መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታዋቂዋ አርቲስት የቀብር ስነስርዓት በ ቅድስ ስላሴ ካቴደራል ወዳጅ ዘመዶቿና አድናቂዎቿ በተገኙበት ተፈጽሟል። አርቲስት ሰብለ ተፈራ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ወሎ ሰፈር እየተባለ በሚጠራው አይቤክስ ሆቴል አካባቢ በግንቦት ወር 1968 ዓም. የተወለደች ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በንፋስ ስልክ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቃለች። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም በዛው የንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የዩናይትድ አረብ ኤምሪት ዜጋ የኬንያን መንግስት ከሰሰች
መስከረም ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በንግድ ስራ የምትደዳረዋ ካሚል ሙሃመድ ታውኒ ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አላት በሚል በኬንያ ልዩ ፖሊስ ተይዛ ለሶማሊና ለኢትዮጵያ መንግስታት ተላልፋ መሰጠቷን ተከትሎ ሰቆቃ እንደተፈጸመባት ተናግራለች። ቃሏን ለፍርድ ቤት ስታሰማ እንባዋ ያቋርጣት እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል። ወ/ት ትዌኒ የህክምናዋን ወጪ ለመሸፈን የኬንያ መንግስት የገንዘብ ካሳ እንዲሰጣት ፍርድ ቤትን ጠይቃለች። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ከሰማ በሁዋላ ከአንድ ...
Read More »ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ረጅሙን የትግል ጉዞ ጀመሩ
ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድምጻችን ይሰማ የትግል ስትራቴጂውን በአዲስ መንገድ እንደሚቀይስ ማስታወቁን ተከትሎ፣ የመጀመሪያውን ትግል አንድ ቁጥር በመያዝ ትግሉን ጀምሯል። ሙስሊሙ ማህበረሰብ በቅርቡ ፍርድ ቤት በሙስሊም መሪዎች ላይ የሰጠውን ፍርድ ” የተቀበረች ፍትህ ቀባሪዋን ትቀብራለች፣ አምባገነናዊ ፍርድ አንቀበልም” የሚል መፈክር በማሰማት ተቃውሞ አሰምቷል። አሃዱን አሃድ፣ ትግላችን ይቀጥላል፣ ድምጻችን ይሰማ፣ ኮሚቴው ይፈታ፣ ሳይፈቱ ሰላም የለም የሚሉ መፈክሮችም ...
Read More »አመት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የዶሮና የቅቤ ዋጋ በእጥፍ ጭማሪ
ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሳይቷል በዘንድሮ የአዲስ አመት ገበያ፣ የዶሮ ዋጋ ከበፊቱ በእጥፍ የጨመረ ሲሆን በአቃቂና በሳሪስ አካባቢ ዶሮ ከ200 ብር እስከ 400 ብር የሚሸጥ ሲሆን፤ በግ ከ1100 እስከ 3500 ብር፣ በሬ ከ4500 እስከ 25ሺ ብር፣ ፍየል ከ750 እስከ 4ሺ ብር እየተሸጡ ነው፡፡ በሾላ ገበያ በግ ከ900 ብር እስከ 4500 ብር፣ በሬ ከ5 ሺህ እስከ 22 ...
Read More »የአዋሳ ሃይቅና የጥቁር ውሃ ወንዝ በኬሚካል መበከላቸው ተገለጸ
ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ባጠናው ጥናት ከአዋሳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሚወጣው ኬሚካል ሃይቁንና ወንዙን በመበከሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል። ከፋብሪካው የሚወጣው ውሃ በቀጥታ ወደ ጥቁር ውሃ ወንዝ የሚፈስ ሲሆን፣ ወንዙም ወደ ሃይቁ የሚፈስ በመሆኑ ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል። የኬሚካሉ ወደ ውሃው መግባት የአሳዎችን ስደት እንደሚያስከትል የሚገልጸው ጥናቱ፣ ውሃውን ለማከም አፋጣኝ እርምጃ ...
Read More »ሁለተኛው የመንግስት እቅድ በፌሽታ ይፋ ሊሆን ነው
ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው መስከረም ወር 2008 መቶ በመቶ በኢህአዴግና አጋሮቹ በተያዘው ፓርላማ ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ሁለተኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ይፋ ለማድረግ በሚል በእነሠራዊት ፍቅሬ እና ሽዋፈራው ደሳለኝ አጋፋሪነት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጅምሮ በሚሌኒየም አዳራሽ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በሚገኙበት ታላቅ የፌሽታ በዓል ተዘጋጅቷል፡፡ እነሠራዊት ፍቅሬ ከመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ...
Read More »እስረኞች ከመኪና ላይ ወርደው አመለጡ
ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከባህርዳር እስረኞችን ጭኖ አዲስ አበባ ወደሚገኘው ማእከላዊ እስር ቤት በመጓዝ ላይ ያለ ሚኒባስ ታክሲ ፣ ማለዳ 1 ሰአት ተኩል አካባቢ ሾላ ሰሜን ሆቴል ወይም መቀጠያ ሃበሻ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ሲደርስ ፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በመቆሙ በውስጡ ከነበሩት 13 እስረኞች መካከል 6ቱ ከመኪናው በመውረድ አምልጠዋል። የተቀሩት ከሚኒባስ ባለመውረዳቸው ወደ ማእከላዊ ተወስደዋል። ፖሊሶቹ የያዙትን ...
Read More »በጋምቤላ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች የኮሌራ ወረሽኝ ተቀሰቀሰ
ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመቶ ሽዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በተጠለሉባቸው የስደተኞች መጠለያዎች ውስጥ የተቀሰቀሰው የኮሌራ ወረሽኝ በአጎራባች የደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ ድንበሮች አካባቢ ስጋት እየፈጠረ ነው። ይህንን ተላላፊ ገዳይ በሽታ ለመግታት የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅትና ዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በጥምረት ክትባትና የንጹህ ውሃ አገልግሎት አቅርቦት መስጠት ጀምረዋል።በአስር የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ለሚገኙ መቶ ሰማንያ ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በቃሊቲ እስር ቤት በፍትሃዊ መንግድ ተይዘዋል ብለው እንደማያምኑ አንድ የእንግሊዝ ባለስልጣን ተናገሩ
ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቫይስ ኒውስ የተባለው ድረገጽ የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ወቅታዊ ሁኔታ ይዞ በወጣው ዘገባ እንደገለጸው፣ የእንግሊዝ ባለስልጣናት አቶ አንዳርጋቸው ታስረው ከነበሩበት ስውር ቦታ ወደ ቃሊቲ መዛወራቸው በጎ ነገር ቢሆንም፣ በቃሊቲ በጥሩ ሁኔታ ተይዘዋል ብለው አያምኑም። የእንግሊዝ የውጭና የጋራ ብልጽግና አገራት ቃል አቀባይ ” ኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም የቆየና ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው አገራት ...
Read More »በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ የወጣው ገንዘብ ለትምህርት ከተመደበው ገንዘብ በብዙ እጅ በለጠ
ጷግሜን ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ የተለያዩ አገራት በፈረንጆች አቆጣጠር ከ2008 እስከ 2012 ለትምህርት የመደቡትን በጀትና ወደ ውጭ አገራት በህገወጥ መንገድ የወጣውን ገንዘብ በማነጻጸር ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ ላይ እንደጠቀሰው ፣ በኢትዮጵያ በህገወጥ መንገድ የወጣው ገንዘብ፣ ለትምህርት ከወጣው ገንዘብ በ245 በመቶ ይልቃል። ድርጅቱ ቀድም ሲል ባወጣው ሪፖርት ከ2008 እስከ 2012 ባሉት አራት አመታት ውስጥ 3 ቢሊዮን ...
Read More »