የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስዊዘርላንድ የዙሪክ ነዋሪ የሆኑት አክቲቪስት ፊዮሬላ ሮማኖ ለኢሳት እንደገለጹት ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ ቀጠሮ አስይዘው ከሚኖሩበት ዙሪክ ኤምባሲው ወደሚገኝበት ጀኔቫ የ3 ሰዓት መንገድ ተጉዘው ቢሄዱም፣ የኤምባሲ ስራተኞቹ በአካል ሲያዩዋቸው በተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደሚሳተፉ ስለለዩዋቸው አገልግሎቱን ሳይሰጡ መልሰዋቸዋል። ኤምባሲው እንደደረሱ ጎይቶም በሚባል ሰራተኛ የተሰጣቸውን ፎርም ከሞሉና ፎቶግራቸውን ከሰጡ በሁዋላ በስዊዘርላንድ ለምን ያህል ዓመት እንደቆዩ ጥያቄ የቀረበላቸው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ካህኑ የአረና አባል በመሆናቸው ዘግናኝ ድብደባ ተፈጸመባቸው
የካቲት ፳፭(ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀፍታ ሑመራ ወረዳ በረኸት ከተማ ነዋሪ የሆኑት ቄስ ሕሉፍ ኸሕሳይ የዓረና-መድረክ ኣባል በመሆናቸው ብቻ ዘግናኝ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ከፓርቲው ጽህፈት ቤት የወጣ መረጃ አመለከተ። እንደ መረጃው ከሆነ ቄስ ህሉፍ በደረሰባቸው ዘግናኝ ድብደባ በህይወትና በሞት መካከል የሚገኙ ሲሆን፤ ለድብኢደባቸው ምክንያቱ የአረና አባል መሆናቸው ብቻ ነው። የካቲት 17 ቀን 2007ዓመተ ምህረት ምሽት 1፡00 ሰዓት ኣከባቢ ...
Read More »አንድ ሱዳናዊ ሹፌር ኢትዮጵያዊቷን በጩቤ ወግቶ ከመኪና ላይ መወርወሩ ህዝባዊ ቁጣ አስነሳ
የካቲት ፳፬(ሃያአራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጊቱ የተፈጸመው ማክሰኞ የካቲት 24 ፣ 2007 ዓም ሲሆን አንድ የሱዳን ታርጋ ያለው ፣ በሱዳናዊ ሹፌር የሚሽከረከር ማዳበሪያ ያጫነ ከባድ መኪና ከሱዳን ወደ ባህርዳር በመጓዝ ላይ ነው። መኪናው እንፍራዝ እየተበላ በሚጠራ አነስተኛ ከተማ ላይ ሲደርስ አንዲት መኪና በመጠበቅ ላይ የነበረች ኢትዮጵያዊት ወጣት ሹፌሩን ትብብር ጠይቃው ትሳፈራለች። ምክንያቱ በውል ባይታወቅም፣ አንዳንዶች እንደሚሉት ሊደፍራት በመሞከሩና ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ መልእክቱን እንዲለውጥ ተጠየቀ
የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ፣ ኤፍ ኤም 96.3፣ ሰማያዊ ፓርቲ ለምርጫ ቅስቀሳ ያቀረባቸውን መልእክቶች እንዲለውጥ፣ ካልለወጠ ግን እንደማያስተላልፍ ገለጸ። ጣቢያው እንዲወጡ ከጠየቃቸው መልእክቶች መካከል ‹‹ሀገራችን ዛሬ በቀሪው ዓለም የምትታወቀው በእርስ በርስ ጦርነት ነው›› የሚለው የሚገኝበት ሲሆን፣ መልእክቱ ለአመጽና ለሁከት የሚያጋልጥ ነው የሚል ምክንያት አቅርቧል። ሌላው እንዲወጣ የተጠየቀው ‹‹ህዝቧ ...
Read More »በቀድሞ መንግስት ምርኮኛ ወታደሮች የተመሰረተው ኦህዴድ የ25 ዓመት የምስረታ በዓሉን ሊያከብር ነው
የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞ የደርግ ወታደሮችን በማሰባሰብ በህወሓት በጎ ፈቃድ የተመሰረተው የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) የተመሠረተበትን 25 ዓመት በድምቀት ለማክበር መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የኦህዴድ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳባ ደበሌ በሰጡት መግለጫ ኦህዴድ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል ከመጋቢት 1 እሰከ መጋቢት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በልዩ ልዩ መርሃግብሮች ያከብራል፡፡ በወጣው ፕሮግራም መሰረትም ከመጋቢት ...
Read More »ም/ል ጠ/ሚኒስትሩ ተቃውሞ ገጠማቸው
የካቲት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የአልጀሪያው -ኤል ኡልማ ቡድኖችን ጨዋታ ለማየት በባህርዳር ስታዲየም በእንግድነት የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን ከጨዋታው በፊት ንግግር እንዲያደርጉ በተጋበዙበት ሰአት ጨዋታውን ለመመልከት በስቴዲየሙ የተገኘው ሕዝብ በታላቅ ቁጣ የተቃውሞ ድምጽ በማሰማቱ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ መገደዳቸውን የክልሉ ወኪላችን ገልጻለች፡፡ አብዛኛው ህዝብ ከተቃውሞ ድምጹ ጋር የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት በእጁ በማሳየት አቶ ደመቀ ንግግራቸውን እንዲያቋርጡ ...
Read More »የአድዋ ድል በአል ተከበረ
የካቲት ፳፫(ሃያሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን የጣሊያንን ወራሪ ሃይል ድል የመቱበትና ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቁሮች በነጮች ላይ የአሸናፊነት ታሪክ የጻፉበት የአድዋ ድል 119 አመት በአል በአዲስ አበባ ተከብሮአል። በርካታ አርበኞችና ወጣቶች ፣ የአድዋን ድል በመሩት በአጼ ሚኒሊክ ሃውልት ዙሪያ በመሰባሰብ ቀኑን አክበረው የዋሉ ሲሆን ወጣቶች የጀግንነት መገለጫ የሆነውን ባህላዊ ሽለላ ሲያሰሙ፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ በፖሊስ እንዲበተኑ ተደርጓል። ፖሊሶች ያልተፈቀደ ሰልፍ ...
Read More »የብረታብረት ኢንዱስትሪዎች ለኪሳራ መዳረጋቸው ተገለጸ
የካቲት ፳፫(ሃያሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብረታብረት ኢንዱስትሪዎች ከኃይል አቅርቦት መቆራረጥ፣ ከአቅርቦት ማነስ እንዲሁም ከውጪ ምንዛሪ እጥረት ጋር ተያይዞ በሙሉ አቅማቸው ማምረት አለመቻላቸውና ለኪሳራም እየተዳረጉ መሆናቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ የብረታብረት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ሰሞኑን በግዮን ሆቴል የ2007 ግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት ባሳወቀበት ወቅት እንደተጠቀሰው በብረታበረት ዘርፍ ወደ 60 የሚሆኑ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ኢንዱስትሪዎች በዋንኛነት ከኃይል አቅርቦት ...
Read More »በከተማ ዘርፍ ከሚሰሩ ሙያተኞች 4 በመቶው ብቻ የምዘና ፈተናውን አለፉ
የካቲት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ዘንዘልማ ግቢ ውስጥ በተካሄደው ስልጠና ለመሳተፍ ከአማራ ክልል ከሚገኙ ከተሞች ለመጡ 450 የከተማ ልማት ዘርፍ ባለሙያዎችና ሃላፊዎች በተሰጠው ግምገማ አስር ባለሙያዎች ብቻ የተሰጣቸውን የብቃት መመዘኛ ማለፋቸው የክልሉንና የፌዴራል ሃላፊዎችን ክፉኛ ማስደንገጡን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ባለሙያዎቹና ሃላፊዎች በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሙያ ሁኔታ የተሰማሩ የከተማ ፕላን ሰራተኞች፣በመሬት ባንክ አገልግሎት የተሰማሩ እና ...
Read More »በአዋሳ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሟቾች ቁጥር ከ20 በላይ ነው ሲሉ የቃጠለው ሰለባ የሆኑ ሰዎች ገለጹ
የካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ዋና ከተማ በአዋሳ የካቲት 14 ቀን 2007 ዓም በደረሰው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ የሟቾች ቁጥር በመንግስት እንደተገለጸው አንድ ሳይሆን ከ20 በላይ መሆኑን ተገጂዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከፍተኛ ንብረት ከወደመባቸውና እሳቱ ሲነሳ በስፍራው ከነበሩት መካከል አንዱ ለኢሳት ሲናገር፣ እርሱ የ6 ሰዎችን የተቃጠለ አስከሬን ማየቱን፣ በስፍራው የሚገኙ ጓደኞቹ ደግሞ በአጠቃላይ እስካሁን 27 አስከሬን ተፈልጎ መቀበሩን ...
Read More »