.የኢሳት አማርኛ ዜና

በሃረር ከፍተኛ የውሃ እና የምግብ ዘይት ችግር ተከሰተ

ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን ከስፍራው እንደዘገበው በከተማዋ በተለይም ቀበሌ 14፣ 15፣ 16፣ 17፣ 18 እና 19 እንዲሁም በሸንኮራ፣ ጀጎልና ቀለዳምባ አካባቢዎች ከፍተኛ የውሃ እጥረት በመከሰቱ ህዝቡ የጀኔሪካን ውሃ በውድ ዋጋ ለመግዛት ተገዷል። የክልሉ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት ከሃረር በ75 ኪሜ ርቀት ላይ አሰሊሶ  በሚባለው ቦታ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ካስቆፈራቸው 17 ...

Read More »

በ10 እስር ቤቶች የተከሰተው ኩፍኝ 9 ሰዎችን ገደለ

ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁጥራቸው ከ4000 በላይ በሚገመት ታራሚዎች ላይ የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ በአማራና በኦሮምያ ክልሎች 9 እስረኞች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። “መንግሰት የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ በቂ የማረሚያቤት ሰራተኛ የለኝም ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ፤ የህክምና አገልግሎት አይሰጥም” በሚሉ ሰበቦች  አደጋው እንዲባባስ እና ለእስረኞች ህይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑ መረጃው ያመለክታል። የኢትዩጵያ የቀይ መስቀል ቡድን በሁለቱ ክልሎች በሚገኙ 16 ...

Read More »

ፈንጅ አምካኝ ወታደሮች በብሄራችን የተነሳ አድሎ ተፈጽሞብናል ሲሉ ተናገሩ

ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዩ ኤርትራ  ጦርነት ወቅት ፈንጅ ያመክኑ የነበሩ  ወታደሮች እስከዛሬ ለከፈልነው መስዋትነት ከ3 እስከ 7 ሺ ብር ብቻ እየተሰጠ፣ ብሄራችን እየተመረጠ ከመከላከያ እንድንሰናበት ተደርገናል ብለዋል። ሰሞኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት  ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ተክለብርሃን ወ/ዓረጋይ ወደ አማራ፣ ኦሮምያና ደቡብ ክልሎች ተዘዋውረው ወታደሮችን ያነጋገሩ ሲሆን “ጊዜው ለልማት እና ለስራ የሚነሳሱበት እንጅ አድማ በመምታት ነገር የሚያሰሩበት ...

Read More »

ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌስ ቡክ ላይ የተለያዩ ጽሁፎችን በመጻፍ በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ደጋፊ ያገኙት ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩ ወጣት ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ባለፈው ቅዳሜ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም፣ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ማእከላዊ ተመልሰዋል። እጆቻቸውን በካቴናዎች የታሰሩት ወጣት ብእረኞች አካላዊ መጎሳቆል ቢታይባቸውም፣ መንፈሳቸው ግን ጠንካራ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል። መንግስት በፌስ ቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ የመገናኛ መንገዶች የሚሰራጩ ...

Read More »

በኬንያዋ የወደብ ከተማ በርካታ ሰዎች ተገደሉ

ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንደፈጸመው በተገመተው በዚህ ጥቃት 48 ሰዎች ተገድለዋል። የቱሪስት መዳረሻ በሆነቸው በላሙ ደሴት በደረሰው ጥቃት ሆቴሎችና መኪኖችም ተቃጥለዋል። ፖሊሶች ከታጣቂዎች ጋር ተኩስ መክፈታቸውን ተከትሎ ታጠቂዎች ወደ ጫካ ገብተው ማምለጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ የፖሊስና የደህንነት ተጠሪያቸውን በማስጠራት በቀጣይ ስለሚወስዱት እርምጃ መክረዋል። አልሸባብ በኬንያ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸመ ነው። ኬንያ ጦሩዋን ወደ ሶማሊያ አስገብታ ...

Read More »

በጎደሬ ወረዳ አካባቢ በምትገኘው ጻኑ  ግጭት ተቀሰቀሰ

ሰኔ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎደሬ ወረዳ አካባቢ በምትገኘው ጻኑ ሃሙስ  ሰኔ 5 ፣ 2006 ዓም  የተነሳው ግጭት ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የወረዳው ባለስልጣናት ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የሌሎች አካባቢ ተወላጆችን አካካቢውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዛቸውን የሚናገሩት ምንጮች፣ በረካታ ነዋሪዎች ተፈናቅለው በአሁኑ ጊዜ ቴፒ ከተማ ውስጥ ሰፍረው እንደሚገኙ ታውቋል። በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ ባይታወቅም አንድ ...

Read More »

የኢህአዴግን የልማት ስኬት እንዲመሰክሩ የተጠሩ ሰዎች ያልተጠበቁ ችግሮችን አነሱ

ሰኔ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው ምርጫ ለአሸናፊነት ያበቃኛል በማለት ኢህአዴግ በተለያዩ አካባቢዎች  የተመረጡ ሰዎች በአምስት አመታት ውስጥ ስለተሰሩ ስራዎች  እንዲመሰክሩ በማድረግ ላይ ቢሆንም፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ያልተጠበቁ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው። በደብረብርሃን ሰሞኑን ተካሂዶ በነበረው ውይይት ህዝቡ የተለያዩ የማህበራዊ አግልግሎት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን አንስቷል። ርዕሰ መምህር ከፈለኝ ዘውዴ እንደተናገሩት በከተማዋ ውስጥ ከ15 ሺ ያላነሱ ነዋሪዎች ለ7 ዓመታት መብራት ሳያገኙ ...

Read More »

አስገዳጁ የፋይናንስ አዋጅጸደቀ

ሰኔ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታክስንገቢን  የማሳደግ ዓላማ በመያዝ በመንግሥትና በግል ድርጅቶች በየዓመቱ ወጥ የሆነ የፋይናንስ ሪፖርት እንዲያቀርቡ የሚያስገድደውን ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው አጽድቆታል፡፡ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ አዋጅ በመባል የሚታወቀው ይህው አዋጅ ዓላማው የደርጅቶችን የፋይናንስ እንቅስቃሴ መረጃ ወጥነት ባለውና በተደራጀ መልኩ እንዲቀርብ ማስቻል ሲሆን እግረመንገድም መረጃዎቹ የታክስ ገቢን ለማሳደግ ያለመነው፡፡ ይህንለማስፈጸምም “የኢትዮጽያየሂሳብአያያዝናኦዲትቦርድ” የሚባልራሱንየቻለተቋምበሚኒስትሮችምክርቤትየሚቋቋምሲሆንቦርዱከፋይናንስሪፖርትጋርበተያያዘየመቆጣጠርናለኦዲተሮችፈቃድየመስጠትሥራዎችንያከናውናል፡፡በዚህአዋጅየተደነገገውንየተላለፈእስከብር 50ሺህወይንምበሶስትዓመታትእስራትእንደሚቀጣአዋጁደንግጓል፡፡ መንግሥትብዙውንጊዜበተለይልማታዊየሚላቸውየግልባለህብቶችናነጋዴዎችጭምርታክስናግብርንያጭበረብራሉበሚልበየጊዜውወቀሳይህአዋጀርእንዲህኣይነቱንተግባርእንደሚታደግእየተገለጸነው፡፡ባለፉትዓመታትአንዳንድገዥውንፓርቲየተጠጉነጋዴዎችታክስበመሰወርናበማጭበርበርከቀድሞዎቹገቢዎችናጉምሩክባለስልጣንከፍተኛኃላፊዎችጋርክስእንደቀረበባቸውየሚታወስነው፡፡

Read More »

የቅድመ ውህደት ስምምነቱ የቅንጅትን ህዝባዊ መንፈስ ይመልሳል ሲል አንድነት አስታወቀ

ሰኔ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ” ውህደታችንን በማጠናከር  የቅንጅትን ህዝባዊ መንፈስ ዳግም እንመልሳለን በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ሁለቱ ፓርቲዎች “ከጥልቅ ውይይት በኋላ ወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ የሚፈልገውን በመገንዘብ፤ የህዝቡን ጥያቄ መመለስ የሚችል የተባበረ የፖለቲካ ሃይል ለመፍጠርና የቅንጅትን ህዝባዊ መንፈስ ለመመለስ የሚያስችላቸው ደረጃ ላይ ” ደርሰዋል ብሎአል። ሁለቱ ፓርቲዎች ሰኔ 1 ቀን ለበርካታ ወራት በጋራ ሲሰሩበት የነበረውን የውህደት ስምምነት ከጫፍ ...

Read More »

በኢራቅ የሱኒ ሙስሊም ተከታዮች የተለያዩ ከተሞችን ያዙ

ሰኔ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አክራሪ የሚባሉት ታጣቂዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢራቅን ሁለተኛ ከተማ መቆጣጠራቸውን አለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። ታጣቂዎቹ ባግዳድን ለመያዝ እንቅስቃሴ ለመጀመር በሚሞክሩበት ሰአት አሜሪካ መንግስት ለኑር አልማለቂ መንግስት ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል። የሺአ እምነት ተከታዮች የሚበዙባት ኢራን ለአልማላቂ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ጦሩዋን ማስገባቱዋትም ተውቋል። በኢራቅ የሺአ የሃይማኖት መሪ የሆኑት አያቶላ አል ሲስታኒ የሺአ እምነት ተከታዮች ...

Read More »