ኢሳት (መጋቢት 20 ፥ 2008) ከአዲስ አበባም ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አሁንም ድረስ እልባት አለማግኘቱንና በክልሉ ፍርሃት ነግሶ መገኘቱን የፈረሳይው ፍራንስ 24 የቴለቪዥን ጣቢያ ማክሰኞ ዘገበ። ከቴለቪዥን ጣቢያው ጋር ቃለ-ምልልስ ያደረጉት የጊንጪ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው አሁንም ድረስ በአካባቢው እስራት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል። የገቡበት ያልታወቀ ነዋሪዎች መሆናቸውን ያስረዱት ነዋሪዎቹ የጸጥታ ሃይሎች የሃይል እርምጃ ሲወስዱ መቆየታቸውን ተናግረዋል። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያ ወደ 30 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እዳ አለባት ተባለ
መጋቢት ፳( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ አንዱአለም ሲሳይ ታዋቂውን የኢኮኖሚክ ፕሮፌሰር ዶ/ር አለማየሁ ገዳን ያቀረቡትን ጥናታዊ ጥሁፍ በመጥቀስ እንደዘገበው የኢትዮጵያ መንግስት በውጭ ብድር ላይ ያለው ፍላጎት እየጨመረ መምጣት ፣ በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኑዋል፡፡ ፕ/ር አለማየሁ ጥናታቸውን ያቀረቡት የማህበራዊ ጥናት መድረክ ባዘጋጀው ውይይት ላይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ከቻይና 17 ቢሊዮን ዶላር፣ ከቱርክ 3 ቢሊዮን ዶላር፣ ከህንድ ...
Read More »በደቡብ ክልል ማረቆ ወረዳ በእርሃቡ ምክንያት ታዳጊ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ተገደዱ
መጋቢት ፳( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ሰሜናዊ ዞን በሃላባ ማረቆ ወረዳ የተከሰተው መጠነ ሰፊ የርሃብ አደጋ አስከፊ መሆኑን ዩኒሴፍ አስታውቀዋል። በደቡብ ክልል ከሚገኙ 136 የገጠር ወረዳዎች ውስጥ በክልሉ ትርፍ አምራች የነበሩት 73 ወረዳዎች ከፍተኛ አደጋ ይንዣበባቸው ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 45ቱ ወረዳዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት አስጊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ዩኒሴፍ አመልክቶአል፡፡ ድርቁን ተከትሎ የተፈጠረው የውሃ እጥረት ...
Read More »በስዊዘርላንድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያውያን የአድዋን በአል አከበሩ
መጋቢት ፳( ሃያ ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ቅዳሜ ማርች 27፣ 2016 በተደረገው የአድዋ በአል ዝግጅት ላይ ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያኖችና የውጭ አገር ዜጎች ተገኝተው በአሉን አክብረዋል፡፡ የበአል ዝግጀቱ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ውሂብ የሽጥላ ፣ አድዋ የኢትዮጵያች ብቻ ሳይሆን የመላው ጥቁሮች ድል በመሆኑ ወጣቶችና ታዳጊዎች ታሪካቸውን እንዲያውቁ ማድረግ ሃላፊነታችን ነው ብለዋል፡፡ በጄኔቭ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ረዳት ፕ/ር ኤስቴል ...
Read More »በኢትዮጵያ የወደፊት አቅጣጫ ላይ የመከረው ስብሰባ ተጠናቀቀ
ኢሳት (መጋቢት 19 ፥ 2008) በቪዥን ኢትዮጵያና ኢሳት በዋሽንግተን ዲሲ ጆርጅ ታውን መሪየት ሆቴል ከማርች 26-27 2016 የተዘጋጀውና በኢትዮጵያ የወደፊት ሁኔታ በለውጥ፥ ዲሞክራሲና፣ የብሄራዊ አንድነት ላይ የሚመክር ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁን የስብሰባው አዘጋጆች ገለጹ። በስብሰባው የኢትዮጵያ የወደፊት አቅጣጫ የሚመለከቱ ጉዳዮች የተዳሰሱበት ሲሆን በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ምሁራን፣ የሲቢክ ድርጅቶች እና የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጥናታዊ ጽሁፎቻቸውን ያቀረቡበትና የተሳተፉበት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ...
Read More »በደቡብ ኦሞ ህወሃት የሚያካሂደውን የመሬት ዝርፊያ መጋለጥ ተከትሎ ሰዎች ታሰሩ
መጋቢት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህወሃትና ከህወሃት ጋር ግንኙነት ያላቸው የአንድ አካባቢ ተወላጆች፣ ከ98 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዞኑን መሬት ለግብርና በሚል ከተቀራመቱትና መሬቱን አስይዘው ከፍተኛ ብድር መውሰዳቸው ከተጋለጠ በሁዋላ፣ የዞኑ ባለስልጣናት የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን ይዘው በማሰር ከአርበኞችን ግንቦት7 ጋር ግንኙነት አላቸው በማለት ክስ ለመመስረት በዝግጅት ላይ ናቸው። የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ም/ል ሊቀመንበርና የዞኑ ...
Read More »በከተሞች ብቻ 10 ሚሊዮን ራሳቸውን መመገብ የማይችሉ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ታወቀ
መጋቢት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ የተከሰተው ከፍተኛ ረሃብ 20 ሚሊዮን ያክል በገጠር የሚኖሩ ዜጎችን ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ መዳረጉን የተመለከተ ዘገባ በተደጋጋሚ ቢቀርብም፣ በከተሞች ስላሉ ራሳቸውን መመገብ ስላልቻሉ ነዋሪዎች ግን ብዙም ሲነገር አይሰማም። ይሁን እንጅ ሰሞኑን መንግስት ባመነው በ11 ከተሞች በከፋ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙና ራሳቸውን መመገብ የማይችሉ 10 ሚሊዮን ዜጎች መኖራቸውንና እነሱን ለመርዳት 300 ሚሊዮን የአሜሪካን ...
Read More »በሽብር ወንጀል የተከሰሱት በቀጠሮ ብዛት እየተጉላሉ ነው
መጋቢት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀደም ብሎ በሽብር ወንጀል የሚከሰሱ የህሊና እስረኞች ጉዳያቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛው ችሎት ሲታይ ቢቆይም፣ መዝገቡ በችሎቱ በመከማቸቱ ፣ ካለፉት 9 ወራት ጀምሮ በጸረ ሽብር አዋጁ አንቀጽ 7 የተከሰሱት በ14ኛ ወንጀል ችሎት እንዲቀርቡ ሲደርግ ቆይቷል። የዚህ ችሎት ዋና ዳኛ አቶ አባሆይ ሲሆኑ፣ ዳኛው በተለያዩ ችሎቶች እየተዘዋወሩ ስለሚሰሩ ተከሳሾች ረጃጅም ቀጠሮዎች ይሰጡዋቸዋል። ...
Read More »አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው
መጋቢት ፲፱ (አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዥው መንግስት የገባላቸውን ዋስትና አምነው ወደ አገር ቤት የተመለሱት የአክሰስ ሪል ስቴት መስራችና ባለቤት አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ተጨማሪ አዲስ ክስ የቀረበባቸው ሲሆን፣ በዋስ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ውሳኔም እንዲታገድ በመደረጉ ከእስር ሳይለቀቁ ቀርተዋል። በአቶ ኤርምያስ ላይ የቀረበው አዲስ ክስ በደረቅ ቼክ አጭበርብረዋል የሚል ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀደም ብሎ በቀረበባቸው ክስ 500 ...
Read More »በተውፊቅ መስጊድ ተቃውሞ ተካሄደ
ኢሳት (መጋቢት 16 ፥ 2008) በየሳምንቱ አርብ የሚካሄደውን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ልዩ የጸሎት ፕሮግራም ተከትሎ አርብ በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ሜክሲኮ ተብሎ በሚጠራው ተውፊቅ መስጊድ ተቃውሞ ተካሄደ። በአራተኛው ተከታታይ ሳምንት በተካሄደው በዚሁ ተቃውሞ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ይደርስብኛል ያሉትን ብሄራዊ ጭቆና በማውገዝ የተለያዩ መፈክሮችን ሲያውለበልቡ ማርፈዳቸውም ታውቋል። “ትግላችን ይቀጥላል” “ፍትህን ቀበሯት” “ኮሜቴው ይፈታ” “የነቃ ህዝብን ያሸነፈ አፈና የለም” የሚሉ መፈክሮችን ሲያውለበልቡ የነበሩት የሙስሊሙ ...
Read More »