ሰኔ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብአዴን ህዳር 11 ቀን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ባከበረ ማግስት ፣ የብአዴን ነባር ታጋዮች “እኛ ከህውሃት አንሰን ታይተናል” ሲሉ በስብሰባ መድረኮች ላይ አሰተያየት ከሰጡ በሁዋላ ለ246 ነባር ታጋዮቹ እውቅና ለመስጠት ተገዷል። 67 ተዋጊዮቹ ከአዲስ አበባ የመጡ ሲሆን፣ 200 የሚሆኑት አባሎቹ ደግሞ ከዋግ ህምራ ሰቆጣ የመጡ ናቸው፡፡ ነባር አባሎቹ ላለፉት 25 ዓመታት ተረስተው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
አጣዳፊ ትውከትና ተቅማት አጣዳፊ በሽታ በአዲስ አበባ ተከሰተ
ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008) ሰሞኑን በተለያዩ ክልሎች ተከስቶ የነበረው የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ በአዲስ አበባ ከተማ መሰራጨት መጀመሩን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አርብ አስታወቀ። በዚሁ በሽታ ምልክት የታየባቸው ሁለት ህሙማን በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ የተገኙ ሲሆን፣ ግለሰቦቹ ወደ ጤና ተቋማት ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የበሽታው ስርጭት በአጭር ጊዜ ሊሰራጭ የሚችል በመሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ጥንቃቄን እንዲያደርጉ አሳስቧል። ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ዳባት የተከሰተው ተቋውሞ እስካሁን እልባት አላገኘም
ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008) ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ከተማ የኤሌክትሪክ ሃይል ማሰራጫ መነሳት ጋር የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አርብ ድረስ እልባት አለማግኘቱንና የከተማዋ አስተዳዳሪዎች ከተማዋን ለቀው ወደጎንደር ከተማ መሰደዳቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ። በሃይል ማሰራጫው ማሽን መነሳት ተቃውሞ ሲያቀቡ የነበሩ ነዋሪዎች የወልቃይት ጉዳይ እልባት እንዲያገኝ ሲሉ አዲስ አስተዳደራዊ ጥያቄን ማቅርብ መጀመራቸው ታውቋል። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የዳባት ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ ...
Read More »የተቅማጥ በሽታ በኦሮሚያና ሶማሊያ ክልል በድጋሚ በወረርሽን መልክ ተቀሰቀሰ
ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008) በቅርቡ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ተቀሰቀሶ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የነበረው አጣዳፊ የተቅማጥ በሽታ በኦሮሚያና ሶማሊያ ክልል በድጋሚ በወረርሽን መልክ ተቀሰቀሰ። በሁለቱ ክልሎች በሚገኝ በርካታ ዞኖች በመሰራጨት ላይ ያለው በሽታ ለመቆጣጠር ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በድርቁ ዙሪያ ይፋ ባደረገው ሪፖርት መልክቷል። በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች ተከስቶ በነበረው በዚሁ በሽታ 14 ሰዎች ...
Read More »በሰብዓዊ መብት ሽፋን በኤርትራ ላይ የተላለፈው ውሳኔ የኢትዮጵያውያን ነጻነት ፈላጊዎችን ኢላማ ያደረገ ነው ተባለ
ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008) በሰብዓዊ መብት ሽፋን በኤርትራ ላይ እየተላለፈ ያለው የፖለቲካ ውሳኔ፣ ከኤርትራውያን ባሻገር ኢትዮጵያውያን ለውጥ ፈላጊዎች ጭምር ኢላማ ያደረገ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ የኤርትራው ባለስልጣን ገለጹ። በእኛ በኩል የምንችለውን እያደረገን እንገኛለን ያሉት አቶ የማነ ገብረዓብ፣ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መርማሪ አባላት ኤርትራን በተመለከተ ያወጡትን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሪፖርት በተመለከተ ከኢሳት ጋር ...
Read More »በማላዊ ታስረው ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን 14 ህጻናትን መታደጉን አለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት አስታወቀ
ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008) የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት በማላዊ እስር ቤቶች ለከፋ የምግብ እጥረት ከተዳረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል 14 ህጻናት መታደግ መቻሉን አስታወቀ። የማላዊ መንግስት በበኩሉ ወደሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው የተላለፈባቸውን የእስር ቅጣት ያጠናቀቀ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በገንዘብ እጥረት የተነሳ ወደሃገራቸው ሊመለሱ አለመቻሉን ገልጿል። የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በበኩላቸው በሶስት እስር ቤቶች የሚገኙ ከ100 በላይ ስደተኛ ...
Read More »በአልሸባብ የተገደሉ ወታደሮች ወደ አገራቸው መጥተው በክብር እንዲቀበሩ የሚጠይቁ አስተያየቶች እየቀረቡ ነው
ሰኔ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት ያነጋገራቸው በአገር ውስጥ የሚገኙ ሰዎች መንግስት በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው ሁሉ ለሟቾች ኢትዮጵያውያንም የክብር አቀባበል ሊያደርግላቸው ይገባል ይላሉ። የሞተ ሰው የለም በማለት መካድ ህዝብን ለማሞኘት መሞከረው ነው ሲሉ ያክላሉ። አልሸባብ የተባለው የሶማሊያ ታጣቂ ቡድን በአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ቡድን በደረሰበት ተደጋጋሚ ጥቃት ከዋና ከዋና የሶማሊያ ግዛቶች ለቆ ቢወጣም፣ ተከታታይ የደፈጣ ጥቃቶችንና የቦንብ ፍንዳታዎችን ...
Read More »በርካታ ጥራት አልባ የኮንዶሚኒየም ቤቶች በነዋሪዎች ህይወት ላይ አደጋ ደቅነዋል ተባለ
ሰኔ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በመገንባት ላይ ያሉ በርካታ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ከጊዜ በሁዋላ በተገልጋዮች ህይወት ላይ አደጋ መደቀናቸውን የግንባታ ባለሙያዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ባለሙያዎቹ እንደሚሉት አብዛኞቹ ቤቶች የሚሰሩት አስቀድሞ ጥልቅ የሆነ የአፈር ምርመራ ሳይደረግባቸው በመሆኑ ከጊዜ በሁዋላ ጉዳት ማስከተላቸው አይቀሬ ነው። መሃንዲሶች እንደሚሉት አብዛኛውን ጊዜ የኮንዶሚኒየም ቤቶች የሚገነቡት ሜዳ እንደተገኘ እንጅ በትክክል የአፈር ምርመራ ተካሂዶባቸው ባለመሆኑ፣ ከጊዜ ...
Read More »የህወሃት ደጋፊዎች የተቃዋሚዎችን ህዝባዊ ስብሰባ ለመቃወም በአውሮፓ የሚገኙ ደጋፊዎቻቸውን ሰልፍ መጥራታቸው ታወቀ።
ሰኔ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ በኖርዌይና በስዊትዘርላንድ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰብ ተግባር ያከናወነው አርበኞች ግንቦት ሰባት ነገ ቅዳሜም ተመሳሳይ ህዝባዊ ስብሰባ በጀርመን ፍራንክፈርት ለማድረግ ዝግጅቱ መጠናቀቁ የታወቀ ሲሆን ይህን ስብሰባ ለመቃወም መንግስት በኤምባሲው አማካይነት የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል። የተቃውሞ ሰልፉን ለሚወጡ የመንግስት ደጋፊዎችም ዛሬ ምሽት በፍራንክፈርት ከተማ ሆቴል ተይዞ የእራት ግብዣ እንደተሰናዳም የደረሰን መረጃ ...
Read More »አልሻባብ 43 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉ ተነገረ
ኢሳት (ሰኔ 2 ፥ 2008) በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አክራሪው የአልሻባብ ቡድን 43 የኢትዮጵያ ወታድሮችን መግደሉ ተነገረ። ግድያው የተፈጸመው የአልሻባብ የአጥፍቶ ጠፊዎች የወታደራዊ ሰፈር ዋናውን በር በመኪና ላይ በተጠመደ ፈንጅ በማጋየታቸው ሲሆን፣ ሟቾቹ የኢትዮጵያ ወታደሮች ለአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) ይሰሩ የነበሩ ናቸው ተብሏል። ወታደራዊ ጥቃቱን የፈጸምነው እኛ ነን ሲል የአልሻባብ ወታደራዊ ተልዕኮዎች ቃል አቀባይ አብዲያሲስ አቡ ሙሳብ ለሮይተርስ መናገራቸው ...
Read More »