ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ማክሰኞ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ትናንት የዩኒቨርስቲ ግቢውን ለቀው በመውጣት ላይ በነበሩ ተማሪዎች ላይ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ የአንዲት ተማሪ ጆሮ መቆረጡንና በርካታ ተማሪዎች እጆቻቸውና እግሮቻቸው መሰበሩን ተማሪዎችና የዩኒቨርስቲው መምህራን ለኢሳት ገልጸዋል። ችግሩ የተፈጠረው የውሃ ኢንጂነሪንግር ተማሪዎች የትምህርት ዘርፍ ለውጥ እንዲደረግ መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው። ዩኒቨርስቲው የትምህርት-ዘርፍ ለውጥ እንደማያደርግ እና መማር የማይፈልጉ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢህአዴግ ሚኒስትሮቹን የግንባሩን ስራ እንዲያከናውኑ መደበ
ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ፓርቲውን እንዲመሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ሁለት ሚኒስትር ዴኤታዎችን ባለፉት ወራት መሾሙን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ኢህአዴግ የመንግስት መዋቅርን ከፓርቲው መዋቅር ጋር አደበላልቆ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ተደጋጋሚ ወቀሳዎችና ትችቶች እየቀረቡበት የቆየ ሲሆን በዚህ መልኩ ግልጽ የሆነ አደረጃጀት በመያዝ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችን ሲመድብ ከአቶ መለስ ሞት በሃላ ...
Read More »የመንግስት ባለስልጣናት የ7 ሚሊዮን ብር መኪና መግዛት ማቆም አለባቸው ሲሉ አፈ ጉባኤው ተናገሩ
ጥር ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አባ ዱላ ገመዳ ይህን የተናገሩት በዛሬ የፓርላማ ውሎ ላይ ነው። የመንግስት መስሪያ ቤቶች በአገር ውስጥ የተመረቱ ምርቶችን መጠቀምና በ7 ሚሊዮን ብር የሚገዙ መኪኖችን መጠቀም ማቆም አለባቸው ብለዋል። ኢሳት አዲስ አበባ መስተዳድር ሰሞኑን እጅግ ዘመናዊ መኪኖቹን በብዙ ሚሊዮን ዶላር ለባለስልጣነቱ ገዝቶ ማከፋፈሉን መዘገቡ ይታወሳል።
Read More »የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጎንደር ላይ ታሰሩ
ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድንበር ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መንግስታት መካከል ያለው ንግግር ለህዝብ ግልጽ እንዲሆን ለመጠየቅ በመጪው እሁድ በጎንደር ከተማ ለማካሄድ የታቀደውን ሰልፍ ለማስተባበር ወደ ጎንደር ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ፣ ሌሊት ከተማዋ ደርሰው በማግስቱ የቅስቀሳ ስራ ሲጀምሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። አመራሮቹ ሲታሰሩ የተመለከተ አንድ ታዛቢ ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቆይታ ...
Read More »ኢህአዴግ ልማቱን ለመጨረስ ከ40 እስከ 45 አመት ያስፈልገዋል ሲሉ አቶ በረከት ተናገሩ
ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጠ/ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ይህን የተናገሩት ለኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች ነው። ለማንኛውም የመገናኛ ብዙሃን ዝግ በሆነው የካድሬዎች ስብሰባ ላይ ጥናታዊ ወረቀታቸውን ያቀረቡት አቶ በረከት፣ ኢህአዴግ የህዝቡን የነፍሰ ወከፍ ገቢ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ለማድረስ ቢያንስ ከ40 እስከ 50 ዓመታት እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል። አቶ በረከት የወደፊቱ የህዳሴ መንገድ በሚል ባቀረቡት ጽሁፍ ...
Read More »አንድ የትምህርት ሚኒስቴር አውቶቡስ ተገልብጦ 6 ሰዎች ሞቱ
ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አውቶቡሱ 40 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደብረማርቆስ በጉዞ እያለ ነበር አባይ በረሃ ውስጥ የተገለበጠው። 6 ሰዎች ወዲያው ሲሞቱ 11 ሰዎች ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል:: ተሰፋሪዎቹ በደብረማርቆስ የሚካሄደውን የትምህርት ፊስቲቫል ለማክበር እየተጓዙ ነበር።
Read More »በሱዳን በስድስት ጎረምሶች የተደፈረችው ወጣት ክስ ተመሰረተባት
ጥር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው እሁድ ጉዳዩዋን ለማየት የተሰየመው ፍርድ ቤት ቀጠሮው እንዲተላለፍ ወስኗል። ፖለስ በበኩሉ ኢትዮጵያዊቷ ወሲቡን የፈጸመችው እና በቪዲዮ እንዲቀረጽ የፈለገችው ተስማምታ ነው በማለት ዝሙት በመፈጸም ክስ ሊመሰርት በሂደት ላይ ነው። ፖሊስ ክሱን ለመመስረት የተነሳሳው ወጣቷ እንደተደፈረች ወዲያውኑ ለፖሊስ ሪፖርት አላደረገችም በሚል ነው። ወጣቷ በበኩሉዋ ደፋሪዎቹ እንገድልሻለን በማለት ስላስፋሩዋት ወዲያዉኑ ሪፖርት ለማድረግ እንዳልቻለች ትገልጻለች። ...
Read More »የኢትዮጵያ መንግስት የግንቦት7 መሪዎችን ኮምፒዩተሮች በዘመናዊ የስለላ መሳሪያዎች ሲሰልል እንደተደረሰበት አንድ አለማቀፍ ተቋም አጋለጠ
ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዝቦችን ደህንነት ከመንግስታት ጥቃት ለመከላከል የተቋቋመው ፕራይቬሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ተቋም ለእንግሊዝ መንግስት የገቢዎቸና ጉምሩክ መስሪያ ቤት በጻፈው ደብዳቤ “ጋማ ኢንተርናሽናል የተባለው የእንግሊዝ ኩባንያ በአለም ላይ የሰብአዊ መብቶችን በመጣስ ለሚታወቁ አገሮች ኮምፒይተሮችን፣ የሞባይልና የስካይፕ የስልክ ግንኙነቶችን እንዲሁም የኢሜል ልውውጦችን በርቀት ሆኖ ለመከታተል የሚያስችለውን ፊን ፊሸር ወይም ፊን ስፓይ በሚል ስም የሚጠራውን የመሰለያ ...
Read More »የአሜሪካ ኮንግረስ ለኢትዮጵያ መከላከያ እና ፖሊስ የሚሰጠው እርዳታ በቅድመ ሁኔታ ላይ እንዲቀመጥ ወሰነ
ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦሚኒበስ አፕሮፕሬሽን ቢል 2014 በድንጋጌው ለኢትዮጵያ ወታደራዊና ፖሊስ ሃይሎች የሚሰጠው ድጋፍ በቅድመ ሁኔታ ላይ እንዲቀመጥ ወስኗል። የኢትዮጵያ መንግስት የፍርድ ቤቶችን ነጻነት ካልጠበቀ፣ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ካላከበረ፣ የሰዎችን የመሰብሰብ፣ የመደራጀትና የሃይማኖት ነጻነትን ካላከበረ፣ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ተቋማት ካለምንም የመንግስት ጣልቃ ገብነት ስራቸውን እንዲሰሩ ካልተደረገ የአሜሪካ ኮንግረስ ድጋፍ አያደርግም ። እንዲሁም ...
Read More »በተለያዩ ክልሎች ዜጎች በህገወጥ መንገድ መፈናቀላቸውን እየገለጹ ነው
ጥር ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል በአሳይታ ወረዳ በርካታ ነዋሪዎች ከ40 አመታት ላናነሰ ጊዜ የኖሩባቸውን ቤቶች እንዲለቁ መታዘዛቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። አብዛኞቹ ተፈናቃዮች በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራኒዮ ደግሞ ከ300 ያላነሱ ጉሊቶች ንብረታቸውን እየተቀሙ መደብሮቻቸው እንዲፈርስባቸው መደረጉ ታውቋል።ሰዎቹ ለረጅም ጊዜ ሲገለገሉበት የነበረውን ጉሊት እንዲያፈርሱ የተገደዱት ህገወጦች ናችሁ ተብለው ነው። ነዋሪዎች ...
Read More »