.የኢሳት አማርኛ ዜና

የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በአቶ አለምነው መኮንን ንግግር ላይ መግለጫ ሳያወጣ ተጠናቀቀ

የካቲት ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ስብሰባውን በባህርዳር ከተማ ሲያካሂድ የሰነበተው የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ የንቅናቄው የጽህፈት ቤት ሀላፊ የአማራውን ህዝብ የዘለፉበትን ንግግር ያስተባብላል ተብሎ ቢጠበቅም፣ ምንም ሳይል ቀርቷል። ንቅናቄው ” ህዝቡ በተቃዋሚዎችና ተባባሪዎቻቸው የሚነዙ አሉባልታዎችን ወደ ጎን በማለት ከብአዴን ጎን ጎን እንዲሰለፍ” የሚል መግለጫ በማውጣት ስብሰባውን አጠናቋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የጠየቅነው አንድ የብአዴን አባል፣ አቶ አለምነው ቀድሞውንም የተናገረው  ...

Read More »

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት አያያዝ አብጠለጠለ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መስሪያ ቤቱ በ2013 ሪፖርቱ በአገሪቱ የሚታዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በዝርዝር አስቀምጧል። በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታዩት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መካከል ሃሳብን በነጻነት የመግልጽና የመደራጀት መብት ቀዳሚ መሆኑን ሪፖርቱ ይገልጻል። ዜጎች በዘፈቀደ ይታሰራሉ፣ ይታፈናሉ፣ በእስር ቤት ይሰቃያሉ፣ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ይገደላሉ፣ በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት ማስፈራሪያ ይደርስባቸዋል እንዲሁም በእስር ቤት ውስጥ አሰቃቂ ድርጊቶች ይፈጸሙባቸዋል። ፍርድ ቤቶች ...

Read More »

በስዊዘርላንድ እና በኖርዌይ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን የሚደግፉ ሰልፎች ተካሄዱ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊዘርላንድ በርን ከተማ በተካሄደው ተቃውሞ በርካታ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር መንግድ ንበረት የሆነ አውሮፓላን በመጥለፍ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ ያሳረፈው ሃይለመድህን አበራ አፋጠኝ ፍትህ እንዲያገኝ ጠይቀዋል። “ሃይለመድህን ወንጀለኛ አይደለም፣ ወንጀለኛው የኢትዮጵያ መንግስት ነው፣ አሸባሪው ወያኔ ነው፣ ህዝቡን አግቶ የያዘው የኢትዮጵያው አሸባሪ መንግስት ነው፣ ዲሞክራሲና ፍትህ ለኢትዮጵያ” የሚለዩና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል። በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲና ...

Read More »

ሱዳንና ኢትዮጵያ በድንበር አካባቢ የጋራ ጥምር ሃይል ለማቋቋም ተስማሙ

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሱዳን የመከላከያ ሚኒስትር አብዱል ራሂም ሙሀመድ እንዳሉት ሁለቱ አገራት ከየመከላከያ ሰራዊታቸው የተውጣጡ ጥምር ሃይል በማቋቋም በድንበሮች ላይ አሰሳ ማድረግ ይጀምራሉ። ሚኒስትሩ በሁለቱ መንግስታት መካከል የሚደረገው ተከታታይ ውይይት እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ አድርጓቸዋል። ስምምነቱን  በኢትዮጵያ በኩል  የመከላከያ ሚኒሰትር ሲራጅ ፈርጌሳ ፈርመዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በርካታ የአገሪቱ ዜጎች የትጥቅ ትግል ለማድረግ የሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚዎችን ለመቀላቀል በሱዳን ...

Read More »

የዩጋንዳ መንግስት ግብረ-ሰዶማዊነትን ለመከላከል ያወጣውን ህግ በመቃወም ምእራባዊያን አገራት እርምጃ እየወሰዱ ነው

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕ/ት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ግብረሰዶማዊነትን ለመከላከል ያወጡት ህግ በርካታ የምእራብ አገራትን ያስቆታ ሲሆን፣ በብዙ የአፍሪካ አገራት ደግሞ ድጋፍ ተችሮአቸዋል። የምእራብ አገራት በሚወስዱት የተቀነባበረ እርምጃ ኖርዌይና ዴንማርክ ለመንግስት በቀጥታ የሚሰጡትን ድጋፍ ሲያቋርጡ፣ የአለም ባንክ ደግሞ ለአገሪቱ የሚሰጠውን የ90 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ አግዷል። የደቡብ አፍሪካው ነጻነት ታጋይ ዴዝሞንድ ቱቱ የኡጋንዳን መንግስት ድርጊት ሲያወግዙ፣ የአሜሪካው ...

Read More »

ሩሲያ የዩክሬን ግዛት የሆነቸውን ክሪሚያን ወረረች

የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩክሬን የተካሄደውን ተቃውሞ ተከትሎ አዲስ መንግስት መመስረቱ ያስቆጣት ሩስያ ክሪሚያ የምትባለውን የዩክሬን  ግዛት አውሮፕላን ማረፊያን በማቆጣጠር ተጽእኖ ለመፍጠር እየሞከች ነው። በክሪሚያ ግዛት 60 በመቶ የሚሆኑት ሩስያውያን ሲሆን፣ ሩሲያ ዜጎቿ ከጥቃት ለመከላከል በማሰብ የወሰደችው እርምጃ መሆኑን ትናገራለች። የምእራባዊያን አገራትና ጊዜያዊው የዩክሬን መንግስት የሩሲያን እርምጃ ግልጽ ወረራ በማለት አውግዘውታል። የሩሲያው መሪ ቭላድሜር ፑቲን ...

Read More »

አቶ አለማየሁ አቶምሳ ከክልሉ ፕሬዚዳንትነትና ከኦሀዴድ ሊቀመንበርነት ለመልቀቅ ደብዳቤ እንዳሰገቡ ተደርጎ በክልሉ መንግስት የተሰጠው መግለጫ ሃሰት ነው ተባለ

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር በክልሉ ፕሬዚዳንት በአቶ አለማየሁ አቶምሳ ቢሮ ውስጥ የተፈጠረውን ጉዳይ በዝርዝር ለኢሳት አስረድተዋል። አቶ አለማየሁ ከኦህዴድ ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር የካቲት 10 ቀን፣ 2006 ዓም በክልሉ ውስጥ ስለሚታየው የመልካም አስተዳደር መበላሸትና የህዝብ ሮሮ፣ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመጣው ሙስና እንዲሁም በድርጅቱ ጎጠኛ አሰራር ዙሪያ እርሳቸውን ከሚቃወሙዋቸው ሌሎች ...

Read More »

ኢህአዴግ የሚያካሂደው የቤት ልማት ለኪራይ ሰብሳቢነት መጋለጡን አመነ

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት 10 ዓመታት ሲካሄደው የቆየውና የቤት ልማት ፕሮግራሙ ለኪራይ ሰብሳቢነትና ብልሹ አሰራሮች የተጋለጠ እንደነበር ኢህአዴግ “አዲስ ራዕይ” በተሰኘ ልሳኑ አምኗል፡፡አዲስ ራዕይ በህዳር – ታህሳስ 2006 ዕትም “የመኖሪያ ቤት ፖሊሲያችንና ለዜጎች የሀብት ክፍፍል ፋይዳው” በሚል ርእስ ባሰፈረው ሐተታ “እስከአሁን በነበረው የቤት ልማታችን ሂደት የተፈጠሩ ክፍተቶች አሉ” ብሏል፡፡ ክፍተቶቹን ሲዘረዝርም “በክልል ከተሞቻችን ቀደም ሲል ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ ተቃውሞውን በሁሉም የአገሪቱ ክፍል እንደሚያቀጣጥል ገለጸ

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፣ የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) በባህርዳር ለታየው ህዝባዊ ተቃውሞ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ባለመሆኑ ተቃውሞውን በሌሎች የአገሪቱ ክልሎች ለመቀጠል ፍላጎት ያለው መሆኑን አመልክቷል። አቶ አለምነው መኮንንን በፍርድ አደባባይ ለማቆም በአጭር ጊዜ ውስጥ ክስ መስርቶ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል። አቶ አለምነው በአማራው ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ጸያፍ ስድብ ተከትሎ በባህርዳር ልዩ የተባለ ...

Read More »

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው የውጭ ምንዛሬ እጥረት እልባት አላገኘም

የካቲት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአስመጭና ላኪ እንዲሁም በግንባታ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች እንደሚገልጹት፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ የአገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ በእጅጉ እየተጎዳ ነው። ምንም እንኳ መንግስት የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዳላጋጠመ በተደጋጋሚ ቢገልጽም፣ በርካታ ነጋዴዎች ወደ ባንኮች ሲሄዱ፣ የሚፈልጉትን መጠን የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት አይችሉም። ከባንኮቹ የሚሰጣቸው መልስ ምንዛሬ የለም የሚል መሆኑን አንዳንድ ነጋዴዎች እንደሚናገሩ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ...

Read More »