አመት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የዶሮና የቅቤ ዋጋ በእጥፍ ጭማሪ

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሳይቷል በዘንድሮ የአዲስ አመት ገበያ፣ የዶሮ ዋጋ ከበፊቱ በእጥፍ የጨመረ ሲሆን በአቃቂና በሳሪስ አካባቢ ዶሮ ከ200 ብር እስከ 400 ብር የሚሸጥ ሲሆን፤ በግ ከ1100 እስከ 3500 ብር፣ በሬ ከ4500 እስከ 25ሺ ብር፣ ፍየል ከ750 እስከ 4ሺ ብር እየተሸጡ ነው፡፡ በሾላ ገበያ በግ ከ900 ብር እስከ 4500 ብር፣ በሬ ከ5 ሺህ እስከ 22 ሺህ ብር ሲሸጥ፤ የዶሮ ዋጋ ከ180 እስከ 350 ብር እንደሚደርስ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በካዛንቺስ አካባቢ ደግሞ በግ ከ800 ብር እስከ 3 ሺህ ብር የሚገኝ ሲሆን የዶሮ ዋጋ ከፍተኛው 400 ብር ነው፡፡ በዘንድሮ የበዓል ገበያ ለእርድ ከሚውሉ እንስሳት መካከል የዶሮ ዋጋ ከአምናው በዓል በእጥፍ በእጥፍ ዋጋ መጨመሩን ሸማቾች እየተናገሩ ነው። በሌላ በኩል በበአሉ ወሳኝ ከሆኑት መካከል በአብዛኞቹ የአዲስ አበባ የገበያ ስፍራዎች ቅቤ በኪሎ እንደየአገሩ ከ140 ጀምሮ እስከ 250 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ የቅቤ ገበያም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር እንደ የደረጃው በኪሎ ከ30 ብር ጀምሮ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ቀይ ሽንኩረት በአትክልት ተራ ገበያ በችርቻሮ ከ14.50 እስከ 16 ብር በጅምላ ደግሞ ከ13-50 እስከ 14 ብር እንደየአይነቱ እየተሸጠ የሚገኝ ሲሆነ በሾላ ገበያም ከ13 ብር እስከ 14 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ ነጭ ሽንኩረት በተለያዩ የገበያ ቦታዎች በኪሎ ከ60 ብር ጀምሮ እስከ 70 ብር እየተሸጠ ሲሆን፡፡ አይብ በኪሎ ከ40-50 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡ የአበሻ እንቁላል በአብዛኛው የመዲናችን ገበያዎች 3.30 እስከ 3.75 እየተሸጠ ሲሆን የፈረንጁ ከ3.50 እስከ 3.75 በመሸጥ ላይ ይገኛል ሲል አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዘግቧል።