ጥቅምት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የድረገጹ አዘጋጆች ለኢሳት በላኩት መግለጫ እንደጠቀሱት ድረገጹ በኢትዮጵያ ውስጥ ወንጀሎችን ያቀዱ፣ ለወንጀሎቹ ውሳኔ የሰጡ፣ ወሳኔዎችን ያስፈጸሙ፣ የመሩና ያቀነባበሩትን በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓ እንዲሁም በየትኛውም የምእራብ ሀገሮች እንደ የሀገሮቹ የህግ አግባብ መሰረት ክስ ለመመሥረት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ መረጃዎችንና ምስክሮችን ማሰባሰብ እና ማጠናቀር አላማ አድርጓል። ወንጀል በፈጸሙት ላይ በቂ መረጃዎች ከተሰበሰቡ በኋላ ህግ ፊት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ከአባይ ግድብ ስራ ጋር በተያያዘ በተወሰኑ የህወሃት ደጋፊዎች ከፍተኛ የደን ጭፍጨፋ እና ምዝበራ እየተካሄደ ነው
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአባይ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት እቅድ እንደሚያሳየው ግድቡ ሲጠናቀቅ 1600 ኪሎሜትር ስኩየር መሬት የሚሸፍን ውሃ የሚተኛበት ሲሆን፣ የዚህ መሬት አካል 90 በመቶው በደን የተሸፈነነ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ አንጻራዊ በሆነ መልኩ የተሻለ የደን ሽፋን አለው የሚባለው ግድቡ የሚሰራበት የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቢሆንም፣ ከ200 ኪሎ ሜትር ያላነሰ ስፋት ያለው የክልሉ ደን በፍጥነት እየተጨፈጨፈ ነው። ...
Read More »የደህንነት ሃይሎች ዜጎችን እያፈኑ መውሰዱን ቀጥለውበታል
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን ተጠናክሮ የቀጠለው የገዢው ፓርቲ አፈና መንግስት ራሱ ያስታጠቃቸውን ታጣቂዎች ትጥቅ እስከማስፈታት መድረሱን ምንጮች ገለጹ በትግራይና በአማራ ክልሎች ባለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው አፈና ቀጥሎ ጥቅምት 26 ቀን 2007 ኣም የሰላም ታጋይ እየጠባለ የሚታወቅ ወጣት ሽሻይ አዘናው በመቀሌ ከተማ በትግራይ ክልል የፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ገ/ህይወት ካህሳይ እና በደህንነት ሃይሎች ከሚሰራበት የኢትዮጵያ ...
Read More »የኢህአዴግ መንግስት ከአረብ ሃገራት ጋር በአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ላይ ሊያደርገው ያሰበው ስምምነት በአረብ ሃገራት መሪዎች ተቀባይነት ማጣቱ ታወቀ
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በኢትዮጵያ እና በአረብ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እንዲሁም መንግስት ወደ አረብ አገራት በሚላኩ ዜጎች ጉዳይ ሊፈጽመው ያሰበው ስምምነት ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ግምገማ ተካሂዶ ነበር። መንግስት ተጓዝ ሰራተኞችን በሚመለከተ ያወጣው ህግ በአረብ መንግስታት እውቅና የተነፈገው ሲሆን፣ የአረብ አገራት ባለስልጣናት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች የሙያ ክህሎት የላቸውም፣ በአገሪቱ ...
Read More »በደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ውሃ መጥፋቱን ተማሪዎች ተናገሩ
ጥቅምት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዩኒቨርስቲው ውስጥ በሚታየው ተደጋጋሚ የሃይል መቆራረጥና የውሃ እጥረት ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ለመከታተል አልቻሉም። ከውሃ እጥረት ጋር በተያያዘ ከጽዳት ጋር ለተያያዙ በሽታዎች ሊደራጉ እንደሚችሉ ተማሪዎች ፍርሃታቸውን ገልጸዋል።
Read More »በቅርቡ በጋምቤላ ተከስቶ በነበረው ግጭት የሞቱ ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ ሆነ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ የአሁኑ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ( ሰመጉ) ባወጣው 132ኛ ልዩ መግለጫ በክልሉ በመንገሽና ጎደሬ ወረዳዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የተገደሉ የ60 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በሪፖርቱ እንደቀረበው 27 የአማራ፣ 27 የመዠንገር፣ 2 የከፋና 4 የኦሮሞ ተወላጆች ተገድለዋል። እንዲሁም 16 የአማራና 6 የመዠንገር ተወላጆች የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው፣ 36 የአማራ ...
Read More »መንግስት የተቃዋሚ መሪዎችን እያደነ ማሰሩን ቀጥሎአል
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሁለት ቀናት ጀምሮ መንግስት በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ የተቃዋሚ አመራሮችን በመያዝ እያሰረ ነው:: በትግራይ ክልል በምዕራባዊያን ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ ዳንሻ ከተማ የአረና ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ዘነበ ሲሳይ ጥቅምት 25፣ 2007 ዓም ከቤታቸው ተነጥለው በመወሰድ ሲታሰሩ፣ በተመሳሳይ ቀን በሁመራ የአረና የቁጥጥር ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ አማረ ተወልደ ታስረዋል። ከወራት ...
Read More »በነ ወርቅነህ አገኘሁ መዝገብ ብይን ለመስጠት የተያዘው ቀጠሮ ተራዘመ
ጥቅምት ፳፭ (ሃያ አምት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ በመሰረተባቸው አቶ ዘላለም ወርቅነህ፣ ሃብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ የሽዋስ አሰፋና በሌሎች 5 ተካሳሾች ላይ ዋስትናን በተመለከተ ሊሰጥ የነበረውን ውሳኔ አራዘመ። ፍርድ ቤቱ የሁሉም ጠበቆች ተዘጋጅተው ባለመቅረባቸው ውሳኔውን ለህዳር 2 ፣ 2007 ማራዘሙን አስታውቋል። እስረኞቹ በሽብር ወንጀል ተከሰው ለወራት በእስር እየተሰቃዩ ...
Read More »በምእራብ አርማጭሆና በመተማ የአንድነት ፓርቲ አደራጆች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ታፍነው ተወሰዱ
ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ የተላኩ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ደህንነቶች፣ ወደ ፓርቲው መሪዎች ቤት ከንጋቱ አስራ አንድ ሰአት ላይ በመሄድ፣ መኖሪያ ቤቶቻቸውን ሰብረው በመግባትና አንዳንዶችንም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በመደብደብ አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ወስደዋቸዋል። የመተማ ወረዳ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በላይነህ ሲሳይ፣ የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ አንጋው ተገኝ እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ አባላት የሆኑት አባይ ዘውዱና እንግዳው ...
Read More »ዘጠኝ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት ትብብር የመጀመሪያ የትግል ስትራቴጂውን ይፋ አደረገ
ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ትብብር የመሰረቱ 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አድርገዋል። ‹‹ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የዝግጅት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል። ‹‹ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ ያለውን ወገናዊነትና ጉዳይ አስፈጻሚነት ፍንትው ...
Read More »