.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌና ሌሎችም የታሰሩት ኢትዮጵያውያን እንዲፈቱ ጠየቁ

ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ ዛሬ በኖርዌይ የእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ የአቶ አንዳርጋቸውን ተላልፎ መሰጠት በእጅጉ አውግዘዋል። ከፍተኛ ቁጣ ባስተናገደው ተቃውሞ እንግሊዝ እየወሰደችው ያለው እርምጃ እንዲብራራላቸው ጠይቀዋል። በኖርዌይ  የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት  ፊት ለፊት ባደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ ደግሞ በቅርቡ ከደቡብ ሱዳን ተይዘው ለኢህአዴግ የደህንነት አባላት ተላልፈው የተሰጡትን የአቶ ኦኬሎ አኳይን ጉዳይ በማንሳት ኖርዌይ መልስ እንድትሰጣቸው ...

Read More »

“ግንቦት ሰባትን ለማዳከም የተወሰዱ እርምጃዎች ከፍተኛ ውጤት አስገኝተዋል” ሲል የፀረ ሺብር ግብረሃይል አስታወቀ፡፡

ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ እና እሁድ በጠቅላይ ሚኒስትር አዳራሽ  የጸረ ሽብር ግብረሃይሉና የኢህአዴግ ባለስልጣናት በጋራ የመከሩ ሲሆን፣ስኬታማ ስራዎችን ለመስራት  3 ሚልየን 400 ሺ ዶላር ወጭ ማድረጉን ገልጿል፡፡ “ኢሳያስ ቢያስፈልገን  እርሱን የመያዝ አቅም ላይነን” በማለትራሱን ያሞካሸውግብረሃይሉ ፣ “ኢህአዴግንግስት ንቧን በመያዙየቀጣዩምርጫድልበርላይይገኛል” ሲልበሪፖርቱ አትቷል። ከሁሉምክልሎችየደህንነትሃይሎችአመራሮችበተካፈሉበትውይይትበቀጣይከግንቦትሰባትሊፈፀምይችላልየተባሉ ስጋቶችም ተነስተዋል።  የመከላከያሃይሉልዩትዕዛዝተሰጥቶትየተዘናጋበትንክልልእንዲሸፍንናከፍተኛጥንቃቄእንዲወስድመመሪያእንዲሰጠው ተወስናል፡፡ “ግንቦትሰባትእስከጎንደርያለምንምእንከንቀድሞመግባትይችላል”የሚለው ሪፖርቱ፤የመከላከያሃይሉእናየደህንነትስራውየላላበመሆኑመጠናከርአለበትብሎአል። ይህንን ተከትሎም በተሰብሳቢዎች መካከል ከፍተኛ ክርክር ተካሂዷል። አንደኛው ወገን ...

Read More »

በአማራ ክልል አርሶ አደሮችን ትጥቅ የማስፈታት ሂደቱ ውጤታማ አይደለም ተባለ፡፡

ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስተዳደር ፀጥታ እና የፖሊስ ኮሚሺን በጋራ የ2006 ዓ.ምየ11 ወራት አፃፀም በገመገሙበት ውይይት የጎጃም ፤የጎንደር ፤የሺዋ እና የኦሮሞ አርሶ አደሮች  ዛሬምበድብቅመሳሪያዎችንበነፍስወከፍበየቤቱይዘው እንደሚገኙያወሱሲሆን፣ አርሶ አደሩ የጦር መሳሪያውን እንዲመልስጥረትቢደረግምአልተሳካምብለዋል፡፡ አዲስህግእንዲወጣየጠየቁትየፀጥታሃይሎች  በአርሶአደሩበህገወጥእጅየተሰገሰገውከ 4 ሚሊዩንበላይየሚገመትየተለያየየጦርመሳሪያ በአገሪቱ ለሚፈጸም ግድያ ዋና መንስኤ መሆኑን   አመልክተዋል፡፡ በዘመቻየጦርመሳሪያማስፈታትእናየቅጣትወሰንመመሪያእንደሃገርአለመኖርችግር  መሆኑንበማንሳትየፊደራል መንግስት የህገወጥመሳሪያቁጥጥርአዋጅእንዲያወጣበሪፖርታቸውጠይቀዋል፡፡ የፌድራልፖሊስ መረጃ እንደሚያመለክተው ከአማራ ክልል በመቀጠል አፋር እና ሶማሌ መሳሪያ ያላ ወረዱ ክልሎች ...

Read More »

አቶ ሽመልስ ከማል የሚመሩት ፕሬስ ድርጅት ደካማ ነው ተባለ

ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርላማ : ባህል ፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ቋሚ ኮምቴ ስብሳቢ 73ኛ የምስረታ ዓመቱን በቅርቡ ያከበረውን የኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅት በቁሙ እየሞተ መሆኑን በመጠቆም በራሱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይትችትአቀረቡ፡፡ የቋሚ ኮምቴው ስብሳቢ ወ/ሮ ፈቲያ ዩሱፍ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ዓርብ እና ቅዳሜ እለት በታተመ ቃለ ምልልሳቸው እንደተናገሩት የአዲስ ዘመን ፣ ኢትዮጵያ ሄራልድ ፣ በሬሳ ፣ ዓልኣለም ...

Read More »

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና የሌሎችም ፖለቲከኞች መታሰር የፈጠረው ህዝባዊ ቁጣ እንደቀጠለ ነው

ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ህገወጥ በሆነ መልኩ አሳልፈው ከሰጡዋቸው በሁዋላ ኢትዮጵያውያን አሁንም ቁጣቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ አንዳንድ ወገኖች ” የአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ልብን የሚሰብር ቢሆንም፣ ወሳኙ ነገር ማዘን ሳይሆን ለለውጥ ቆርጦ በመነሳት መታገል ነው” ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የየመን መንግስት የወሰደውን እርምጃ እንዲሁም የኢህአዴግ መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን አስሮ ...

Read More »

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በረመዳን ጾም ተጠናክሮ የቀጠለው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ፣ ዛሬም በበኒ መስጂድ እጅግ ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት ተካሂዷል። ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች ” የእምነት ነጻነታችን ይከበር፣ ለከፈልነው መስዋትነት ተመጣጣኝ ውጤት እናመጣለን” የሚሉ መፈክሮችን ጽፈው አሳይተዋል። ከሁለት አመት በላይ የዘለቀው የሙስሊሙ ተቃውሞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መሪዎቹ እየገለጹ ነው።

Read More »

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የሚፈጸመው እስር እንዳሳሰበው ገለጸ

ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ተጠናክሮ የቀጠለው እስር በአገሪቱ ውስጥ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይኖር ያደረገ ነው ብሎአል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ያሉበት ሁኔታ አለመታወቁንና ለከፍተኛ ስቃይ ሊዳረጉ እንደሚችሉ መግለጹንና አለማቀፉ ማህበረሰብ አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ማሳሰቡን ያስታወሰው አምነስቲ፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ ደንኤል ሽበሺ፣ አብርሃ ደስታ፣ የሽዋስ አሰፋና ሀብታሙ አያሌው የተባሉ ታዋቂ ፖለቲከኖች መታሰራቸው ...

Read More »

አቶ አንዳርጋቸውን መታሰር ተከትሎ ኢትዮጵያውያን  ቁጣቸውን መግለጽ ቀጥለዋል

ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ሰሞኑን ከአገር ቤት በሚደወሉ ስለኮች የተጨናነቀ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ደዋዮች የኢህአዴግን ስርአት በሃይል ለመፋለም መቁረጣቸውን የሚገልጹ ናቸው። እንደሰሞኑ ሁሉ ” መንገዱን አሳዩን እና አቶ አንዳርጋቸው ይዘውት የተነሱትን ራእይ እውን እናድርገው ” የሚሉ ወጣቶች እየተበራከቱ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ህዝቡ ራሱን እያደራጀ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባው እያሳሰቡ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ መንግስት ህዝቡን ለማረጋጋት በሚል አቶ አንዳርጋቸውን ...

Read More »

ታዋቂዎቹ ፖለቲከኞች በማእከላዊ እስር ቤት መታሰራቸው ታወቀ

ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌደራል ፖሊሶች እየተደበደበ ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስዶ የነበረው ታዋቂው ፖለቲከኛና ጸሃፊ አብርሃ ደስታ ማእከላዊ እስር ቤት መታሰሩ ታውቋል። የአብረሃ መኖረያ ቤት በፖሊሶች እንደተፈተሸም ለማወቅ ተችሎአል። የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወጣት ሃብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው ምክትል የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ዳንኤል ሽበሺ እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ የሽዋስ አሰፋ ዛሬ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ...

Read More »

የህወሃቱ የስለላ ሃለፊ ታሰረ

ሐምሌ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህወሃት አባል የሆነውና በሶማሊ ክልል የደህንነት ሃለፊ በመሆን ሲሰራ የነበረው መቶ አለቃ አወጣሃኝ በክልሉ ፕሬዚዳንት ትእዛዝ እንዲታሰር ተደርጓል። ግለሰቡ በምን ምክንያት እንደታሰረ ለማወቅ ባይቻልም፣ በክልሉ ፕሬዚዳንት እና በህወሃት የጸጥታ ሰራተኞች መካከል እየተካረረ የመጣው አለመግባባት ማሳያ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።

Read More »