...

Read More »

ከ600 በላይ አባዎራዎች ቤታቸውን በ3 ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ታዘዙ

ታህሳስ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ትእዛዙን የሰጠው የቦሌ ክፍለከተማ ሲሆን፣ ነዋሪዎቹ እስከ ማክሰኞ ቤታቸውን ለቀው ካልወጡ ፣ አፍራሽ ግብረሀይል በጉልበት እንደሚያፈርስባቸው አስታውቋል። “በሶስት ቀናት ውስጥ የት እንሄዳለን?’ ሲሉ የሚጠይቁት ነዋሪዎች ፣በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ የሚታየው የቤት ኪራይ መጨመር አስግቶናል ብለዋል። ሜዳ ላይ እንዃ እንዳንወድቅ ሜዳውም እየታረሰ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ምሬታቸውን ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ ባለስልጣናት በስልጣናቸው ...

Read More »

በኢትዩጵያ ያለ እድሜ ጋብቻ እንደቀጠለ መሆኑ ተገለጸ

ታህሳስ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- በኢትዩጵያ  62 በመቶ የሚሆኑት ከ 20- 49 እድሜ ክልል የሆናቸው ሴቶች ጋብቻ የመሰረቱት እድሚያቸው ከ 18 ዓመት በታች በነበሩበት ወቅት ነው፡፡ አቶ ተስፋየ ተካ የህዝብ ጤና ባለሙያ ባደረጉት ጥናት በላፈው ዓመት ልዩነቶችን ለማወቅ በተካሄደ ጥናት  በአማራ ክልል ያለ እድሜ ጋብቻ  ከፍተኛውን መጠን እንደያዘ ይኸው ጥናት ይጠቁማል፡፡48 በመቶ በገጠር 28 በመቶ በከተማ ያገቡ ሴቶች ...

Read More »

የድምጻችን ይሰማ ዋና መሪዎች እንዲከላከሉ ተበየነባቸው

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- በሽብር ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ መሪዎች ተከላከሉ መባላቸውን ጠበቃ  ተማም አባ ቡልጉ ተናግረዋል። 12 ሰዎች በነጻ የተለቀቁ ሲሆን፣ እነ አቶ አቡበከር አህመድና ሌሎች ደግሞ በተከሰሱበት ሽብር የማድረግ ወንጀል ሳይሆን ሽብር በማነሳሳት ጉዳይ ላይ እንዲካለከሉ ተበይኖአል። ሙራድ ሹኩር ጀማል፣  ኑሩ ቱርኪ  ኑሩ፣ ሼህ ባህሩ ኡመር ሸኩር እና ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው ደግሞ ...

Read More »

መድረክ በኢትዮጵያ ያለው አፈና መባባሱን ገለጸ

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መድረክ  ዓርብ ታህሳስ 4 ቀን 2006 ዓ.ም በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን፣  ዶ/ር መረራ ጉዲና ለኢሳት እንደገለጹት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው አፈና እየተባባሰ መሄዱ መግለጫውን ለመስጠት አስገድዷቸዋል። የሳውድ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን እርምጃ ለመቃወም መድረክ ቢጠይቅም በገዢው ፓርቲ መከልከሉን ዶ/ር መረራ አውስተዋል ( 1፡49-03፡10) መንግስት የሳውድ አረቢያ ...

Read More »

የሕገመንግስት የትርጉም ጥያቄ ያስነሳው የአቶ መላኩ ጉዳይ ዛሬም አልተቋጨም

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ክሳቸው በየትኛው ፍርድ ቤት ይታይ በሚለው ጉዳይ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመጨረሻ ውሳኔውን እንዲያሳውቅ ሲል የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ትእዛዝ በመስጠት ለታህሳስ 22 ቀን 2006 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጉዳዩን የመረመረው የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ...

Read More »

በኔልሰን ማንዴላ የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ መስማት ለተሳናቸው ትርጉም ያቀርብ የነበረው ግለሰብ የተሳሳተ መልእክት ሲያስተላልፍ ነበር ተባለ

ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ማክሰኞ በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ በተደረገው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ  ከመድረክ ይተላለፍ የነበረውን ዝግጅት በምልክት ቋንቋ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች እንዲያስተላልፍ  ተመድቦ የነበረው  ሰው፤ ያሳይ የነበረው አካላዊ እንቅስቃሴና ምልክት የውሸት እንደነበር መጋለጡን ዓለማቀፍ ብዙሀን መገናኛ እየዘገቡ ነው። ድርጊቱ የደቡብ አፍሪካን መንግስትና በ ዓለማቀፍ ደረጃም መስማት የተሳናቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ክፉኛ አስቆጥቷል። ከነ ባራክ ...

Read More »

40 በ 60 እና 10 በ 90 የቤት እቅዶች መንግስትን ፈተና ውስጥ ጥለውታል

ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- መንግስት በውጭ አገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ሀቅሙ ላላቸው ዜጎች የ40 በ60 እንዲሁም በአዲስ አበባ በአነስተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ዜጎች ደግሞ የ10 በዘጠና እና የ20 በ80 የቤት ልማት እዶችን ዘርግቷል። በ10/90 850 ሺ በ 20/80 ደግሞ 350 ሺ የአዲስ አበባ ነዋሪ ተመዝግቦ እድሉን በመጠባበቅ ላይ ሲሆን ከ12 ሺ በላይ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ 40 በ60 ...

Read More »

በኢትዮጵያ ለሚታየው መብራት መጥፋት መስሪያቤቶች እርስ በርስ እየተካሰሱ ነው

ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች እና በሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ከተሞች መብራት በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ሲሆን፣ መብራት ሀይል የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተናበው ለመስራት አልቻሉም በሚል ወቀሳ አሰምቷል።  በጉዳዩ ዙሪያ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው የኢትዩጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ     40 በመቶ የሚሆነው ኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ የሚፈጠረው በሰው ሰራሺ አደጋ ነው ያሉ ሲሆን፣  ከአዲስ አበባ መንገድ እና ...

Read More »

በአርባ ምንጭ ዙሪያ የሚገኙ መምህራን ደሞዛቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ

ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- መምህራኑ ለኢሳት እንደተናገሩት ያለፍላጎታቸው ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ መቆረጡን በመቃወም የተቆረጠው ገንዘብ ተመልሶ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ሙሉ ደሞዛችን እስካልተሰጠን ድረስ ምንም አይነት ክፍያ አንቀበለም ያሉት መምህራኑ፣ እስከ ፊታችን አርብ ሙሉ ደሞዛችን የማይሰጠን ከሆነ የስራ ማቆም አድማ እንዳርጋለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በደቡብ ክልል መንግስት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከመምህራኑ ደሞዝ ላይ ያለፍላጎታቸው እየተቆረጠ ...

Read More »