ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የኦሮምያ ልዩ ዞን እየተባለ በሚጠራው የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ የሚገኘው የአርሶአደሩ መሬት በከተማዋ ውስጥ ባልኖሩና ማንነታቸው በማይታወቅ ሰዎች ስም መያዙን ለኢሳት የደረሰው ሰነድ አመልክቷል። ከ4 ሺ በላይ ሰዎችን ስም ዝርዝር በያዘው በዚህ ሰነድ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች የአባታቸውን ስም ብቻ በመቀያየር ከ 140 እስከ 500 ካሬ ሜትር ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአማራው ክልል መሪ ንግግር ህዝቡ ቁጣውን እየገለጸ ነው
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብአዴን የጽ/ቤት ሃላፊና የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት የሆኑት አለምነው መኮንን የአማራውን ህዝብ መዝለፋቸውን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ቁጫቸውን እየገለጹ ነው። በማህበራዊ የመገናኛ መንገዶች ከሚሰጡት አስተያየቶች በተጨማሪ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት በመደውል አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ ግለሰቡ ከመነሻቸ ጠንካራ የትምህርት ደረጃ የሌላቸው በመሆኑ፣ ከዚህ ያለፈ እንዲናገሩ አይጠበቅም ብለዋል ሌላው አስተያየት ሰጪ ደግሞ ...
Read More »አራት ኢትዮጵያውያን በኬንያ የጸረ ሽብር ግብረሃይል ተያዙ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምስራቅ አፍሪካ ሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት አራቱ ኢትዮጵያውያን በኬንያ የጸረ ሽብር ግብረሃይል የታየዙት በተለያዩ ቀናት ነው። ቱምሳ ሮባ ካቲሶ የተያዘው ኢስሊ እየተባለ በሚጠራው የገበያ ስፍራ ሲሆን፣ በሁለት መኪኖች የመጡ የጸጥታ ሃይሎች በፈረንጆች አቆጣጠር ፌብሩዋሪ 1፣ አፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ ወስደውታል። ጫላ አብደላ፣ ናሚ አብደላ፣ እንዲሁም ስሙ በውል ...
Read More »የጣሊያን ፖሊሶች ከ1 ሺ በላይ የሚሆኑ ስደተኞችን ህይወት አተረፉ
ጥር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአፍሪካ በመርከብ ተሳፍረው ወደ አውሮፓ ለመግባት የሞከሩ 1 ሺ 100 የሚጠጉ ስደተኞች በጣሊያን ፖሊሶች እርዳታ አውሮፓ እንዲገቡ ተድርጓል። ከዚህ በፊት ላምባዱሳ እየተባለ በሚጠራው የጣሊያን ግዛት አካባቢ ከደረሰውን አሰቃቂ አደጋ በሁዋላ የጣሊያን ፖሊሶች ወደ አውሮፓ የሚገቡ አፍሪካውያንን ህይወት እየታደጉ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ ወደ አውሮፓ ከገቡት መካከል 50 ህጻናትና 47 ሴቶች ...
Read More »አውራ የኢህአዴግ ፓርቲዎች አዳጊ ክልሎችን ለማስተዳደር ስልጣን ተሰጣቸው
ጥር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ እየተባለ የሚጠራውን ግንባር የመሰረቱት 4ቱ ፓርቲዎች ህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን አዳጊ ክልሎች እየተባሉ የሚጠሩትን ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ፣ ድሬዳዋ፣ ሶማሊና አፋር ክልሎችን ለማስተዳደርና በበላይነት ለመምራት መከፋፈላቸውን ከኢህአዴግ ፅ/ቤት የተገኘው የውሰጥ መረጃ አመለከተ። በኢትዮጵያ ህገ መንግስት አንቀጽ 52 ክልሎች ራስን በራስ የማስተዳደር ስልጣን የተሰጣቸው ሲሆን፣ ስልጣናቸውን ተጠቅመመውም የክልሉን የኢኮኖሚ፣ የመህበራዊና የልማት ...
Read More »የወጪ ንግድ እያሽስቆለቆለ ነው ተባለ
ጥር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እጅግ በተለጠጠው የኢትዮጽያ መንግስት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መሰረት በያዝነው 2006 በጀት ግማሽ ዓመት የወጪ ንግዱ ገቢ በከፍተኛ ደረጃ ማሽቆልቆል ማሳየቱን ያገኘናቸው መረጃዎች ጠቆሙ፡፡ በ2006 ግማሽ የበጀት ዓመት ከሆርቲካልቸር እና ከቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኤክስፖርት የተገኘው ገቢ ከዕቅዱ አንጻር እጅግ አነስተኛ መሆኑ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ ከሆርቲካልቸር ዘርፍ ማለትም አበባ ፣አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን ለውጪ ገበያ ...
Read More »መንግስት አንዳንድ ብቅ በማለት ላይ ያሉ ነጻ ጋዜጦችን ለመቅጨት እየሰራ ነው ተባለ
ጥር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የጋዜጦችና የመጽሔቶችን ስርጭት አስተካክላለሁ በሚል ያዘጋጀውን መጠይቅ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለሚዲያዎችና ለአከፋፋዮች በማስሞላት ላይ ሲሆን ዋና አላማውም አንዳንድ ብቅ በማለት ላይ ያሉትን ነጻ ጋዜጦችን ለመቅጨት ያለመ ነው ተብሎአል፡፡ ከእንግሊዝ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄደው ጥናት መነሻ ” የጋዜጣና መጽሔት አከፋፋዮች ሕግና ስርዓትን ባልተከተለ መልክ ስርጭቱን በመያዝ መንግስት ...
Read More »በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የቤንዚን እጥረት ተከሰተ
ጥር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቤንዚንና የናፍጣ እጥረቱ በመላ አገሪቱ የተከሰተ ሲሆን በተለይም በአዲስ አበባ፣ በሶማሊ ክልል በጂጂጋ፣ ሀረርና ሌሎችም ከተሞች፣ በደቡብ ደግሞ በሃዋሳ ፣ ሆሳዕና ፣ ወላይታ ሶዶ እና ሚዛን አማን መከሰቱን የደረሰን ዜና ያመለክታል። በጅጅጋ ከሁለት ቀናት በሁዋላ ነዋሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት ሲጋፉ ታይቷል። ችግሩ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያዎች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸውና ነዳጁን ማከፋፈል በማቆማቸው የተፈጠረ ...
Read More »ሱዳንና ግብጽ ወታደራዊ ግንኙነታቸውን ለማጠንከር ተስማሙ
ጥር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግብጹ ወታደራዊ አዛዥ እና የአገሪቱ መሪ ማርሻል አብደል ፋታህ አል ሲሲ ከሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር አብደል ራሂም ሙሃመድ ሁሴን ጋር ወታደራዊ ግንኙነቱን ለማጠንከርና የጋራ ድንበሮቻቸውን ለመጠበቅ መስማማታቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል። ሚኒስትር ሁሴን ካይሮ በመሄድ የግብጹን ወታደራዊ መሪ ያገኙ ሲሆን፣ ሁለቱ አገራት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ የሱዳኑ ወታደራዊ አዛዥ እንደገለጹት ...
Read More »የቡራዩ ነዋሪዎች ፌደራል ፖሊስ ከአካባቢው እንዲወጣ እየጠየቁ ነው
ጥር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ልዩ ዞን በቡራዩ ከተማ ትናንት የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ የፌደራል ፖሊሶች በከተማዋ ወጣቶች ላይ የሚፈጽሙት ተደጋጋሚ ግድያ፣ የጸጥታ ስጋት ስለፈጠረብን አካባቢውን ለቆ ይውጣ በማለት መጠየቃቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል። የመንግስት ባለስልጣናት በበኩላቸው ገዳይ የፌደራል ፖሊሶችን ለፍርድ እናቀርባለን በማለት ህዝቡን ለማረጋጋት እየሞከሩ ነው። በህዝቡና በፌደራል ፖሊስ መካከል ግጭቱ የተነሳው ከትናንት ...
Read More »