ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመላ አገሪቱ የስልክ መልእክቶችን በመደወል ለአቶ አንዳርጋቸው ጀግንነት ድጋፋቸውን የሚገልጹ፣ በእርሱ መታሰር የኢትዮጵያ ህዝብ የተሰማውን ስሜት የሚገልጹና ስለቀጣዩ ህዝባዊ እርምጃ አስተያየቶችን የሚሰጡ በርካታ የስልክ መልእክቶች ለኢሳት እየደረሱ ነው። “እድሜየ 50ዎቹ አጋማሽ ነው፣ ከስራ ውየ ስገባ የሰማሁት ዜና አስደንግጦኛል፣ ስሜቴን መቆጣጠርም አልቻልኩም፣ ቤተሰቤን ልጆቼን ትቼ ትግሉን ለመቀላቀል ወስኛለሁ” በማለት የተናገሩት አንድ የመንግስት ሰራተኛ፣ የመን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች በአቶ አንዳርጋቸው መታገት ዙሪያ መግለጫ እያወጡ ነው
ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአፓ የየመን የጸጥታ ሃይሎች በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የወሰዱትን እርምጃ በጽኑ አውግዞ፣ የአገሪቱ መንግስት በአስቸኳይ እንዲለቀው ጠይቋል። አንዳርጋቸው በአምባገነኖች ፍርድ ቤት በሽብር ወንጀል ተከሶ ሞት የተፈረደበት በመሆኑ፣ ተላልፎ ቢሰጥ ለከፋ ስቃይና ሞት ሊዳረግ እንደሚችል አስጠንቅቋል። የአቶ አንዳርጋቸው መታሰር አደገኛ የሆነ አሰራር የሚፈጥር በመሆኑ ድርጊቱ በጽኑ ሊኮነን ይገባዋል ሲል ኢህአፓ አሳስቧል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ተነስቶ ...
Read More »በመላው አለም የሽብር ጥቃቶች ሊፈጸሙ ይችላል በሚል ጥበቃዎች ተጠናክረዋል
ሰኔ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአሜሪካ መንግስት ባወጣው መግለጫ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸው የሽብር ድርጅቶች ጥቃት ለመፈጸም በመዘጋጀት ላይ ለመሆናቸው አስተማማኝ መረጃ እንደደረሰው አመልክቷል። ይህን ተከትሎም በእንግሊዝ፣ በአሜሪካ እና በሌሎችም አገራት አየር መንገዶች ላይ የሚታየው ጥበቃ ተጠናክሯል”” ኡጋንዳም በአየር መንገዷ ላይ ሽብር ሊፈጸም ይችላል በሚል ከፍተኛ ጥበቃ እያደረገች ነው።
Read More »የአቶ አንዳርጋቸው እገታ ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ከየአቅጣጫው ቁጣቸውን እየገለጹ ነው
ሰኔ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን መንግስት የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ማገቱን ተከትሎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች ቁጣቸውን እየገለጹ ነው። አላማጣ አካባቢ የሚኖሩ አንድ አስተያየት ሰጪ ” የየመን መንግስት ያገተው አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ነው። በዚህ የቁርጥ ቀን ልጅ ላይ አንድ ነገር ቢደረግ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆ ብሎ ይነሳል። የመን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ...
Read More »በእስራኤል እና በፍልስጤሞች መካከል ያለው ውጥረት እንደጨመረ ነው
ሰኔ ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ታፍኖ የተወሰደ የፍልስጤም ወጣት መገደሉን ተከትሎ ፍልስጤማውያን ቁጣቸውን እየገለጹ ነው። የ17 አመቱ ወጣት ሙሃመድ አቡ ካድር በመኪና ታፍኖ ሲወሰድ የአይን ምስክሮች ማየታቸውን ተናግረዋል። ፍልስጤማውያን ከእስራኤል ፖሊሶች ጋር መጋጨታቸውን ተከትሎ የእስራኤሉ መሪ ቤንጃሚን ናታንያሁ ግድያውን አውግዘው፣ የእየሩሳሌም ከንቲባ የህዝቡን ቁጣ እንዲያበርዱ አሳስበዋል። የፍልስጤም መሪዎች በበኩላቸው እስራኤል 3 ወጣቶች መገደላቸውን ተከትሎ የወሰደችው የበቀል እርምጃ ...
Read More »ግንቦት7 አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለማስፈታት ጥረቱን መቀጠሉን አስታወቀ
ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንቅናቄው የስራ አስፈጻሚ አባልና የህዝባዊ እምቢተኝነት ዘርፍ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ የየመን የጸጥታ ሃይሎች አቶ አንዳርጋቸውን በአስቸኳይ ይለቁት ዘንድ ለአገሪቱ ፕሬዚዳንት ደብዳቤ ከመጻፍ ጀምሮ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፎችን እና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉበትን መንገድ እያመቻቹ ነው። ግንቦት7 ለየመን ፕሬዚዳንት ፊልድ ማርሻል አብዱ ራቡ ማንሱር ሃዲ እኤአ ሰኔ ...
Read More »የአቶ አንዳርጋቸውን ጽጌን በየመን መታፈን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ አስተያየቶችን እያሰጡ ነው
ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን የጸጥታ ሃይሎች የግንቦት7 ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸውን ማፈናቸውን ተከትሎ በፌስቡክ፣ በቲውቲርና በድረገጾች ላይ የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥተዋል። አክቲቪስት አበበ ገላው በበኩሉ የመንአቶአንዳርጋቸውጽጌንማገቷሌላአደገኛናበጣምአሳሳቢክስተትነው።የአንባገነኑየህወሃትስርወመንግስትተቃዋሚዎችንማንምአገርበምንምአይነትሁኔታማፈን፣ማሰርናማንገገላታትአለምአቀፍህግንየሚጥስህገወጥድርጊትነው።የመንአቶአንዳርጋቸውንለወያኔአሳልፋእንዳትሰጥናያለምንምቅድመሁኔታእንድትለቅሁሉምነጻነትናፋቂኢትዮጵያዊሁሉበጋራጥረትሊያደርግይገባል።የየመንኤምባሲዎችንበያሉበትበተቃውሞማጨናነቅናእንቅልፍመንሳትእንዲሁምአለምአቀፍጫናማድረግያስፈልጋል።ግዜሳይረፍድይህንንየቁርጥቀንኢትዮጵያዊለመታደግበያለንበትበጋራእንረባረብ።” ሲል ጥሪ አቅርቧል። ፕራይድ ዲ ባሰፈረው ጽሁፍ ደግሞ ” እውነተኛ ታጋይ ሊታሰር ሊሞት ይችላል፣ የተጀመረውን ትግል ግን ሊያስሩትም ሆነ ሊገሉት ከቶ አይቻላቸውም። ኢትዮጵያም አንድ አንዳርጋቸውን ብቻ ሳይሆን ሚሊዮን አንዳርጋቸውን ...
Read More »3 እስራኤላዊ ወጣቶች መገደላቸውን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ጨምሯል።
ሰኔ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሶስት የእስራኤል ወጣቶች ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ መገደላቸው እንደታወቀ የእስራኤል መንግስት ድርጊቱን በፈጸመው በሃማስ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ ማስታወቁዋን ተከትሎ በአካባቢው ያለው ውጥረት አይሏል። የአገሪቱ መሪ ጠ/ሚ ናትኒያሁ ” ወጣቶቹ በሰው እንስሶች ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ” ተገድለዋል ያሉ ሲሆን፣ በሃማስ ላይ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ዝተዋል። ይህን ተከትሎም ማምሻውን እስራኤል በሃማስ ወታደራዊ ተቋማት ላይ ከ30 ላላነሰ ...
Read More »በአዊ ዞን ነዋሪዎች በየጊዜው ቤት እንዲያፈርሱ መታዘዛቸው እንዳስመረራቸው ገለጹ`
ብአዴን ለመጪው ምርጫ ዝግጅት በሚል በተለያዩ የአማራ ክልሎች እያካሄደ ባለው ውይይት የአዊ ዞን ነጋዴዎችና ነዋሪዎች መንግስት በየጊዜው በሚያወጣው መመሪያ መሰላቸታቸውንና ቤት አፍርሱ በመባላቸው ለችግር መደረጋቸውን ገልጸዋል። በውጭአገራት ለረጅም አመታት ኖራ፣ በአነገሯ ኢንቨስት እንድታደርግ ተጠይቃ ወደ አገሯ የገባች ነዋሪ ፣ ወደ አገሯ ከመግባቱዋ በፊት ሲነገራት የነበረው ማግባቢያና ወደ አገሯ ከተመለሰች በሁዋላ በአካል ያየችው ነገር እንደተለያየባት ገልጻለች። ” በአገርሽ ላይ አትሰሪም በሉኝና ...
Read More »የዞን ዘጠኝ ጸሃፊዎች በድጋሜ ተቀጠሩ
በማህበራዊ ድረገጾች በመጻፍ የሚታወቁት የዞን ዘጠኝ አባላት እሁድ እለት ችሎት ቀርበው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል። ፖሊስ ምርመራየን አልጨረስኩም፣ ግብረአበሮቻቸውም አልተያዙም በሚል ሰበብ የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆ የ15 ቀናት ጊዜ ተፈቅዶለታል። አቤል ዋበላ፣ በፈቃዱ ሃይሉና ማህሌት ፋንታሁን የተባሉ ወጣት ጸሃፊዎች ለሀምሌ 7 ቀን 2006 ዓም ተቀጥረዋል። ችሎቱን ለመከታተል የሄደው ህዝብ ወደ ችሎት እንዳይገባ የተከለከለ ሲሆን ከጠበቃው ከአቶ ...
Read More »