ሚያዝያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቴሬንሴ ሊዮንስ በዋሽንግተን ፖስት ላይ “ነጻና ፍትሀዊ ምርጫን ከኢትዮጵያ ጋር ምን አገናኘው?”በሚል ርዕስ ባሰፈሩት ጽሁፍ በመጪው ግንቦት 16 በ ኢትዮጵያ የሚካሄደው ምርጫ የመርሀግብር ማሟያ እንጂ ትርጉም ያለው እንዳልኾነ ገልጸዋል። ሂደቱ ከቅድመ-ምርጫ ጀምሮ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ እንዳልነበር በስፋት ያብራሩት ጸሃፊው ”ዜጎች አዲስ መንግስት የማይመርጡበት ትርጉም የለሽ ምርጫ”ሲል አጣጥለውታል። የአሜሪካ ምክትል የውጪ ጉዳይ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በትጥቅ ትግል ለዉጥ ለማምጣት የሚታገሉ ድርጅቶች የጥምረት ስምምነት ተፈራረሙ
በገዢው የኢህአዴግ መንግስት ላይ የትጥቅ ትግልን እያካሄዱ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ወደ ጥምረት እና ውህደት የሚወስዳቸውን ውይይት መጀመራቸውን ባለፈዉ አርብ ይፋ አደረጉ ። የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፥ የጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፥ የቤኒሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፥ የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ነቅናቄ፥ እና የአርበኞች ግንቦት ፯ ለአንድነት እና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ የጥምረት ብሎም የውህደት ዉይይቶችን መጀመራቸውን አስታወቁ ። “ሀገርን እና ህዝብን ለማዳን የጋራ ግብ አድርጎ ለመስራት” ...
Read More »አንድ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኝ ወጣት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ተገደለ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ 22 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖረው የ25 ዓመቱ ሲሳይ ተሾመ በቅጽል ስሙ ገብሬ ያለፉትን 8 ዓመታት በቃሊቲና በዝዋይ እስር ቤቶች እየተመላለሰ አሳልፏል። በተለይ ወደ ዝዋይ እስር ቤት ከተላለፈ በሁዋላ ፣ ሃጎስ የተባለው የእስር ቤቱ ሃላፊ ” አንተ የነፍጠኛ ልጅ እንበቀለሃለን፣ በእኔ እጅ ነው የምትሞተው” እያሉ ይደበድቡትና ይዝቱበት ነበር። ባለፈው ቅዳሜ ...
Read More »የኢሳት የአሞስ ስርጭት እንደገና ታፈነ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት በናይል ሳት ሲያስተላልፈው የነበረው ስርጭቱ በ2 ሳምንታት ውስጥ የኢህአዴግ አገዛዝ ባሳደረው የዲፕሎማሲ ጫና ከአየር ላይ እንዲወርድ ከተደረገ በሁዋላ፣ በአሞስ ስርጭቱን ቢጀምርም፣ ከአገሪቱ በሚለቀቀው ሞገድ እንደገና በመታፈኑ ከአየር ላይ እንዲወርድ ተደርጓል። ኢሳት ባለፉት 5 አማታት 8 የሳተላይት ጣቢያዎችን እየቀያየረ ስርጭቱን ሲያቀርብ ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢሳትን ለማፈን የሚታየው የዲፕሎማሲ ዘመቻ፣ አገዛዙ ...
Read More »በሶማሊ ክልል በደረሰው ድርቅ ከ2 ሺ በላይ የቤት እንስሳት አለቁ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተለያዩ አለማቀፍ ድርጅቶች የመስክ ጉብኝት በማድረግ ባወጡት ሪፖርት በሲቲ ዞን ባለፈው ወር ብቻ በተከሰተው ድርቅ ከ2 ሺ በላይ በጎችና ፍየሎች ሲያልቁ ነዋሪዎችም እየተሰደዱ ነው። በረሃቡ ምክንያት በሃዲጋላ ወረዳ ጉርጉር ቀበሌ በጎች የሌሎችን በጎች ቆዳ ሲበሉ መታየታቸውን በስእል የተደገፈው ሪፖርት ያሳያል። አይሺያ፣ ሃድሃጋላ፣ ከፊል ሽንሌ፣ ከፊል ደምበል፣ ሰሜን ኤረር፣ ከፊል አፍዴም እና ...
Read More »የስኳር ፕሮጀክቶች በፋይናንስ ችግር ምክንያት ሳይሳኩ ቀሩ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች መካከል የስኳር ፕሮጀክቶች በዋነኛነት በፋይናንስ እጥረት ምክንያት እንዳልተሳኩ ከስኳር ኮርፖሬሽን የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡ በሰኔ ወር 2007 መጨረሻ የሚጠናቀቀው የአምስት ዓመት መርሃግብሩ ከተያዙት ፕሮጀክቶች አንዱ የስኳር ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ለፕሮጀክቶቹ ተስፋ ተጥሎባቸው የነበሩት አበዳሪ ተቋማት ገንዘብ ሊሰጡ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ዕቅዱ ሙሉ በሙሉ ማሳካት ሳይቻል ...
Read More »ወጣት እስማኤል ዳውድን ጨምሮ 18 ተከሳሾች ላይ ክስ ተመሰረተ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት አይኤስን ለማውገዝ ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በጠራው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ አስነስተዋል የተባሉትና በወረዳ 9 ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙት ተከሳሾች ላይ መደበኛ ክስ ተከፈተ። በዚህም መሰረት የሚሊዮኖች ድምፅ ጋዜጣ አምደኛና የአንድነት አባል የነበረው ወጣት እስማኤል ዳውድን ጨምሮ በሌሎች 18 ተከሳሾች ላይ የፌደራል ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል። በወንጀል ዝርዝሩ ላይ ተከሳሾቹ ...
Read More »የምርጫ ገጠመኝ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እየተዋከቡ፣ እየታሰሩና ደብደባም እየተፈጸመባቸው መሆኑን በየጊዜው የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ። የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች አንድ ጊዜ የቡና ሌላ ጊዜ የእድር እያሉ በተለይም እናቶችን እየሰበሰቡ ኢህአዴግን እንዲመርጡ፣ ልጆቻቸውንም አመጽ እንዳያስነሱ እንዲመክሩ ለማግባባት ይጥራሉ። መራጮች በኢህአዴግ ካድሬዎች የቅስቀሳ መንገድ መማረራቸውን ከመግለጽ ውጭ ፣ ይህ ...
Read More »በጋምቤላ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዉ ህይወት ጠፋ
በጋምቤላ ክልል ጎደሬ ወረዳ ሜጢ ከተማ አካባቢ ሰሞኑን በተቀሰቀሰ ግጭት አምስት ሰዎች መሞታቸውን የአይን እማኞች ለኢሳት ገልጸዋል ። በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ማጣታቸውን የሚናገሩት የወረዳው ነዋሪዎች የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ጥያቄዎችን ባነሱ ነዋሪዎች ላይ የሚወስዱት እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል ። በተለይ ከሁለት ሳምንት በኋላ ከሚካሄድውን ምርጫ ጋር በተያያዘ ውጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉን የገለጹት እማኞች፥ ከተገደሉት አምስት ሰዎች በተጨማሪ ሁለት ነዋሪዎች ...
Read More »በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያዉያን የፀሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት ተካሄደ
በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ እና አካባቢዋ ያሉ አብያተ ክርስቲያንናት እንዲሁም የተለያዩ የሲቪል ድርጅቶች በቅርቡ በየመን፥ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢትዮጵያዊያንን ለመዘከር እሁድ እለት በዚህ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ የመታሰቢያ ዝግጅቶችን አካሄዱ። ነዋሪነታቸው በዋሺንግተን ዲሲ እና በአካባቢዋ በርካታ ኢትዮጵያዊን በታደሙበት በዚህ ዝግጅት፥ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ሟች ኢትዮጵያዊያንን አስመልክቶ ያስተላለፉት የሀዘን መልክት ተነቧል። ልዪ የጸሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት በተከናወነበት በዚሁ ...
Read More »