በአርባ ምንጭ ዙሪያ የሚገኙ መምህራን ደሞዛቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ

(ሁለት)ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :- መምህራኑ ለኢሳት እንደተናገሩት ያለፍላጎታቸው ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ መቆረጡን በመቃወም የተቆረጠው ገንዘብ ተመልሶ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ሙሉ ደሞዛችን እስካልተሰጠን ድረስ ምንም አይነት ክፍያ አንቀበለም ያሉት መምህራኑ፣ እስከ ፊታችን አርብ ሙሉ ደሞዛችን የማይሰጠን ከሆነ የስራ ማቆም አድማ እንዳርጋለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በደቡብ ክልል መንግስት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከመምህራኑ ደሞዝ ላይ ያለፍላጎታቸው እየተቆረጠ መሆኑ የመምህራኑን ተቃውሞ እያስተናገደ ነው።