እስረኞች ከመኪና ላይ ወርደው አመለጡ

ጷግሜን ፭፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከባህርዳር እስረኞችን ጭኖ አዲስ አበባ ወደሚገኘው ማእከላዊ እስር ቤት በመጓዝ ላይ ያለ ሚኒባስ ታክሲ ፣ ማለዳ 1 ሰአት ተኩል አካባቢ ሾላ ሰሜን ሆቴል ወይም መቀጠያ ሃበሻ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ሲደርስ ፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በመቆሙ በውስጡ ከነበሩት 13 እስረኞች መካከል 6ቱ ከመኪናው በመውረድ አምልጠዋል። የተቀሩት ከሚኒባስ ባለመውረዳቸው ወደ ማእከላዊ ተወስደዋል።
ፖሊሶቹ የያዙትን ጥይት በመተኮስ እስረኞችን ለማስቆም ቢሞክሩም ፣ በተከሱ የተደናገጠው ህዝብ አብሮ በመሮጡ ለእስረኞቹ ጥሩ ሽፋን ሆኗቸው አምልጠዋል። ተጨማሪ ፖሊሶችና የደህንነት መኪኖች ወደ አካባቢው ቢደርሱም የተያዘ ሰው አለመኖሩ ታውቋል።