የምርጫ ገጠመኝ

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት እየተዋከቡ፣ እየታሰሩና ደብደባም እየተፈጸመባቸው መሆኑን በየጊዜው የሚደርሱን መረጃዎች
ያሳያሉ።
የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች አንድ ጊዜ የቡና ሌላ ጊዜ የእድር እያሉ በተለይም እናቶችን እየሰበሰቡ ኢህአዴግን እንዲመርጡ፣ ልጆቻቸውንም አመጽ እንዳያስነሱ እንዲመክሩ ለማግባባት ይጥራሉ።
መራጮች በኢህአዴግ ካድሬዎች የቅስቀሳ መንገድ መማረራቸውን ከመግለጽ ውጭ ፣ ይህ ነው የሚባል እርምጃ ሲወስዱ አይሰማም። ሰሞኑን አንድ የአዲስ አበባ ወጣት የወሰደው እርምጃ ጥላቸው የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ ነው።
አንድ የኢህአዴግ ካድሬ የኢህአዴግ ምልክት የሆነውን የንብ ቲሽርት ለብሳ በየመንደሩ እየዞረች፣ ቤት ለቤት እያንኳኳች ኢህአዴግን ምረጡ ትላለች። ካድሬዋ አንድ ወጣት ቤት ስትደርስ፣ ወጣቱ “ምን ልታደርጊ መጣሽ?” ይላታል።
እሷም በድፍረት መለሰችለት። በመልሷ የተበሳጨው ወጣት ” ድርጅትሽ ቆሻሻ! አሁንስ በጣም ጠገባችሁ!” የሚሉና ሌሎችንም ስድቦች ከሰደባት በሁዋላ፣ በንዴት አንገቷ አካባቢ ሲመታት ወጣቷም መሬት ላይ ወደቀች። ካድሬዋም
ከሰአታት በሁዋላ ነፍስ ዘርቶባት ከመቶት ተርፋለች። እንዴት ተደፈርን ያሉት የኢህአዴግ ካድሬዎች፣ ወጣቱን ለመያዝ አሰሳውን አጠናክረውታል። ዘጋቢያችን ይህን ዜና እስካጠናከረበት ሰአት ድረስ ወጣቱ አልተያዘም።