በአማራ ክልል አርሶ አደሮችን ትጥቅ የማስፈታት ሂደቱ ውጤታማ አይደለም ተባለ፡፡

ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአስተዳደር ፀጥታ እና የፖሊስ ኮሚሺን በጋራ የ2006 ዓ.ምየ11 ወራት አፃፀም በገመገሙበት ውይይት የጎጃም ፤የጎንደር ፤የሺዋ እና የኦሮሞ አርሶ አደሮች  ዛሬምበድብቅመሳሪያዎችንበነፍስወከፍበየቤቱይዘው እንደሚገኙያወሱሲሆን፣ አርሶ አደሩ የጦር መሳሪያውን እንዲመልስጥረትቢደረግምአልተሳካምብለዋል፡፡

አዲስህግእንዲወጣየጠየቁትየፀጥታሃይሎች  በአርሶአደሩበህገወጥእጅየተሰገሰገውከ 4 ሚሊዩንበላይየሚገመትየተለያየየጦርመሳሪያ በአገሪቱ ለሚፈጸም ግድያ ዋና መንስኤ መሆኑን   አመልክተዋል፡፡

በዘመቻየጦርመሳሪያማስፈታትእናየቅጣትወሰንመመሪያእንደሃገርአለመኖርችግር  መሆኑንበማንሳትየፊደራል መንግስት የህገወጥመሳሪያቁጥጥርአዋጅእንዲያወጣበሪፖርታቸውጠይቀዋል፡፡

የፌድራልፖሊስ መረጃ እንደሚያመለክተው ከአማራ ክልል በመቀጠል አፋር እና ሶማሌ መሳሪያ ያላ ወረዱ ክልሎች ተብለው ተጠቅሰዋል።