.የኢሳት አማርኛ ዜና

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲታደጋቸው እየተማጸኑ ነው

ታህሳስ ፲፰ አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዩኒቲ በሚባለው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን በጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ መገኘታቸውንና ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን ተናግረዋል። በግዛቱ ውስጥ በአንድ የመንገድ ስራ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ 6 ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የሚደረገውን የተኩስ ልውውጥ ለማምለጥ ያለፉትን ሁለት ቀናት በከባድ ማሽነሪዎች ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአካባቢያቸው 2 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና 3ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ...

Read More »

በሳውድ አረቢያ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ውስጥ ዘረኝነትና ሙስና ተስፋፍቷል ተባለ

ታህሳስ ፲፰( አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከቆንስላው ባገኘው የውስጥ መረጃ በሃላፊነት ላይ የተመደቡት አምስቱ ዲፕሎማቶች በዘረኝነትና በሙስና ከመዘፈቃቸው ም በተጨማሪ ሊሴ ፓሴ ለማውጣት ወደ ቆንስላው የሚደውሉትን ስደተኞች በስብሰባ ሰበብ የሉም በማስባል ጉዳያቸውን እያስፈጸሙ እንደልሆነ ተመልክቷል። ከአንድ ወር በፊት ከ160 ሺ በላይ ህዝብ የተፈናቀለበትን ችግር ለማወቅ በቆንስላው የተገኙትና ከዲፕሎማቶች ውጭ ያሉ ሰራተኞችን ብቻ በመሰብሰብ ” የችግሩ ምንጭ ...

Read More »

በቅርቡ ከእስር በተለቀቁት አንዳንድ የሙስሊም የመፍትሄ ኮሚቴ አባላት መካከል በ6ቱ ላይ ይግባኝ ሊጠየቅ ነው

ታህሳስ ፲፰( አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ምድብ ችሎት ካሰናበታቸው ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን መካከል በስድስቱ ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ መጠየቁ ታውቋል። አቃቢ ህግ ውሳኔው እንደተላለፈ ይግባኝ እንደሚል ባስታወቀው መሰረት ይግባኝ ማለቱ ታውቋል።  አቃቢ ህግ ይግባኝ የጠየቀባቸው ሰዎች ስም ዝርዝር አልታወቀም። አንዳንድ አስተያያት ሰጪዎች አቃቢ ህግ ይግባኝ መጠየቁ ፍርድ ቤቱ ነጻ መሆኑን ለማሳየት ተብሎ የተቀነባበረ ...

Read More »

በሞቃዲሹ ምግብ ቤት ውስጥ በተጠመደ ፈንጅ 11 ሰዎች ተገደሉ

ታህሳስ ፲፰ ( አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንዳጠመደው በሚገመተው ፈንጅ ከሞቱት መካከል 6ቱ ወታደሮች ናቸው ተብሎአል። አንድ የሞቃዲሹ ፖሊስ ባለስልጣን ግን የሞቱት ወታደሮች ቁጥር 3 ናቸው ይላሉ። ወታደሮች ወርሀዊ ደሞዛቸውን ተቀብለው በምግብ ቤቱ ውስጥ እንደተገኙ ፍንዳታው መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል። የምግብ ቤቱን ባለቤት ጨምሮ 5 ሲቪሎች የተገደሉ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ ፍንዳታውን አደረስኩ የሚል ወገን መግለጫ አልሰጠም። አልሸባብ ...

Read More »

በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በነጭ ሳር ግቢ የሚማሩ ከ25 ያላነሱ ተማሪዎች መታሰራቸው ታወቀ

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ተማሪዎቹ የታሰሩት ካለፈው አርብ ጀምሮ ሲሆን፣ እስካሁንም በእነርሱ ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት አለመቆሙ ታውቋል። በግቢው ውስጥ ተማሪዎች የሚጠቀሙበት መጸዳጃ የተበላሸ መሆን፣ የምግብ ጥራት መጓደል፣ የውሀ እጥረት፣ የመብራት ለረጅም ጊዜ መቋረጥ፣ የትምህርት ስርአቱ በተገቢው መልኩ አለመከናወን፣ የመጽሀፍት እጥረት፣ የኮምፒዩተር አለመኖር እና በተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው የጤና መቃወስ ተማሪዎች ተቃውሞ እንዲያነሱ ግድ ብሎአቸዋል። ...

Read More »

በቦሌ ቡልቡላ፣ በለሚና እና በአቃቂ ክፍለ ከተማ በርካታ ህዝብ ሜዳ ላይ መውደቁ ተገለጸ

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደገለጹት ላለፉት 25 አመታት ከኖሩበት ቤት በጉልበት ተነሱ በመባላቸው ሜዳ ላይ ለመውደቅ ተገደዋል። ነዋሪዎቹ ስሜታቸውን በከፍተኛ ሀዘን እየገለጹ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል። የመንግስትን እርምጃ በመቃወማቸው የተወሰኑ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁንም ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአዳማም በተመሳሳይ መንገድ  ከ25 ሺ በላይ ህዝብ ቤት አልባ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።

Read More »

ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ሕዝብ ያዋጣው 5.7 ቢሊየን ብር ነው ተባለ

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት ዓመታት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ከሕዝብ የተዋጣው ገንዘብ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ሲነገር ቢቆይም አንድ ባለስልጣን ግን ትክክለኛው አሀዝ  5 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ነው ሲሉ ተናግረዋል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ጽ/ቤት የአቶ በረከት ስምኦን ምክትል የሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሃን ጠቅሶ መንግስታዊው አዲስ ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እጣ ፋንታ አልታወቀም

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ባለፈው ረቡዕ ቦር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የታየውን ከፍተና ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አልታወቀም። በርካታ ደቡብ ሱዳናውያን በመንግስት ደጋፊና ተቃዋሚዎ ታጣቂዎች መገደላቸውን ሲኤን ኤን የዘገበ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚኖሩ ከ1 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን እጣ ፋንታ እስካሁን በውል አለመታወቁንም ከአካባቢው ሸሽተው ወደ ኡጋንዳ ድንበር የደረሱ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ...

Read More »

የፌዴሬሽን ምክርቤት በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-በአቶ ካሳ ተክለብርሃን የሚመራው የፌዴሬሽን ምክርቤት ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሙስና ወንጀል በተከሰሱት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት የፊታችን ሰኞ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ታወቀ፡፡ የፌዴራሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል በመጠርጠር በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ስር ከባለስልጣናትና ባለሀብቶች ጋር ክስ የመሰረተባቸው አቶ መላኩ ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን ተገደው የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጁባ ገቡ

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ የተደፈሩ 4 ሴቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል በሚገኝበት ጁባ ደርሰው ምርመራ እየተደረገላቸው ነው። ሴቶቹ መደፈራቸውንና ሆስፒታል መግባታቸውን ኢሳት ለማረጋገጥ የቻለ ሲሆን፣ ሴቶቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ያደረገው ጥረት በመስመር ግንኙነት የተነሳ ሊሳካለት አልቻለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከውጭ ጉዳይ ...

Read More »