የኢሳት የአሞስ ስርጭት እንደገና ታፈነ

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት በናይል ሳት ሲያስተላልፈው የነበረው ስርጭቱ በ2 ሳምንታት ውስጥ የኢህአዴግ አገዛዝ ባሳደረው የዲፕሎማሲ ጫና ከአየር ላይ እንዲወርድ ከተደረገ በሁዋላ፣ በአሞስ ስርጭቱን
ቢጀምርም፣ ከአገሪቱ በሚለቀቀው ሞገድ እንደገና በመታፈኑ ከአየር ላይ እንዲወርድ ተደርጓል።

ኢሳት ባለፉት 5 አማታት 8 የሳተላይት ጣቢያዎችን እየቀያየረ ስርጭቱን ሲያቀርብ ቆይቷል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢሳትን ለማፈን የሚታየው የዲፕሎማሲ ዘመቻ፣ አገዛዙ በኢሳት ስርጭት ክፉኛ መደናገጡን እንደሚያሳይ አስተዳደሩ ገልጿል።

የኢሳት አስተዳደር ሌሎች የሳተላይት ጣቢያዎችን በማፈላለግ ላይ ሲሆን፣ እንደተሳካ ለውድ ተመልካቾች ያስታውቋል። በኢሳት ሬዲዮ ላይም የአፈና ሙከራ እየተደረገ በመሆኑ ስርችቱ አልፎ አልፎ እየተቋረጠ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች
ያሳያሉ።