.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሃረር በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች መቃብር መገኘቱን ተከትሎ ግጭት ተነሳ

ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀበሌ 19 ልዩ ስሙ ሃመሬሳ ወይም መድፈኛ ጀርባ በሚባለው አካባቢ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓም በቁፋሮ ላይ የነበረ አንድ የግሪደር ሹፌር የተከማቹ አስከሬኖችን አግኝቷል። የ2ቱ አስከሬን ምንም አይነት የመበስበስ ምልክት አለማሳየቱን የገለጸው ወኪላችን፣ ግለሰቦቹ በቅርቡ የተገደሉ መሆናቸውን ያሳያል ብሎአል። አንደኛው ሟች እጆጁን ወደ ሁዋላ ለፊጥኝ ታስሮ የተገኘ ሲሆን ሌላው ደግሞ አይኖቹ በጨርቅ ተሸፍነዋል። የአራት ...

Read More »

በዲላ በግብር የተማረሩ ነጋዴዎች ስራ አቆሙ

ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በበግምብ ገበያ አዳራሽ ውስጥ በጨርቃጨርቅ  የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ከ100 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ስራ ያቆሙት ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ግብር እንድንከፍል ተጠይቀናል በሚል ምክንያት ነው። ነጋዴዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከደረጃ ሐ ወደ ደረጃ ለ እንዲሸጋገሩ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት እንዲከፍሉ መታዘዛቸውን ለመቃወም ነጋዴዎቹ ወደ አዋሳ አምርተዋል። የክልሉ ባለስልጣናት ለነጋዴዎቹ ጥያቄ የሰጡት መልስ አልታወቀም። ...

Read More »

በአዳማ በርካታ የንግድ ማስታወቂያዎች የአጻጻፍ መመሪያ አልተከተሉም በሚል ተሰረዙ

ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮምያ ክልል መስተዳድር የክልሉን የማስታወቂያ አጻጻፍ መመሪያ አልተከተሉም ያላቸውን የበርካታ ድርጅቶች ማስታወቂያዎች መሰረዙ ታውቋል። የንግድ ማስታወቂያቸውን በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ የጻፉ የንግድ ድርጅቶች ማስታወቂያቸውን እንዲለውጡና በኦሮምኛ እንዲጽፉ ሲታዘዙ ፣ ከማስታወቂያ ሰሌዳው ላይ በተጨማሪ ቋንቋ ለመጻፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ደግሞ  በኦሮምኛ የተጻፈውን በጉልህ ሁኔታ ከላይ ካስቀመጡ በሁዋላ በተጨማሪ ቋንቋ የተጻፈውን በትንሹ ከታች እንዲያስቀምጡ ታዘዋል። የመስተዳድሩ ባለስልጣናት በአማርኛ ...

Read More »

በሚቀጥለው የበጀት አመት የ21 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንደሚኖር ተገለጸ

ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 30/2006 በሚጠናቀቀውየዘንድሮውበጀትዓመትከተያዘው 155 ነጥብ 9 ቢሊየንብር  ውስጥ 16 ነጥብ 6 ቢሊየንብርየበጀትጉድለትየነበረሲሆን፣  በ2007 የበጀት ጉድለቱ አድጎ 21 ነጥብ 2 ቢሊየን ብርእንደሚደርስ ታውቋል። ከ2007 አጠቃላይበጀትማለትም 178 ቢሊየን 565 ሚሊየን 906 ሺህ 571 ብርውስጥከሃገርውስጥ፣ከውጭአገርዕርዳታናብድርበድምሩብር 157 ቢሊየን 357 ሚሊየን 947 ሺህ 657 ያህልገንዘብለመደጎምየታቀደመሆኑንምየገንዘብናኢኮኖሚልማትሚኒስትሩአቶሶፊያንአህመድለፓርላማው  ካቀረቡትሪፖርትለመረዳትይቻላል፡፡ የቀጣዩዓመትበጀትውስጥ 34 ቢሊየን 304 ሚሊየን 872 ሺህ 764 ብርበብድርናዕርዳታማለትም 17 ነጥብ 5 ቢሊየንብርበብድር፣ ...

Read More »

ቴዎድሮስ አድሃኖም አል ሲሲ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ጠየቁ

ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአባይ ግድብ ጋር ተያይዞ በአገር ውስጥ ግብጽን የማጥላላቱ ዘመቻ በስፋት የቀጠለ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለአዲሱ የግብጽ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ የጉብኝት ጥያቄ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ግብጽን የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ሲገልጹ፣ አል ሲሲም ከኢትዮጵያ ጋር የመተባባር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የፖሊቲካ ተቃዋሚዎችን ከግብጽ ጋር ይሰራሉ በማለት በመገናኛ ...

Read More »

የሰኔ 1 ሰማእታት በሀገር ቤት እና በውጪ ሀገራት በልዩ ስነ-ስርዓት ታስበው ዋሉ።

ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ምርጫ 97ትን ተከትሎ  የዛሬ 9 ዓመት  ሰኔ  1 ቀን  በግፍ የተጨፈጨፉ ሰማእታት ኢትዮጵያን ጨምሮ  በበርካታ የውጪ ሀገራት  በልዩ ልዩ ፕሮግራም  ተዘክረዋል። በኢትዮጰያ ሰማያዊ ፓርቲ፣አንድነት ፓርቲ እና መኢአድ ሰማእታቱን በተለያዩ ፕሮግራሞች አስበው የዋሉ ሲሆን፣ በተለያዩ የአውሮፓ እና አሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጰያውያንም  በደማቅ ስነ-ስርዓቶች መታሰቢያ አድርገውላቸዋል። ሰማያዊ ፓርቲ ባሰናዳው መታስቢያ ፐሮግራም ላይ የተገኙት ፐሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፦ ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ተሸለመ

ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ2014 “የጎልደን ፔን ኦፍ ፍሪደም” ሽልማት አሸናፊ የሆነው እስክንድርነጋ ዛሬ ሽልማቱን ተቀበለ። በጣሊያን ቶሪኖ በተካሄደው የሽልማት ስነ-ስር ዓት  ላይ  እስክንድርን ወክሎ ሽልማቱን የተቀበለው በቃሊቲእስርላይየነበረው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ ነው። “ምኞቴ ይህን ሽልማት እኔ እንድቀበለው አልነበረም” በማለት ንግግሩን የጀመረው ማርቲን፣ “ዛሬ ጠዋት ስነሳ  ምናለ፦“ ተፈታሁኮ፤ ሽልማቱን እኔ ራሴ ልቀበል እመጣለሁ” የሚል ስልክ ከአዲስ አበባ በስልክ ብሰማ ...

Read More »

አንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በደብረማርቆስ እና በአዳማ ከተሞች  ደማቅ ሰልፎችን አድረገ።

ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት!” በሚል መሪ ሀሳብ ትናንት እሁድ በሁለቱ ከተሞች ባደረጋቸው ሰልፎች በሺህዎች የሚቆጠሩ የየከተሞቹ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት የ ኢህ አዴግ መንግስት እየፈጸማቸው ናቸው ባሉዋቸው ሀገራዊና አስተዳደራዊ በደሎችዙሪያ የተቃወሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ከብ መንግስታዊ ቢሮከራሲዎች እና እልህ አስጨራሽ ወጣ ውረዶች በሁዋላ በተደረጉት ሰልፎች በተለይም መሬት የመንግስት የፖለቲካ መሳሪያ መሆኑ እንዲያከትም እና ገበሬው የመሬት ...

Read More »

በፓኪስታን- ካራች አውሮፕላን ማረፊያ ከባድ ጥቃት ተፈጸመ።

ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንደ ቢቢሲ ሪፖርት፤በሀገሪቱ ታላቅ አውሮፐላን እሀድ እለት በተከፍተው ጥቃት አስር የጥበቃ  ሰራተኞችን ጨምሮ  በትኝሹ 28 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፤ የታሊባን አማጺዎች ለጥቃቱ ሀላፊነቱን ወስደዋል። ጥቃቱ የተጀመረው እሁድ ማምሻው ላይ ለካርጎ ጭነት እና “ለቪ. አይ፣ፒ” በረራ በሚያገለግሉት የካራቺ  ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው ክፍሎች ላይ ነው። ሰኞ ማለዳ በአውሮፐላን ማረፊያው አዲስ የተኩስ ልውውጥ መሰማቱን ተከትሎ  የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሰጡት ...

Read More »

በአዲስ አበባ የህዝብ መፈናቀል እንደሚቀጥል መረጃዎች አመለከቱ

ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ማደስና ፕላን ዝግጅት በሚባለው ፕሮግራሙ በመሃል አዲስ አበባ የሚገኙ ኪስ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን በስፋት እንደሚያፈናቅል የሚነገርለትን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የአስተዳደሩ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ አካባቢን መልሶ የማልማት ገጽታ አለው በሚባለው ሥራ ውስጥ ዘንድሮ ከተካተቱ አካባቢዎች መካከል በካዛንቺስ 26 ሄክታር፣በደጃችውቤ 11.6 ሄክታር፤በሸበሌሆቴልዙሪያ 10.4 ሄክታር፣አሜሪካንግቢ 16 ሄክታር፣በአፍሪካህብረትቁጥር 2 ወደ 15 ...

Read More »