ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአንድ አመት በፊት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ስራ አሰማራችሁዋለሁ በሚል መንግስት ካሰበሰባቸው ከ2 ሺ 500 ያላነሱ ወጣቶች 1 ሺ 500 የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው በተለያዩ የመከላከያ ተቋማት ቢመደቡም፣ ቃል የተገባላቸው እና በተግባር የሚያዩት ነገር ባለመጣጣሙ ስራቸውን ጥለው መጥፋታቸውን ሰልጣኖች ተናግረዋል። አሚባራ በሚባለው አካባቢ የሚገኝ ጫካ መንጥረው ህንጻ በመስራት ስልጠና የጀመሩ ወጣቶች እንደሚሉት፣ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ወጣት ሳሙኤል አወቀን ገድሏል የተባለው ሰው ቃል የግድያውን ድራማ ያመለክታል ተባለ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት፣ የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም አደራጅ የሆነውን የወጣት ሳሙኤል አወቀን ገዳይ በ19 አመታት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል። ይሁን እንጅ ገዳይ ተብሎ የቀረበው አቶ ተቀበል ገዱ ለፍርድ ቤት የሰጠው ቃል እና ፖሊስ በወቅቱ የሰጠው መግለጫ ሊጣጣሙ አልቻሉም። ገዳይ ተብሎ የቀረበው ሰው ለፍርድ ቤቱ ግድያውን የፈጸመው መጠጥ ቤት አብረው ...
Read More »ሜሮን አለማየሁ ተፈረደባት!
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ሰበብ ታስራ ‹‹ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ በማወክ›› ወንጀል የተከሰሰችው ሜሮን አለማየሁ የ6 ወር እስር ተፈርዶባታል፡፡ ሜሮን አለማየሁ ሚያዝያ 14 በተጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት የለም፣ አትነሳም ወይ፣ የታረደው ወገን ያነተ አይደለም ወይ›› በሚል ሁከትና ብጥብጥ ፈጥራለች ተብላ በተከሰሰችበት ክስ ፣ በዋስ ...
Read More »የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ወጣ
ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ ስምንተኛ ክፍል ያልደረሰ/ች ሠራተኛ ወደውጭ ሀገር መላክ የሚከለክል ሲሆን በሥራው የሚሰማሩ ኤጀንሲዎች ወደ 2 ሚሊየን ብር ወይም 100 ሺ ዶላር ለዋስትና ማስከበሪያ ካላስያዙ ወደስራ እንዳይገቡ ክልከላ አስቀመጠ፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለውን አዋጅቁጥር 632/2001 ሙሉ በሙሉ የሚሰርዘው ይህ ረቂቅ አዋጅ በቀድሞ አዋጅ ፈቃድ የተሰጣቸው ኤጀንሲዎች ...
Read More »በምስራቅ ጎጃም ዞን ከምርጫ ጋር በተያያዘ አርሶ አድሮች እየታሰሩ ነው
ኢሳት ዜና (ሰኔ 26 2007) በቅርቡ በምስራቅ ጎጃም ዞን በወጣት እጩ የፓርላማ ተወዳዳሪ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በርካታ ሰዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው በመታሰር ላይ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ ። በዞኑ የሚገኙ አርሶ አደሮች ከ 15 አምት በፊት ያልከፈላቹት የማዳበሪያ እዳ አለባችሁ እየተባሉ በጅምላ መታሰራቸውን የተናገሩት እማኞች ገበሬዎቹ በሞት የተላዩዋቸውን ዘመዶች እዳ ጭምር እንዲከፍሉ መገደዳቸውም ታውቋል። የዞኑ ባለስልጣናት የማዳበሪያ እዳን ምክንያት ...
Read More »ከምርጫ 2007 በሁዋላ በስፖርታዊ ውድድሮች የተለያዩ የተቃውሞ ክስተቶች እየታዩ ነው ተባለ
ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን በድንገት በተጠራው ስብሰባ ኮሚሽነር ያየህ አዲስ ፣ የብሄራዊ ሊጉ ጨዋታዎች በሚካሄዱበት ከተሞች ከምርጫ 2007 በኋላ የሚታዩ የስፖርታዊ “ጨዋነት ጉድለቶች” አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡ ወቅቱ የምርጫ ውጤት ይፋ የሆነበት በመሆኑ በተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎች ላይ ልዩ ጥንቃቄ እንዲደረግም ተናግረዋል። ኮሚሽነር ያየህ ” ዛሬ በስፖርት ሜዳ የሚታየው ተቃውሞ ...
Read More »የኢትዮጵያ ፓርላማ የምርጫ ቦርድ ቁልፍ ሰው የነበሩትን ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሔርን የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮምሽን ኮምሽነር አድርጎ ሾመ፡፡
ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዶ/ር አዲሱ የምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ቢሆኑም ከህወሃት/ኢህአዴግ ቀጥተኛ መመሪያ በመቀበልና በማስፈጸም ረገድ ቁልፍ ሰው መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በተለይ ተቃዋሚዎች እንዲዳከሙና ትንንሽ ልዩነቶቻቸውን በማጦዝ ፓርቲዎች እንዲናጉና እንዲፈርሱ ከኢህአዴግ ጋር እየተናበቡ የሚሰሩ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚያቀርቡትንም አቤቱታ በማድበስበስ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃና፤ ዶ/ር አዲሱ የሚሰጡዋቸውን ...
Read More »የድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ፍርድ የማሰማት ሂደት ለሰኞ ተራዘመ
ሰኔ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱት የኮሚቴው አባላት የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል በሚል ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙስሊም ኢትዮጵያዊ በችሎቱ ቢታደምም፣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የማሰማቱን ሂደት በድጋሜ ወደ ሰኞ አራዝሟል። ችሎቱ የአቃቢ ህግ መስክሮችን ቃል አንብቦ ከጨረሰ በሁዋላ ተከሳሾች ለፖሊስ ሰጡት ያለውን ቃል በንባብ አሰምቷል። የፊታችን ሰኞ የመጨረሻው የፍርድ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። ...
Read More »በድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ የሚሰጠው ፍርድ ለነገ ተራዘመ
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በድምጻችን ይሰማ የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የነበረውን ፍርድ ያራዘመ ሲሆን፣ ፍርዱ ለምን እንደተራዘመ ግን በግልጽ የታወቀ ነገር የለም። በአቶ አቡበከር አህመድ መዝገብ 18 የኮሚቴው አባላት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው የመጨረሻውን ፍርድ ለመስማት ችሎት የተገኙ ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ የክሱን ጭብጥና የምስክሮችን ቃል በማጠቃለያ መልክ ...
Read More »ለመከላከያ ሰራዊት አባልነት የሚመዘገብ ወጣት መጥፋቱ እየተነገረ ነው
ሰኔ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመከላከያ ሰራዊት ያወጣው አዲስ የቅጥር ማስታወቂያ ተቀባይነት አለማግኘቱን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በሰሜን ሸዋ ከሁለት ሳምንት በፊት የወጣውን የቅጥር ማስታወቂያ ተከትሎ ተመዝጋቢ በመጥፋቱ፣ የአካባቢው ባለስልጣናት የሚያደርጉት ጠፍቷቸዋል። በአርባምንጭ ደግሞ የኢህአዴግ ካድሬዎች በመኪና እየዞሩ ወጣቱ ለመከላከያ አባልነት እንዲመዘገብ እየቀሰቀሱ ነው። ይሁን እንጅ ለጥሪው ወጣቱ የሚሰጠው ምላሽ እጅግ አነስተኛ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ። ...
Read More »