አቶ ሽመልስ ከማል የሚመሩት ፕሬስ ድርጅት ደካማ ነው ተባለ

ሐምሌ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርላማ : ባህል ፣ ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ቋሚ ኮምቴ ስብሳቢ 73ኛ የምስረታ ዓመቱን በቅርቡ ያከበረውን የኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅት በቁሙ እየሞተ መሆኑን በመጠቆም በራሱ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይትችትአቀረቡ፡፡

የቋሚ ኮምቴው ስብሳቢ ወ/ሮ ፈቲያ ዩሱፍ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ዓርብ እና ቅዳሜ እለት በታተመ ቃለ ምልልሳቸው እንደተናገሩት የአዲስ ዘመን ፣ ኢትዮጵያ ሄራልድ ፣ በሬሳ ፣ ዓልኣለም ጋዜጦች እና የዘመን መጽሄት አሳታሚ የሆነውና በአቶሽመልስከማልየቦርድሰብሳቢነትየሚመራው  የኢትዮጽያፕሬስድርጅትተወዳዳሪመሆንእንዳልቻለ፣ የጋዜጦቹህትመትቁጥርምከጊዜወደጊዜእያሽቆለቆለእንደመጣ፣በገበያላይየሚያነበውእንደሌለበመጥቀስበይፋ ድክመቱንተናግረዋል፡፡

ድርጅቱ ችግሩን ለመቅረፍ ወደ ኮርፖሬት አደረጃጀት እንዲገባ በተደጋጋሚ እንደ ተነገረው ነገርግን በማኔጅመንቱ  ድክመት እንዳልተሳካ ተናግረዋል፡፡ «አምናሪፎርምውስጥግቡብለናቸውየሆነነገርጀምረውእኛሥራበዝቶብን ወደሌላዘወርስንልይተውታል» በማለት የማኔጅመንቱን እንዝህላልነት አሳይተዋል፡፡

ሠራተኛውገሚሱበሲቪልሰርቪስ፣አንዳንዱበቦርድእንደሚተዳደርናይህልዩነትበኮርፖሬትአደረጃጀት እንዲስተካከልተነግሮአቸውምእንዳላስተካከሉትወ/ሮፈቲያገልጸዋል።