ሚያዚያ ፲፱(አሥራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ዛሬ ጠዋት አያት ሰሚት አካባቢ ሞሃ ለስላሳ ፋብሪካ አጠገብ በመገንባት ላይ ያለ ባለ 5 ፎቅ ህንፃ የተደረመሰ ሲሆን፣ በህንፃው ውስጥ የዳሽን እና አቢሲኒያ ባንክ ቅርንጫፎች ይገኙበት እንደነበር ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡ አደጋው በስራ ሰአት ቢከሰት ኖሮ በሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ ይችል እንደነበር የገለጸው ዘጋቢያችን፣ አደጋው በየቀበሌው ያለው የግንባታ ቁጥጥር መስሪያ ቤት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ሶስት ሰዎች በቂሊንጦ ምንነቱ ያልታወቀ መድሃኒት እንድንውጥ ተጠየቅን አሉ
ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2008) ባለፈው ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ የሽብርተኛ ወንጀል ክስ የተመሰረተባቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) አመራርና ሌሎች ሶስት አባላት በቂሊንጦ እስር ቤት የማያውቁትን መድሃኒት እንዲውጡ መጠየቃቸውን ማክሰኞ ለችሎት ገለጹ። በእስር ቤቱ የቀረበላቸውን መድሃኒት አንውጥም በማለታቸውም ከሌሎች ተከሳሾች ተለይተው ለብቻቸው ለአራት ቀን ያህል በጨለማ ክፍል ውስጥ መቆየታቸውን የፓርቲ አመራት የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ለፍርድ ቤት አስረድተዋል። የፓርቲው አመራርን ጨምሮ ...
Read More »በጋምቤላ የተፈጸመውን ግድያ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ነዋሪዎች እየታሰሩ ነው
ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2008) በቅርቡ በጋምቤላ ክልል የተፈጸመን ግድያ በማውገዝ በጋምቤላ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍን ያካሄዱ ነዋሪዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች እየታሰሩ መሆናቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። በዚሁ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ፎቶግራፍ አንስታችኋል እንዲሁም ሰልፉን አስተባብራችኋል የተባሉ ነዋሪዎች ቤት ለቤት በመካሄድ ላይ ባለ የእስር ዘመቻ ሰለባ መሆናቸውን እማኞች ገልጸዋል። የመንግስት የፀጥታ ሃይሎች እየወሰዱ ባለው እርምጃ ግራ መጋባታቸውን እየገለጹ ያሉት ነዋሪዎች ከሰልፉ ጀርባ ...
Read More »ዴቪድ ካሜሩን ኢትዮጵያን ያልጎበኙበት ምክንያት አልታወቀም
ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2008) የብሪታኒያው ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን በመጋቢት ወር በኢትዮጵያ ያደርጉታል የተባለው ጉብኝት ከአንድ ወር በላይ ሳይካሄድ የቀረበት ምክንያት ሳይታወቅ ቀጥሏል። ሁለም መንግስታት ጉብኝቱ ስለቀረበት ምክንያት የሰጡት መግለጫ የለም። የብሪታኒያው ጠ/ሚ/ር ዴቢድ ካሜሩን፣ በመጪው ሰኔ ወር በኬንያ ጉብኝት እንደሚያደርጉ በጥር ወር ተገልጾ የነበረ ሲሆን፣ ይኸው የኬንያ ጉብኝት በታቀደው ጊዜ ውስጥ እንደሚካሄድ ይፋዊ መረጃዎች አመልክተዋል። የብሪታኒያው ጠ/ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን፣ ...
Read More »በጋምቤላ የተከሰተው ግጭት የግብረሰናይ ድርጅቶችን ስራ አውኳል ተባለ
ኢሳት (ሚያዚያ 18 ፥ 2008) ሁለት የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በመኪና ተገጭተው መሞታቸውን ተከትሎ፣ በጋምቤላ ከተማ የቀጠለው ግጭት የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የሌሎች ግብረ-ሰናይ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ እያወከ መገኘቱ ታወቀ። የደቡብ ሱዳን ኑዌር ተወላጆች ከካምፕ ወጥተው በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያደረሱት ጥቃት ለመበቀል የተንቀሳቀሱት ወገኖች፣ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ንብረቶች ላይ ጭምር ጥቃት ማድረሳቸው ተመልክቷል። አክሽን አጌንስት ሃንገር (ACF) የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሾፌር ሁለት የኑዌር ...
Read More »ሃረር ከቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ ተወጥራ ዋለች
ሚያዚያ ፲፰(አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከ 2 ሺ በላይ ቤቶችን ለማፍረስ በዝግጅት ጋር ያለው የክልሉ መንግስት፣ ዛሬ ከህዝብ ጋር ተፋጦ መዋሉን ወኪላችን ገልጿል። ህዝቡ “ከ10 አመታት በፊት ቤቶችን ስንሰራ ዝም ብላችሁ አሁን ለምን እርምጃ ለመውሰድ ተነሳችሁ? በክረምት ቤተሰቦቻችንን ሜዳ ላይ መበተን ሰብአዊነት ነው ወይ? ለምን ቤቶቹን ህጋዊ አታደርጉልንም?” የሚሉ ጥያቄዎችን ሲጠይቅ የቆዬ ቢሆንም፣ መልስ ሊያገኝ አልቻለም። ...
Read More »የደቡብ ኦሞ መምህራን ያነሱዋቸው አገራዊ ጥያቄዎች ባለስልጣናቱን አስቆጡ
ሚያዚያ ፲፰(አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓም የጸረ ሙስና ጥምረት በሚል ፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ቦዲ ፣ የ8 ወረዳዎች ጸረ-ሙስና ኮሚሺነሮች፣ የሃይማሮት ተቋማት ተወካዮች፣ የእድር አመራሮች፣ የመምህራን ማህበራት፣ የንግድ ማህበረሰብ ማህበር ተወካዮች፣ የሴቶችና ወጣቶች ፎረም እንዲሁም የደኢህዴን ተወካዮች በተገኙበት በተካሄደው ስብሰባ መምህራንና የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች በርካታ አገራዊ ጥያቄዎችን አንስተዋል። የንግዱ ማህበረሰብ ተወካይ ...
Read More »በጋምቤላ የቤት ለቤት ፍተሻ በመካሄድ ላይ ነው
ሚያዚያ ፲፰(አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንደዘገቡት በጃዊ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የተደረገውን ግድያ ተከትሎ በከተማው የሚታየው ውጥረት እንዳጨመረ ሲሆን፣ ዛሬ ፖሊስ አውራ ጎዳናዎችን በመዝጋት እንዲሁም በሰዎች መኖሪያ ቤቶች በመግባት ፍተሻ ሲያደርግ ውሎአል። የኑዌር ሱዳናውያን ከአንድ የመኪና አደጋ ጋር በተያያዘ የወሰዱት አሰቃቂ እርምጃ የ21 ኢትዮጵያውያንን ህይወት የቀጠፈ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያን ለምን ተጠቃን በሚል ስሜት የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ያደረጉት ...
Read More »ለእርዳታ የመጣ የስንዴ ዱቄት ተሰርቆ ለዳቦ ቤት እየተሸጠ ነው።
ሚያዚያ ፲፰(አሥራ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምስራቅ አፍሪቃ ካለፉት 50 ዓመት ወዲህ ባልታዬ ከፍተኛ በሆነ ድርቅ መጠቃቱን ተክቶሎ በኢትዮጵያ የረሀብተኛ ቁጥር 20 ሚሊዮን መድረሱን የመንግስታቱ ድርጅትና የዓለማቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ሪፖርት ያሳያል። ከነዚህ ተረጅዎች መካከል 8 ሚሊዮን ያህሉ ህይወታቸው በቋፍ ላይ የሚገኝ ህጻናት ናቸው። የተረጅዎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ የማሻቀቡን ያህል ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ የቀረበው የእርዳታ ጥያቄ በበቂ ሁኔታ ምላሽ ...
Read More »በሶማሊና አፋር ክልሎች በቅርቡ የደረሰው ጎርፍ የእርዳታ አቅርቦት ለማድረስ ከፍተኛ እንቅፋት መሆኑን የእርዳታ ተቋማት አስታወቁ
ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2008) በቅርቡ በሶማሊና አፋር ክልሎች የደረሰው የጎርፍ አደጋ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ሰዎች የእርዳታ አቅርቦት እንዳይደርስ ተፅዕኖ መፍጠሩን የእርዳታ ተቋማት ሰኞ አስታወቁ። ከ20 ለሚበልጡ ሰዎች ሞት ምክንያት ሆኖ የነበረው የጎርፍ አደጋ በርካታ የትራንስፖርት መሰረተ-ልማቶችን በማውደሙ የእርዳታ እህል ለተረጂዎች እየደረሰ እንዳልሆነ የኖርዌይ የስደተኞች ኮሚሽን ገልጿል። በሶማሊ ክልል የድርጅቱ ተወካይ የሆኑት ሞሃመድ ሃሰን ለችግሩ አስቸኳይ መፍትሄ ካልተገኘለት በርካታ ...
Read More »