.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢሳትየድጋፍኮሚቴበኖርዌይየባንክሒሳብቁጥርከፈተ

ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳትኖርዌይየድጋፍኮሚቴ፤በኦስሎናበተለያዩአካባቢዎችኢሳትን  ለማጠናከርናየአቅማቸውንለማበርከትለሚተጉየኢሳትደጋፊዎችናቤተሰቦች፤በያሉበትቀላልእናአመቺየሆነውንየአከፋፈልመንገድይጠቀሙዘንድበማሰብ፤በኖርዌይኦስሎበኢሳትስም  የባንክሒሳብቁጥርመክፈቱንበደስታገልጿል። በተለያየምክንያትየባንክሒሳብቁጥራችንለመጠቀምሁኔታዎችየማያመቿችሁየኢሳትደጋፊዎችለዚሁበተዘጋጁየገነዘብመቀበያደረሰኞችበመጠቀምኢሳትንበመደገፍለድምፅአልባወገንዎድምፅ እንዲሆኑ ኮሚቴው አስታውቋል። የሂሳብ ቁጥሩን በድረገጻችን የምታገኙት መሆኑን ለማስታወቅ እንወዳለን። የባንክ ሒሳብ ቁጥር DNB 1503 462 8537 Oslo Norway ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ ፦ 452 06 390 / 947 11 734  ይደውሉ ። የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ በኖርዌይ

Read More »

በአፋር የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ 8 ሰዎች በፌደራል ፖሊሶች ተገደሉ

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁርቁራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በአፋር እና በሶማሊ ጎሳ አባላት መካከል የተነሳውን ውዝግብ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ በወሰደው እርምጃ 8 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ሰዎች እና የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሲገልጽ ፣ አፋር ህዝብ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ ደግሞ የሟቾቹን ቁጥር 12 አድርሶታል። የፌደራል ፖሊስ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በአዋሽ ሰባት ኪሎ አካባቢ ህዝቡ ወደ ወደ አውራ ...

Read More »

በአዊ ዞን የሚገኙ የመኢአድ አባላት ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ያነጋገራቸው በአዊ ዞን የሚኖሩ የመኢአድ አባላት እንደተናገሩት የመንግስት ታጣቂዎች ኢህአዴግ አባላት ለመሆን ፈቃደኛያልሆኑ የፓርቲውን አባላት እያሳደዱና ድብደባ እየፈጸሙባቸው ነው። አቶ ዘሪሁን ባንቲሁን የተባለው አርሶ አደር ለኢሳት እንደገለጹት ሁለት መለዮ የለበሱ ታጣቂዎች ምሽት ላይ ቤታቸውን አስከፍተው በፈጸሙባቸው ድበደባ ለከፍተኛ አካል ጉዳት ተዳርገዋል። ሌሎች የመኢአድ አባላትም እንዲሁ የገዢው ፓርቲ አባላት ካልሆናችሁ በሚል ተመሳሳይ ...

Read More »

የስቀለት በአል እየተከበረ ነው

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክርስቶስ እየሱስን ስቅለት ለመዘከር በየአመቱ የሚከበረው የስቅለት በአል ዘንድሮም በጾምና በጸሎት እየተከበረ ነው። የኢሳት ዘጋቢ ያነጋገራቸው አንዳንድ ምእመናን በጾም በጸሎትና ስግደታቸው ወቅት እግዚአብሄር ኢትዮጵያን እንዲጎበኝ መለመናቸውን ተናግረዋል። “በአገራችን ችጋር ጠፍቶ ሁሉም በደስታ እንዲኖር እመኛለሁ” የምትለው አንዲት የ19 ዓመት ወጣት፣ የዘንድሮው የፋሲካ በአል ለሁሉም ደስታን ይዞ እንዲመጣ ተመኝታለች። ከጾም ጸሎት በተጨማሪ የታመሙትን በመጠየቅ ...

Read More »

በጭልጋ የተነሳው ተቃውሞ ሊያገረሽ እንደሚችል ተማሪዎች አስጠነቀቁ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት ቀናት ከቅማንት ህዝብ የማንነት እና የአስተዳደር ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬ ጋብ ብሎ የዋለ ቢሆንም፣ መንግስት ያሰራቸውን የብሄረሰቡን ወኪሎችና መምህራኖችን የማይፈታ ከሆነ፣ ነገ ቅዳሜ በድጋሜ  ተቃውሞ እንደሚያስነሱ ተማሪዎች አስጠንቅቀዋል። የወረዳው ባለስልጣናት በበኩላቸው ቀሳውስቱንና አገር ሽማግሌዎችን በመያዝ ከተማሪዎች ጋር ለመነጋገር የሽምግልና ጥረት ጀምረዋል። የልዩ ሃይል የፖሊስ አባላት ዛሬም ድረስ በአይከል ...

Read More »

ሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤት ከህዝብ አግለልጋይነቱ ወጥቶ የፓርቲ ስራ ማሰፈፀሚያ እየሆነ ነው ተባለ፡፡

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በሚመራው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ ውይይት ሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤት ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ፣ ለህዝብ ተቋማት እና የመንግስት ቢሮዎች የአሰራር ስርዓቱ ውጤታማና  ቀልጣፋ እንዲሆኑ ከማገዝ ይልቅ በፖለቲካ አሰተሳሰብ እና የፓርቲ ስራዎችን በመስራት የተጠመደ በመሆኑ በርካታ የሲቪል ሰርቪስ ስራዎች ሳይሰሩ እንደሚቀሩ ተመልክቷል፡፡ ተገልጋዮች በአግልግሎት እጦት እየተማረሩ እና እየተሰቃዩ መሆናቸውን እየገለጹ መሆኑን ...

Read More »

በአማራ ብሄር ላይ እየደረሰ ያለው በደል ኢትዮጵያዊነታችንን እየተፈታተነ ነው ሲሉ የአገር ሽማግሊዎች ገለጹ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በክልሉ ነዋሪዎች ላይ የፈጠረው ጥላቻ እና እየወሰደ ያለው እርምጃ የኢትዩጵያዊ ማንነታቸውን እየተፈታተነው እንደመጣ የክልሉ የሀገር ሺማግሌዎች ለመስተዳድሩ ባለስልጣናት አቤቱታ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡ የአገር ሽማግሌዎቹ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ባስገቡት ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው በቅርቡ በባህር ዳር ከተማ በህገወጥ መንገድ ተገነቡ የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ በተወሰደ እርምጃ አራት ንፁሃን ዜጎች መገደላቸው አሳፋሪ መሆኑን ጠቅሰዋል። ...

Read More »

የአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ እናቶችን እና ለጋ አራሶችን ጤና ለማሻሻል 40 ሚልዮን ዩሮ ለገሰ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአውሮፓ ኅብረት “በኢትዮጵያ በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች የማዋለድ አገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት በሚሰኘው ፕሮጀክት በኩል ለፌደራል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የ40 ሚልዮን ዩሮ ልገሳ ማበርከቱን አስታውቋል፡፡ ከአውሮፓ ኅብረት የተበረከተው አዲሱ ልገሳ በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ የእናቶችን ጤና እና የለጋ አራሶችን ክብካቤ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ይውላል፡፡ ከዚህ ልገሳ ውስጥ፤ 20 ሚልዮን ዩሮ ያህሉ ለፌደራል የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በተመድ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ደጋፊዎች ሳይሆኑ አይቀርም የተባሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች መጠለያ ግቢ ውስጥ በሰነዘሩት ጥቃት ከ30 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውን ዘገባዎች አመልክተዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዚህ በሁዋላ ጥቃት ቢፈጸም አጸፋዊ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል። በአገሪቱ የሚታየው ጦርነት ወደ ጎሳ ግጭት ያመራል ተብሎ እየተፈራ ነው። ፕ/ት ሳልቫኪር በአዲስ አበባ ጉብኝት በማድረግ የሰላም ...

Read More »

በጭልጋ ወረዳ ተማሪዎች ባስነሱት ተቃውሞ ጉዳት መደርሱ ተሰማ

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ጎንደር ዞን በጭልጋ ወረዳ በአይከል ከተማ ከቅማንት ብሄረሰብ የማንነትና የአስተዳደር ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳ የተማሪዎች ተቃውሞ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች በአድማ በታኝ ፖሊሶች ተደብድበው ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ወደ አካባቢው ሄዶ የተለያዩ መጠይቆችን በማድረግ በብሄረሰቡ ለቀረበው ጥያቄ መልስ ይሰጣል ተብሎ እየተጠበቀ ባለበት ወቅት ችግሩ መነሳቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ፌዴሬሽኑ ...

Read More »