በቅርቡ ከእስር በተለቀቁት አንዳንድ የሙስሊም የመፍትሄ ኮሚቴ አባላት መካከል በ6ቱ ላይ ይግባኝ ሊጠየቅ ነው

ታህሳስ ፲፰( አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ምድብ ችሎት ካሰናበታቸው ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን መካከል በስድስቱ ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ መጠየቁ ታውቋል።

አቃቢ ህግ ውሳኔው እንደተላለፈ ይግባኝ እንደሚል ባስታወቀው መሰረት ይግባኝ ማለቱ ታውቋል።  አቃቢ ህግ ይግባኝ የጠየቀባቸው ሰዎች ስም ዝርዝር አልታወቀም። አንዳንድ አስተያያት ሰጪዎች አቃቢ ህግ ይግባኝ መጠየቁ ፍርድ ቤቱ ነጻ መሆኑን ለማሳየት ተብሎ የተቀነባበረ ድራማ ነው።

የኮሚቴ አባላቱ ሰሞኑን ከቃሊቲ ባወጡት መግለጫ ከፍተኛ ሆነ አካላዊና መንፈሳዊ ሰቆቃ በኢትዮጵያ የእስር ቤት ባለስልጣናት ቢፈጸምባቸው ፣ ሙስሊሙ የሚያደርገውን ትግል አጠንክሮ መቀጠል እንዳለበት ማሳሰባቸው ይታወቃል።