ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናንት በስቲያ ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጭ ከጧቱ 1 ሰአት ተኩል ላይ ወደ ቢሮአቸው በመግባት ራሳቸውን ከ2ኛ ፎቅ ወርውረው የገደሉት የ62 አመቱ ዲፕሎማት አቶ ፍሰሃ ተስፉ ስለ አሟሟታቸው መንስኤ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም። ክሮናካ ዲ ሮማ የተባለው የጣሊያን ጋዜጣ ዛሬ ይዞት በወጣው ሰፊ ዘገባ ዲፕሎማቱ ከመሞታቸው ከሁለት ቀናት በፊት ከስራ ተነስተው ወደ አገራቸው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ ተስርተዋል የተባሉ ቤቶችን የማፍረስ ሂደቱ እንደቀጠለ ነው
ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት መንግስት በህወገወጥ መንገድ ተስረተዋል ያላቸውን ቤቶች ያለምንም ተተኪ ቦታና ቤት በማፍረሱ በርካታ ቤተሰቦች ሜዳ ላይ እየተበተኑ ነው። ኮልፌ አካባቢ አንፎ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው ሰፈር ከ2 ሺ እስከ 3 ሺ ቤቶች መፍረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚኖሩ ከ570 በላይ ቤቶች ይፈርሳሉ በመባሉ ነዋሪዎች አቤቱታዎችን ...
Read More »ደብረ ብርሃን በአንበጣ መንጋ መወረሩዋ ታወቀ
ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በደብረብርሃን ከተማ መታየቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአንበጣ መንጋው በአካባቢው ባለ እጽዋት ላይ ያደረሰው ጉዳት ይኑር አይኑር በውል አልታወቀም።
Read More »በደቡብ ሱዳን ለተከሰተው ረሃብ የገንዘብ ድጋፍ እየተሰባሰበ ነው
ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና በተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር መካከል የተጀመረው ጦርነት ከ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ለረሃብ ማጋለጡን ተከትሎ በኖርዌይ በተካሄደው የእርዳታ ማሰባሰብ ስራ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ተገኝቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ችግሩን ለመቅረፍ ከ1 ቢሊዮን 800 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ እየገለጸ ነው። በርካታ ገበሬዎች በጦርነት የተነሳ ማረስ እንዳልቻሉ እና የረሃቡም መንስኤ ጦርነቱ መሆኑን ...
Read More »የሶማሊ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ወሬዎች እየተናፈሱ ነው
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦህዴድ -ህወሃት እንደተቀነባበረ በሚነገርለት አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ የሶማሊ ክልል ተወላጅ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ያለመ መሆኑን ለኢሳት ደረሰው መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ካድሬዎች ” የሶማሊ ተማሪዎች ከመንግስት ጎን ቆመው በኦሮሞ ተማሪዎች ዙሪያ መረጃ እየሰጡን ነው” የሚል አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መነዛቱ፣ የሶማሊ ተማሪዎችን ስጋት ላይ የጣላቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ከመንግስት ጎን ...
Read More »በጣሊያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለስልጣን መሞታቸው ታወቀ
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአባታቸው ስም ለጊዜው ያልታወቀውና በተጠባባቂ አምባሳደር ማእረግ ደረጃ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ፍስሃ ጧት ስራ ከገቡ በሁዋላ መሞታቸው ታውቋል። ኢሳት ስለ አሟሟታቸው ዝርዝር መረጃ ባያገኝም አንዳንድ ጣሊያን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግለሰቡ የሞቱት ከ3ኛ ፎቅ ላይ ራሳቸውን ወርውረው ነው ይላሉ። ፖሊስ ወደ አካባቢው ደርሶ ምርመራ ካደረገ በሁዋላ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንና መሞታቸውን ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል። ...
Read More »በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቀው የኢትዮጵያ መንግሥት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በአብዛኛዎቹ ዘርፎች እንደማይሳካ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡
ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ2003 እስከ 2007 ዓ.ም ሊከናወን የታቀደው የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከፋይናንስ አቅም ፣ከሰለጠነ የሰው ኃይል እና ከመሠረተ ልማት አለመሟላትና ከመሳሰሉ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ፈተናዎች ገጥመውታል፡፡ በዕቅዱ ዓመታት 11 በመቶና ከዚያ በላይ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የታሰበ ቢሆንም ባለፉት ሶስት የዕቅዱ ዓመታት የተመዘገበው እድገት 10 በመቶ ብቻ ነው፡፡ ከኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ አንጻር በሚጠበቀው አቅጣጫ እና በጎላ መልኩ ...
Read More »በቡራዩ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር አሁንም በርካታ ወጣቶች ታስረው እንደሚገኙ ታወቀ
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ አዲሱ ካርታ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በቡራዩ ከታሰሩት ከ200 በላይ ወጣቶች መካከል ከ40 በላይ የሚሆኑት አሁንም ታስረው ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን የእስር ቤት ምንጮች ገልጸዋል። አብዛኞቹ በ25 ሺ ብር ዋስ ወይም በቦታ ካርታ እንዲፈቱ ቢደረግም ገንዘብ መክፈል ያልቻሉትና ከኦነግ ጋር ግንኙነት ያላቸው ተብለው የተጠረጠሩት እንዳይፈቱ ተደርጓል። እስረኞቹ ፍርድ ቤት ...
Read More »አንድነት በዝዋይ እስር ቤት የሚደርሰውን ህገወጥ ድርጊት አወገዘ
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ባወጣው መግለጫ በዝዋይ በፖለቲካ እስረኞችና ጋዜጠኞች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሚፈፀምባቸው ለመረዳት መቻሉን ገልጿል። የእስረኞች ቤተሰቦች ለጥየቃ በሚሄዱበት ጊዜ መጎብኘት እንደማይችሉና ይዘውት የሄዱትን ምግብ ይዘውት ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ፓርቲው በመግለጫው ጠቅሷል። “እስረኞቹ የሚፈፀምባቸውን በደል ለማሳወቅ ለ3 ቀናት የሚቆይ የርሃብ አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ የዝዋይ ማረሚያ ቤት ...
Read More »በአዲስ አበባ ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ሰዎች ብሶታቸውን እየገለጹ ነው
ግንቦት ፲፪ (አስራ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እንደ አዲስ ተጠናክሮ በቀጠለው በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉትን ቤት የማፍረስ ዘመቻ በርካታ ነዋሪዎችን ሜዳ ላይ እየበተነ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። አለም ባንክ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በርካታ ነዋሪዎች ባልተጠበቁት ሰአት ቤታቸው እንዲፈርስ በመደረጉ ነፍሰጡሮች ሳይቀር ለከፍተኛ ችግር ተደርገው ነበር። የመንግስትን ድርጊት የተቃወሙትም እንዲሁ እየተደበደቡ አንዳንዶች እንዲታሰሩ ተደርጓል። ዛሬ ማክሰኞ ሰሚት እየተባለ ...
Read More »