የአዋሳ ሃይቅና የጥቁር ውሃ ወንዝ በኬሚካል መበከላቸው ተገለጸ

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ባጠናው ጥናት ከአዋሳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ የሚወጣው ኬሚካል ሃይቁንና ወንዙን በመበከሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ህይወት አደጋ ላይ ወድቋል።
ከፋብሪካው የሚወጣው ውሃ በቀጥታ ወደ ጥቁር ውሃ ወንዝ የሚፈስ ሲሆን፣ ወንዙም ወደ ሃይቁ የሚፈስ በመሆኑ ተጨማሪ ስጋት ፈጥሯል። የኬሚካሉ ወደ ውሃው መግባት የአሳዎችን ስደት እንደሚያስከትል የሚገልጸው ጥናቱ፣ ውሃውን ለማከም አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስቧል።